12/07/2025
ማንኛውም የዶሮ እርባታ ሊጀምር ያሰበ ግለሰብ
ወደ ዶሮ እርባታ ከመግባቱ በፊት መልስ ሊሰጥባቸው የሚገቡ መሰረታዊ ጥያቄዎች
1) ዶሮ እርባታ ከመጀመራችን በፊት ቀድመን
ምን ምን ማወቅ ይገባናል ?
1-2) ገንዘብ ግዜ ስለ ዶሮ እርባታ ዕውቀት ቦታ
ፍላጎት ትጋት አለን ወይ ?
1-3) የዶሮ እርባታ ለመጀመር የመደብነው
በጀት ምን ያህል ነው፡ መኖዋቸውን እና ሕክምናቸውን ወጪ ጨምሮ ምን ያክል ዶሮችን ለማርባት ያስችለናል
1-4) ዶሮ እርባታ ለመጀመር የተዘጋጀ ቦታ አለን ወይ ምን ያህል ካሬ ለዶሮ እርባታ ያዘጋጀነው ቦታ ምን ያህል ዶሮ ይችልልናል
1-5) ስለ ዶሮች እና ዶሮ እርባታ በባለ ሞያ ስልጠና ወስደናል ወይ ?
ስልጠና ባንወስድም የተለያዮ ትክክለኛ መረጃዎችን በመፅሐፍ በፅሁፍ በምክር ወስደናል ወይ?
አከባቢያችን ላይ ስልጠናና ምክር ሊሰጠን የሚችል የበቃ ባለሞያ አለ ወይ ? ከሌለስ ከማበራዊ ሚዴያ ከእንተርኔት ከኦን ላይን አማካሪዎች በስልክም ጭምር ጠቃሚ መረጃዎችን የመሰብሰብ ብቃታችን ምን ያክል ነው ?
2) የዶሮ ዓይነት ዝርያ
በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጲያ ላይ ለእርባታ የሚመረጠው የዶሮ ዝርያ ዓይነት የትኞቹ ናቸው ?
2-1) ለስጋ የትኞቹ ?
2-2) ለእንቁላል የትኞቹ ?
2-3) ከጊዜ አንፆር ፈጥነው የሚደርሱት የትኞቹ ናቸው ?
2-4) ከዶሮ መኖ አንፆር ብዙ መኖ የማይፈጁትስ የትኞቹ የዶሮ ዝርያወች ናቸው ?
3) የዶሮ መኖ
3-1) ለርቢ የመረጥነው ዶሮ በቀን ምን ያህል
ግራም በአግባቡ የተዘጋጀ መኖ ይፈልጋል በሳምንት በወርስ ?
3-2) አንድ ለማርባት የመረጥነው ዶሮ ዓይነት የመኖ ወጪ
ወደ ገንዘብ ሲለወጥ በቀን በሳምንት በወር
ምን ያህል ነው
4) ገበያ
4-1) ፍላጎት አከባቢያችን ላይ የዶሮ ስጋ ፍላጎት ምን ያህል ነው የዕንቁላልስ ፍላጎት ምን ያህል ነው አከባቢያችን ላይ የገበያው ፍላጎት ዝቅተኛ ከሆነ ሌላ አከባቢ የገበያ ትስስር እንዴት መፍጠር እችላለሁ ?
4-2) የተሻለ የገበያ ፍላጎት የት ነው ያለው
እንዴትስ ተደራሽ አደርጋለው
5) ሕክምና
5-1) የዶሮ ሕክምና እንዴት ማግኘት ይቻላል
በአከባቢያችን የእንስሳት እክምና አገልግሎት አለ ወይ በተለይ የዶሮ
5-2) ለዶሮች ክትባት ማግኘት ግዴታ ነው አከባቢዬ ላይ ማግኘት እንዴት እችላለው
እነዚህንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች መልስ ሊያገኝላቸው ግድ ይላል
መልካም ቀን Minch accubreed