Orgin Man Kind

Orgin Man Kind prodide crediable information socio-economic and poletical aspects of Africa and all over our globe .

Internal aggression of Sudan strongly continued by changing its direction from oil to military transitional leaders reca...
12/06/2021

Internal aggression of Sudan strongly continued by changing its direction from oil to military transitional leaders recalling from it's power said the young Sudanese people.

13/04/2021
ሰበር ዜና በአዲስ አበባ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የትራንስፖርት ዘርፍ ሀላፊ የነበሩት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ሰለሞን ኪዳኔ አብሯቸው የነበረው የጌታቸው አስፋ ወንድም ዳንኤል አ...
07/01/2021

ሰበር ዜና

በአዲስ አበባ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የትራንስፖርት ዘርፍ ሀላፊ የነበሩት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ሰለሞን ኪዳኔ አብሯቸው የነበረው የጌታቸው አስፋ ወንድም ዳንኤል አሰፋ እጅ አልሰጥም በማለት እርምጃ ሲወሰድበት ኢ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በፍቃደኝነት እጅ ሰተው በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል::

ኢ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በትራንስፖርት ዘርፍ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንትባ በመሆን ከለውጡ በኃላ ከተሾሙ ከአንድ አመት ተክል በኃላ ህወሓት ወደ መቀሌ ሸሽቶ ከተበቀ በኃላ በህወሓት አባልነታቸው ስለቅጠል ከምክትል ከንቲባ ማዕረግነታችው ሲነሱ እሳቸውም ወደ መቀሌ በመሄድ ከህወሓት ጋር መሽገው ስራ ስጎነጉኑ የነበሩ ወጣት ነበሩ:: በነገርችን ላይ ኢ/ር ሰለሞንን ከአንድም ሶስት ግዜ በኢንተርቪውና በጥያቄ ጉዳይ በስልክ አውርቻቸው አውቃለሁ ወጣት ነህ ለሀገርህ ብዙ ትሰራለህ በርታ ብየውም አውቅ ነበር::

13/09/2020

prodide crediable information socio-economic and poletical aspects of Africa and all over our globe .

13/05/2020

Posting transactions up to financial reporting and financial decision

ፋሲል ከነማ ከድሬደዋ ከነማ መጋቢት 04-2012 በ17ኛው ሳምንት ጨዋታ ይገናኛል በመሆኑም ፋሲል ከነማ የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ መሪ እንደ መሆኑ መጠን ይጠበቃ ደረጀውን አስጠብቆ እንደሚወጣ!...
12/03/2020

ፋሲል ከነማ ከድሬደዋ ከነማ መጋቢት 04-2012 በ17ኛው ሳምንት ጨዋታ ይገናኛል በመሆኑም ፋሲል ከነማ የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ መሪ እንደ መሆኑ መጠን ይጠበቃ ደረጀውን አስጠብቆ እንደሚወጣ!!

09/01/2020

ህወሓት ራሱን ችሎ ከኢህአዴግ ጋር የጀመረውን እንዲጨርስ እንመክራለን - ጀዋር መሀመድ ለቢቢሲ

: የተለያዩ ፓርቲዎች አብረው ለመሥራት የሚያስችሏቸው እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው። አሁን አንተ ኦፌኮን ተቀላቅለሀል። ሕወሓት ከእናንተ ጋር አብሮ የመሥራት ጥያቄ ቢያቀረብ ትቀበላላችሁ?

ጀዋር፡ በሕወሓትና በእነ ዐብይ መካከል የተፈጠረው በአንድ ቤተሰብ ውስጥ፣ በአንድ ፓርቲ ውስጥ የተከሰተ ግጭት ነው። ይህ ግጭት እንግዲህ ሕወሓት በበላይነት ኢሕአዴግን ሲመራ የነበረ ነው። አብረው አገር ሲዘርፉ ሲጎዱና ሕዝብን ሲያሰቃዩ ነበር። አሁን ይኼ ለውጥ ምስቅልቅላቸውን አውጥቷቸዋል። በመካከላቸው ያለው ግጭት ፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን የደህንነትም ጭምር ነው።

ከሁለቱ አንዱን በማቅረብ የዚህ ውስብስብ፣ ብዙ ቆሻሻ ያለበት ግጭት አካል መሆን አንፈልግም። ሕወሓትም ሕገ መንግስቱንና ሕጉን በጠበቀ መልኩ ክልሉን እንደሚያስተዳድር ፓርቲ መብትና ግዴታውን እንደሚወጣ እንጠብቃለን። የፌደራል መንግሥቱም ሆነ የፌደራል መንግሥቱን እየመሩ ያሉት የቀድሞ ኢሕአዴጎችም ግጭትን ባረገበ መልኩ ከሕወሓት ጋር አላስፈላጊ እሰጥ አገባ ውስጥ ገብተው ትግራይንና የፌደራል መንግሥቱን አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ ከማስገባት እንዲቆጠቡ በተደጋጋሚ ስንመክር ነበር። አሁንም የምንመክረው እርሱኑ ነው።

ግን እንደኔ ግምትም ሆነ ምክር ሕወሓትን አሁን ወደ ተቃዋሚው በማምጣት በኢሕአዴግ መካከል የተፈጠረውን ግጭት ወደ ራሳችን መጋበዝ የለብንም።

ሕወሓትም ራሱን ችሎ ከኢሕአዴግ ጋር የጀመረውን፣ ከቀድሞ ባልደረቦቻቸው ጋር የጀመሩትን፣ በሰላማዊና ሕጋዊ መልኩ እንዲጨርሱ [ነው የምንመክረው]። [ቀሪው ነገር] ወደፊት በሂደት ምናልባት ከምርጫው በኋላ አሸንፈው የሚመጡ ከሆነ የሚታይ ይሆናል።

ከዚያ ወዲህ ግን የኢህአዴግን የበሰበሰና የተበለሻሸ፣ ብዙ ግለሰባዊ ሽኩቻዎች ያሉበት፣ የአገር ደህንነትን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ሽኩቻዎችና ግጭቶችን፣ ወደ ተቃዋሚው በማምጣት ተቃዋሚውን የዚያ ሰለባ ማድረግ ትክክል ነው ብዬ አላምንም። እኔ ያለሁበትም ሆነ ሌሎቹ ፓርቲዎች እዚህ ውስጥ አይሳተፉም።

: የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የመደመር ፍልስፍና እንደማያምኑ፣ የተቻኮለ መሆኑንም መግለጻቸውን ይታወሳል። በኋላ ደግሞ ተመልሰው አብረው ለመሥራት ተስማምተዋል። እንደዚህ አይነት ልዩነቶች ሲፈጠሩ ይህ የመጀመሪያው አይደለምና እነዚህ መንገራገጮች ያሰጉሀል?

#ጀዋር፡ ለማ መገርሳ የዚህ አገር ታላቅ ባለውለታ ነው። ይህ ትግል እየጦፈ በመጣ ወቅት፣ ሥርዓት ሳይፈርስ አገር ለአደጋ ሳይጋለጥ፣ በድርድር የሚካሄድ ሽግግር እንዲካሄድ፣ የእርሱ ቁርጠኛ አቋም፣ አመራር በጣም በጣም ወሳኝ ነበር። የአገራችን ከፍተኛ ባለውለታ ነው።

ያም ብቻ ሳይሆን ዐብይ አሕመድን ወደ ሥልጣን ያመጣው ራሱ ለማ ነው። ከዚያ በኋላ ዐብይንም አገርንም በከፍተኛ ትዕግሥት አገልግሏል። ልዩነቶች መፈጠር ከጀመሩ ቆይተዋል። ግለሰባዊ አይደሉም። ሽግግሩ የተመራበት አካሄድ ትክክል አይደለም የሚል አቋም ወስዷል። ይህንን በውስጥ የምናውቀው ነው። ሆኖም ግን ሁለቱ ካላቸው ከፍተኛ ሚና አንጻር ሽግግሩ ላይ የሚኖረውን አደጋ ለማ በደንብ አድርጎ የሚረዳ ሰው በመሆኑ የተነሳ ረዥም ጊዜ በውስጥ ብቻ በተወሰኑ ሰዎች መካከል ይዞት ነው የቆየው። መጨረሻ ላይም ተቃውሞ ውህደቱን በአቋም ማክሸፍ ይችል ነበር። ያን ማድረግ ሊያመጣ የሚችለውን ግጭትና አለመረጋጋት በመገንዘብ ውህደቱ ከተፈፀመ በኋላ አቋሙን ለሕዝብ ግልጽ አድርጓል።

ከዚያ በኋላም ነገሮች እየተባባሱ እንዳይሄዱ፣ በኦሮሚያ ውስጥ ሰፊ የሆነ በቢሮክራሲው ችግር መፈጠር ስለጀመረ ነገሮችን በውይይት እንፈታለን በሚል ነገሮችን ወደ መረጋጋት መመለስ ችሏል።

ከዚህ አንጻር ለማ አገርን ለአደጋ የሚያደርስ፣ ክልሉንም ፌዴሬሹኑንም ለአደጋ የሚጥል እርምጃ ይሠራል ብዬ አላምንም። ዐብይም ቢሆን ይህንን የሚረዳ ይመስለኛል። ወደፊትም እንግዲህ እየተወያየን፣ እየተረዳዳን ወደፊት የምንሄድ ነው የሚሆነው። ለማ ቀላል ሰው አይደለም።

አሁን ብቻ ሳይሆን፣ ወደፊትም አገሪቱ ለምትወስደው እርምጃ ከፍተኛ ሚና የሚኖረው ሰው ነው። ከፍተኛ እውቀት፣ ተሰሚነት፣ ያለው ግለሰብ ነው። ወደፊትም ከተስማሙና ፓርቲውን ማሻሻል ሊያቀራርባቸው የሚችል ከሆነ በዚያ፣ ካልሆነ ግን ከተቃዋሚው ጋር በመሆን በግለሰብ ደረጃም ቢሆን ለአገር የሚጠቅም፣ ይህንን ሽግግር የሚያሳካ ሥራዎችን ይሠራል ብዬ ነው የማስበው።

ለማ እንግዲህ የፖለቲካ መሪ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ አዋቂና እንደአገር ሽማግሌም የሚያረጋጋ ሰው ነው። ወደፊትም ለማ ብዙ ነገር ይሠራል የሚል እምነት አለኝ።

Address

Addis Ababa
Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Orgin Man Kind posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Orgin Man Kind:

Share