Helena Love

Helena Love Digital Marketing expert

Are you looking to capitalize on Ethiopia's national shift away from single-use plastics? This comprehensive feasibility...
06/08/2026

Are you looking to capitalize on Ethiopia's national shift away from single-use plastics? This comprehensive feasibility study for a paper bag manufacturing plant in Addis Ababa provides a complete, bank-ready roadmap for success. Designed to capture a rapidly growing eco-friendly packaging sector, this document covers every operational, technical, and financial requirement to launch a highly profitable factory.
Download it here..

This comprehensive feasibility study for a paper bag manufacturing plant provides a complete, bank-ready roadmap for success. Designed to capture a ra...

29/07/2026

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሙፈሪያት ካሚል የሚመሩት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመቻችቶታል በተባለ ወደ ስዊድን አገር የሰለጠነ የሰው ኃይል ስምሪት ዕቅድ፣ ከ20 ሺህ በላይ ዜጎች ለእንግልት እና ለገንዘብ ብዝበዛ መዳረጋቸውን አመለከቱ። ሕጋዊውን አሰራር ወደ ጎን በመተው በግል ጥቅም በተደለሉ እና በቅርቡ በቁጥጥር ስር በዋሉ የሚኒስቴሩ ኃላፊዎች ጣልቃ ገብነት ምክንያት ዜጎች ያወጡት ገንዘብ ሳይመለስላቸውና የጠበቁትን የሥራ ዕድል ሳያገኙ ቀርተዋል።

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር የስራ ስምሪትን በህጋዊ መንገድ ማመቻቸት ከጀመረ ወደ አምስት ዓመታት ገደማ ሆኖታል። ይህንን ተከትሎ ዜጎች በየወረዳቸው በሚገኙ የሚኒስቴሩ ጽህፈት ቤቶች የጣት አሻራ በመስጠት እና መለያ ኮድ በመቀበል ተመዝግበው ነበር።

በሂደትም "ሚሊዮን" የተባለ የግል ኩባንያ የሰለጠነ የሰው ኃይልን ወደ ስዊድን ለመውሰድ ፍላጎት እንዳለው በመግለጽ፣ ለ20 ሺህ ያህል ዜጎች በስልክ አጭር የጽሁፍ መልእክት (ቴክስት) ጥሪ ቀረበላቸው። አመልካቾች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባወጣቸው 17 የተለያዩ የሙያ ዘርፎች (ዲፓርትመንቶች) ተመዝግበው "ተመርጣችኋል" የሚል ምላሽ ደረሳቸው።

ዜጎች ይህንኑ "ተመርጣችኋል" የሚል መረጃ በመያዝ ወደ ስራና ክህሎት ቢሮ ሲያቀኑ፣ የስልጠና ኮርስ መውሰድ ግዴታ መሆኑ ተነገራቸው። ለዚህም እያንዳንዱ አመልካች በቴሌብር አማካኝነት 3,600 ብር ከፍሎ ኮርሱን ወሰደ። ሆኖም ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ተስፋ የተደረገው የጉዞ ሂደት ቆሞ "ጠብቁ" ከሚል በቀር ምንም ዓይነት ተጨባጭ እርምጃ አልተወሰደም።

ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰቡት ተጎጂዎች በአዲስ አበባ ወደሚገኘው የሚኒስቴሩ ዋና ቢሮ በማቅናት ጥያቄያቸውን በደብዳቤ አቀረቡ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሰጠው ምላሽ፣ "አቀጣጣሪው ኩባንያ የሰርቪስ ክፍያ ስለጠየቀን እና እሱን መክፈል ስላልቻልን ጊዜ ስጡን" የሚል ሰበብ አቀረበ። ዜጎቹ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዘንድሮ ጥር 2018 ዓ.ም ድረስ በአጠቃላይ አራት ጊዜ "ወይ ጉዟችን ይሳካ፣ አሊያም ገንዘባችን ይመለስ" የሚል ደብዳቤ ቢያስገቡም ሰሚ ጆሮ አላገኙም።

ከዚህ ውዝግብ ጀርባ ያለው ዋነኛ ችግር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር በዋሉት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች አቶ ብርሃኑ አለቃ እና አብርሃም አስራት የተፈጠረ መሆኑ ተጋልጧል።

የስዊድን አገር ኩባንያ ኢትዮጵያዊ ተወካይ የሆነው አቶ ቢኒያም ፍቃዱ በተደጋጋሚ እንዳስረዳው፣ የኩባንያው ፍላጎት ሰራተኞችን በጥሩ የትምህርት ደረጃቸው እና በስራ ልምዳቸው ላይ ብቻ ተመስርቶ በነጻ ውድድር መመልመል ነበር። ሆኖም በስራና ክህሎት ሚኒስቴር በኩል ጉዳዩን ይመሩ የነበሩት እነ አቶ ብርሃኑ፣ በራሳቸው መንገድ መርጠው (በጉቦ እና በዘመድ አዝማድ) የፈለጉትን ሰው ብቻ ለመላክ ጥያቄ አቀረቡ።

ኩባንያው አሰራሩ ከህግ እና ከሙያ ሥነ-ምግባር የጸዳ መሆን እንዳለበት በማሳሰብ የባለስልጣናቱን የሙስና ጥያቄ ውድቅ በማድረጉ፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል መግባባት ሊፈጠር አልቻለም። በዚህም ምክንያት የስምሪት ውሉ ሙሉ በሙሉ ሊቋረጥ ችሏል።

ይህ በህገ-ወጥ ባለስልጣናት እና በኩባንያው መካከል የተፈጠረው አለመግባባት የብዙ ሺህ ዜጎችን ህይወት፣ ጊዜ እና ተስፋ አበላሽቷል። ተጎጂዎቹ ክፍያቸው እንዲመለስላቸው ቢጠይቁም፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ኃላፊዎች "የከፈላችሁት ለወሰዳችሁት ኮርስ ነው" በሚል ሰበብ ገንዘባቸውን ሊመልሱላቸው ፈቃደኛ አልሆኑም።

መንግስት በቅርቡ በስራና ክህሎት ሚኒስቴር ውስጥ የተንሰራፋውን ሙስና ለማጽዳት የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ እነ አቶ ብርሃኑ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ቢታወቅም፣ በስማቸው እና በስዊድን የስራ ዕድል ተስፋ ተታልለው ገንዘባቸውን የተነጠቁት እና እንግልት የደረሰባቸው ዜጎች አሁንም ፍትህን እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

27/07/2026

#አሳዛኝ ዜና እና የፍትህ ጥሪ !

አረጋዊው እና ቄሱ መነኩሴዉ አባ ገብረ መስቀል በግፍ ተገደሉ!

የድርጊቱ ዝርዝር ቀን እና ሰዓት፦ ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓ.ም (ከጠዋቱ 5:00 አካባቢ)

ቦታ፦ ከደብር ቆይታቸው ወደ ከተማው በመመለስ ላይ እያሉ (ሳንጃ ከተማ፣ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ በር ላይ ፊታቸዉን በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ተመተዉ ሂወታቸዉ አልፏል)

​ሟች፦ አባ ገብረ መስቀል (ቄስ እና መነኩሴ)
​ዕድሜ፦ 95 ዓመት (ትውልድ እና እድገታቸው በከንታ አቦ)

​አገልግሎት፦ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ታማኝ አገልጋይ

​እኒህ አባት የሰው እጅ ሳይጠብቁ በዕድሜያቸው መግፋት ምክንያት እጃቸው እየተንቀጠቀጠ፣ ዞረው ለምነው የሚበሉ፣ እንኳን በጥይት ሊመቱ ይቅርና ስድብ እንኳ የማይገባቸው እጅግ ምስኪን አረጋዊ መነኩሴ ነበሩ። በዛሬው ዕለት ግን በግፈኞች አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው አልፏል።

እኒህ አባት መነኩሴ ለኔ የስጋ ዝምድናም ምንም ነገር የላቸዉም እንዲሁ ከተማዉ ላይ እየዞሩ ለምነዉ ሲበሉ እና አንዳድ በጎ አድራጎት ሲኖር ነዉ ጥሪ የምናደርግላቸዉ ከዛ ዉጭ መፃሀፍ አብበዉ ለምነዉ ሚበሉ አባት መሆናቸዉን አዉቃለሁ ።

​በእውነት ምን አይነት ዘመን ላይ እንደደረስን የሚያስደምም እና ልብን የሚሰብር ለመስማትም ለማየትም እጅግ እጅግ የሚዘገንን አሳዛኝ ድርጊት በዛሬው ዕለት በሳንጃ ከተማ፣ ሚካኤል ቤተክሪስቷኑ ቅጥር ግቢ በር ላይ ተፈጽሟል ሲል Lij Solomon Abye ዝርዝሩን ገልጿል ።

በተለይ ወጣቱ ይሆነን ጉዳይ ፎቶዉን በማዉረድ በራሳቹሁ ድረ ገፅ በማስቀመጥ ለቀጣይ አስከፊ ለሚፈጠሩት ነገር በማዉገዝ የበኩላቹሁን እንድትወጡ ጥሪ ቀርቧል ።

ለሃይማኖት አባቶች፦ በየደብሩ፣ በየገበያው እና በሀዘን በደስታ ቦታወች እና በተለያዩ አደባባዮች በመገኘት እና አጋጣሚወችን በመጠቀም ይህንን መሰል አረመኔያዊ እና ሰይጣናዊ ድርጊት በግልጽ እንድታወግዙልን፤

ለእናቶች እና ለአባቶች የገዛ ልጆቻቹሁን እንዲመክር፣ እንዲገሥጽ እና ወደ ትክክለኛው መንገድ እንድትመልሱልን፤

​ለመንግሥት አካላት እና ለአካባቢዉ ማህበረሰብ፦ ለዚህ አሰቃቂ ወንጀል ተጠያቂ የሆኑ አካላት ለፍትህ እንዲቀርቡና ተገቢውን ፍርድ እንዲያገኙ፤

​ለእያንዳንዱ የሀገሬ ሰው፦ ይህንን መልእክት በየገጻችሁ በማጋራት (Share በማድረግ) ድምፅ እንድትሆኑ እና ድርጊቱን በጋራ እንድናወግዝ ጥሪ እናስተላልፋለን።

27/07/2026

ከ13ኛ ፎቅ ላይ የወደቀ 37 ኪ.ግ ከባድ ቁስ የብሩሁ ተማሪ አቤልን ሕይወት በአንድ ቅጽበት ቀየረው!

ከታች የምትመለከቱት ልጅ አቤል መለሠ ይበላል። ​በት/ት ደረጃው ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ Matric ፈተናውን ለመውሰድ ከፍተኛ ሁኔታ በመዘጋጀት ትምህርቱን እየተከታተለ ነበረ።

ታኅሣሥ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከ ት/ቤት ወደ ቤት ለመመለስ ትራንስፖርት ለመያዝ በእግረኛ መንገድ ላይ ሲሄድ ፒያሳ ሀገር አቀፍ ቲያትር አካባቢ በመገንባት ላይ ያለ ህንፃ ከ13ኛ ፎቅ ላይ የወደቀ ከባድ 37 ኪ.ግ የሚመዝን ሙሉ ጭንቅላቱ ላይ በመውደቅ የራስ ቅሉ (Skull) ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ራሱን ስቶ ወድቋል።

​በኋላም በቤተሰብ እና በህንፃ ስራ ተቋራጩ ርብርብ ወደ ላንሴት ጠቅላይ ሆስፒታል ተወስዶ የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ከተደረገለት በኋላ ለ7 ወር ያህል በአደጋው ምክንያት በደረሰበት ከፍተኛ ህመምና ጉዳት እስካሁን ድረስ ራሱን ስቶ በአልጋ ላይ ይገኛል።

​አደጋውን ያደረሰበት ተቋራጭም ከመጋቢት 5, 2018 ቀን ጀምሮ የሕክምናውን ወጪ ያቋረጠ በመሆኑ ለረጅም ወራት ቤተሰቦቹ በሕክምና ወጪ ጫና ውስጥ ቤት ለማከም ተገደዋል።

​ይሁን እንጂ ተጨማሪ የማከም አቅም የሌላቸው ስለሆነ ከዚህ በታች በተጠቀሰው በወላጅ እናቱ እታለማሁ አሰፋው ወ/መድኅን አካውንት አቤል መለስን ሕይወት ታደጉን ጤናው ተመልሶ ...

​እንደጓደኞቹ ቀና ብሎ እንዲሄድ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን።

​የባንክ ሒሳብ ቁጥር : እታለማሁ አሰፋው ወ/መድኅን

​CBE: 1000348860538

​📞 0911398024 / 0931534451

እባካችሁን ይህን መረጃ SHARE (ሼር) በማድረግ ለብዙዎች እንዲደርስ እና የአቤልን ሕይወት ለመታደግ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ አድርጉ! የእርስዎ አንድ ሼር የሰው ሕይወት ሊታደግ ይችላል።

Via ቤተሰብ

ጉርሻ page

🌴🌴🌴

25/07/2026

Watch, follow, and discover more trending content.

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Helena Love posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share