Ethiopian History

Ethiopian History Oromo First

12/04/2021

We are looking for executive secretary

15/01/2021

ሱዳን ፤ግብጽ እና ኢትዮጵያ
(ስዩም መርጋ ጥር 2013 ዓ.ም)
ታሪክን የኋሊት መዝዘን ብናይ የእነዚህ ሶስት ሀገራት የግጭት ታሪክ በትንሹ ሀለት መቶ አመታትን አስቆጥሯል፡፡ ልክ የዛሬ 215 አመት መለትም በ1801 ዓ.ም በጎርጎሮሳዊያን ዘመን አንድ ሞሓመድ አሊ የተባለ የአልባኒያ ሰዉ ጥቂት የኦቶማን ቱርክ ጦር እየመራ ከ አንግሊዝ ወታደር ጋር ግብጽን ወርረዉ የነበረዉን የፈረንሳይ ጦር ላይ ዘመተ (በ 1789 ዓ.ም የፈረንሳዩ አብዮተኛ መሪ ናፖሊዎን ግብጽን ይዞ ነበር)፡፡ ከአራት አመት በኋላ ሞሐመድ አሊ የግብጽ መሪ ሆነ (እስከ 1952 ዓ.ም ድረስ ግብጽን የመራዉ ሞሐመድ አሊ የመሰረተዉ ስረዎ መንግስት እንደ ሆነ ልብ ይሏል)፡፡ ሞሐመድ ሁለት ዋና ዋና ፖሊሲዎችን ቀርጾ ወደ ስራ ገባ 1ኛ- ለአስተዳደሩ የሚመቹ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መደላደል መፍጠር ሲሆን 2ኛዉ ደግሞ ታላቋን ግብጽ መገንባት ነዉ፡፡ ለዚህም ሲባል በ1821 ዓ.ም ግብጽ ሱዳንን ወረረች ትንሽ ቆይተው ሱዳንን እንደ ቤዝ እየተጠቀሙ ግብጾች የኢትዮጵያን የድንበር ከተሞችን እነደ መተማ ፤ ጉባ እና ኮሞሻ ሼክደሞችን ወረሩ፡፡ የግብጽ ዋነኛ የወረራ ግብ በኢትዮጵያ የሚገኘዉን የጥቁር አባይ ወንዝን መቆጣጠር ነዉ፡፡ ከጥንት ጀምሮ የግብጽ ህልዉና በአባይ ወንዝ ላይ የተመሰረተ ብቻ ሳይሆን እነደ ሀገር የተፈጠረችዉም በአባይ ወንዝ ምክንያት ነዉ፡፡ ግሪካዊ ሄሮዶተስ ‹ግብጽ የአባይ ስጦታ ናት› (Egypt is the Gift of Nile) ማለቱም ለዚህ ነዉ (አባይ የግብጽ ስጦታ ነዉ አላለም)፡፡ ለዚህም ነዉ አጼ ዘርዐ ያዕቆብ ለግብጽ መሪዎች በቁጣ በጻፈዉ ደብዳቤ ‹እግዚአብሔርን ባልፈራ ኖሮ የአባይን አቅጣጫ እቀይረዉ ነበር ›ማለቱ (had it not been for the fear of God, I could divert the direction of Nile).
በሰሜን በኩል የነበረዉን የግብጽን ወረራ እነ ደጃች ዉቤ የሲሜኑ ገዥ፤ደጃች ኪንፉ የቁኣራ ገዥ ለመመከት ሞክረዉ ነበር፡፡ በምዕራብ በኩል ደግሞ እነ በከሬ ጎዳና የሌቃ ነቀምቴ ሞቲ እነ ቱሉ የ ሌቃ ቄለም ሞቲ እና የጊዳሚ መሪዎች የግብፅን ወረራ መክተው ነበር። ልክ እነደ ዛሬዉ ሁሉ ኢትዮጵያ የዉሰጥ የፖለቲካ ችግር በነበረበት የዘመነ መሳፍንት ጊዜ ቀን ጠብቀዉ ነበር ግብጾች ኢተዮጵያን ለመዉረር የተነሱት፡፡ ከዚያን ዘመን ጀምሮ ሱዳኖች በተለይ መሓዲስቶች የግብጽ የጦር ፈረስ በመሆን ያገለግሉ ጀመር፡፡ ከዚህ ታሪክ የሚከተሉትን ሶስት ነገሮችን እንማራለን
1ኛ- ግብጽ በሱዳን እጅ ኢትዮጵያን እየወጋች እነደነበረ እና ዛሬም የሱዳን ጦር የግብጽ ጉዳይ እየፈጸመ እንደ ሆነ፡፡
2ኛ- ኢትዮጵያ በዉስጥ ጉዳይ ስትጠመድ በዉጭ ሀይል የመወረር አድሉ ከፍ ያለ እነደ ሆነ፡፡ በተለይም ግብጽ እና ሱዳን ክፉ ቀን እየጠበቁ ኢትዮጰያን ለመዉረር ሁል ጊዜ በዝግጅት እንደሚኖሩ ፡፡ (የአሁኑን የሱዳን እና የግብጽ ወረራ የአሜሪካም እጅ አይዞ ባይነትም የታከለበት ነዉ፡፡ የሰሞኑን የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሹም በካይሮ እና ካርቱም የነበረዉ ጉብኝት የዚህ ማሳያ ነዉ)
3ኛ- ግብጾች አባይ ወንዝን በበላይነት መጠቀም ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን በመዉረር የአባይ ወንዝን ምንጭ የመቆጣጠር ታሪካዊ ፍላጎት ያላቸዉ መሆኑን ታሪክ ያስረዳናል፡፡

Address

Adama
1020

Opening Hours

09:00 - 17:00

Telephone

+251576617169

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian History posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share