Yefeker hager

Yefeker  hager Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yefeker hager, Business service, Addis Abeba, Addis Ababa.

 #በሴት የሰራዊት አባላት የታየው ጀግንነት እና ቆራጥነት ወጣት ሴት የፖሊስ ኦፊሰሮችን ወደ ፌደራል ፖሊስ እንዲቀላቀሉ ግንዛቤ ፈጥሯል ።የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብ...
08/03/2023

#በሴት የሰራዊት አባላት የታየው ጀግንነት እና ቆራጥነት ወጣት ሴት የፖሊስ ኦፊሰሮችን ወደ ፌደራል ፖሊስ እንዲቀላቀሉ ግንዛቤ ፈጥሯል ።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን አስመልክቶ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ለሴት አባላቱ እውቅና ሰጥቷል።
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ÷ሴት የኮሚሽኑ አባላት ለሀገር በታማኝነት እና ጀግንነት መቆምን በተለያዩ ግዳጆች በተግባር አስመስክረዋል ብለዋል፡፡

ይህ ጀግንነትና ቆራጥነትም በሌሎች የተቋሙ የስራ ዘርፎች እንዲተገበር ነው ኮሚሽነሩ የጠየቁት፡፡
በመርሐ ግብሩ በተለያዩ ግዳጆች የሀገራቸውን ህልውና በማስጠበቅ ስራ ጉዳት ለደረሰባቸው አባላት የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ከዚህ በፊት የፖሊስ ሆስፒታል 60ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ የተሸለሙት የአንገት ሃብል በግዳጅ ወቅት ለቆሰለች ሴት የሰራዊት አባል አበርክተዋል።

 #ኢትዮጵያን ለማሳነስና ኢትዮጵያዊነትን ለማኮሰስ ሌት ተቀን ሴራ የሚጎነጉኑ አካላት፤ ዐድዋ ያጋመደንን ማንነት ሊበጥሱ እንደተሳሉ ምላጮች አስበን በጋራ እንታገላቸዋለን።ጠቅላይ ሚኒስትር አብ...
01/03/2023

#ኢትዮጵያን ለማሳነስና ኢትዮጵያዊነትን ለማኮሰስ ሌት ተቀን ሴራ የሚጎነጉኑ አካላት፤ ዐድዋ ያጋመደንን ማንነት ሊበጥሱ እንደተሳሉ ምላጮች አስበን በጋራ እንታገላቸዋለን።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

💧“ኢትዮጵያን እናፈርሳለን፤ ኢትዮጵየን ለማፍረስም ሲኦል ደረስ እንወርዳለን” ያሉትን ጥቂት ነፍጥ አምላኪ ጠመንጃ ነካሾችን ወደ ተመኙት ሲኦል አውርዶ ኢትዮጵያን ከማፈራረስ እና ከብተና  የታ...
28/02/2023

💧“ኢትዮጵያን እናፈርሳለን፤ ኢትዮጵየን ለማፍረስም ሲኦል ደረስ እንወርዳለን” ያሉትን ጥቂት ነፍጥ አምላኪ ጠመንጃ ነካሾችን ወደ ተመኙት ሲኦል አውርዶ ኢትዮጵያን ከማፈራረስ እና ከብተና የታደገ ዘመኑን የተረዳ ዘመናዊ መሪ ነው። የጠ/ሚር አብይ የፖለቲካ አካሄድ ስግብግብነትን እና ራስ ወዳድነትን በክፉኛ የሚፀየፍ፣ የሆዳሞችን ያግበሰበሱትን ለምስኪኖች ማከፋፈል ነው። እንዲህ አይነት አስተሳሰብን በውስጥህ መፍጠር የምትችለው ደሞ የራስህ ጥቅምና እና ዝና ወደ ጎን ትተህ ራስህን ለሀገር እና ለምትወደው ህዝብ አሳልፈህ ስትሰጥ ብቻ እና ብቻ ነው።

 !!           የመደመር እሳቤ በሀገር ግንባታ ሂደት ሁሉም ተዋኒያን የማይተካ ሚና እንዳላቸው ይገነዘባል። በመሆኑም  ሰብዓዊ ፣ ቁሳዊ፣ መንፈሳዊና ሌሎችም አቅሞችና እሴቶች ተሰባስበው...
27/02/2023

!!
የመደመር እሳቤ በሀገር ግንባታ ሂደት ሁሉም ተዋኒያን የማይተካ ሚና እንዳላቸው ይገነዘባል። በመሆኑም ሰብዓዊ ፣ ቁሳዊ፣ መንፈሳዊና ሌሎችም አቅሞችና እሴቶች ተሰባስበውና ተደምረዉ በሀገር ግንባታዉ ሂደትጉልህ ሚና እንዲጫወቱ በመሥራት አስፈላጊነት ላይ ያተኩራል። ኃይልን የመሰብሰብ የማከማቸትና የማደርጀት አቅጣጫን ይከተላል መደመር። የመደመር መንገድ አካታች ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ፍሬ እንዲያፈራ መሠረት የሚሆን ነዉ። ከልዩነቶቻችን ይልቅ የሚያስተሳስሩን እዉነታዎች ሚዛን ይደፋሉና ለምክክር ቅድሚያ መስጠት አስፈላጊ ነዉ።

💧ለአፍሪካ ነጻነት የተጉ የድሮ እና ያሁኑ ጀግኖችበ1880ዎቹ እና 1890ዎቹ ከኢትዮጵያ ውጭ አፍሪካን ሀገራት በቀኝ ግዛት (በኮሎኒያሊዝም) ተይዟል። ኢትዮጵያ ላይ ግን በጀግኖቿ መራር ትግል...
25/02/2023

💧ለአፍሪካ ነጻነት የተጉ የድሮ እና ያሁኑ ጀግኖች
በ1880ዎቹ እና 1890ዎቹ ከኢትዮጵያ ውጭ አፍሪካን ሀገራት በቀኝ ግዛት (በኮሎኒያሊዝም) ተይዟል።
ኢትዮጵያ ላይ ግን በጀግኖቿ መራር ትግል እና መስእዋትነት ኢትዮጵያ ላይ የባሪያ ስርዓት ለማንገስ የመጣው ጠላት ህፍረት ተከናንቧል። የነጮች የበላይነት አመለካከት ፈራርሷል። ጥቁሮች ለነጻነታቸው መዋጋት እንደሚችሉ ወኔ አግኝቷል።
ባሁኑ ግዜ ቀኝ ግዛት (ኮሎኒያሊዝም) ወደ ኒኦ ኤምፔሪያሊዝም ተቀይሯል። አፍሪካን በአካል ሳይገዙ ከሩቁ መበዝበዝ እና መጮቆን ማለት ነው። ይሄንን አደገኛ የጭቆና እና የብዝበዛ ስርዓት ከአፍሪካ በሁሉም ዘርፍ ለመናድ በጥንካሬ እየሠሩ ከሉት ውስጥ ግምባር ቀደሙ ክቡር ጠ/ሚር አብይ ናቸው።

  መለስ ብሎ የቃኘ፣  በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ ያለፈች ሃገር መሆኑን ይረዳል። ኢትዮጵያ ‘ያጠፋታል’ የተባለ በርካታ ጠንካራ ፈተናዎች የገጠማት ቢሆንም፣ አንዴም በፈተና አልተረታችም። ኢትዮ...
24/02/2023

መለስ ብሎ የቃኘ፣ በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ ያለፈች ሃገር መሆኑን ይረዳል። ኢትዮጵያ ‘ያጠፋታል’ የተባለ በርካታ ጠንካራ ፈተናዎች የገጠማት ቢሆንም፣ አንዴም በፈተና አልተረታችም። ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትንም ፈተና ለታሪክ ትታ ተሻግራ የበለጸገች ታላቅ ሃገር ተሆናለች!

 #ለኢትዮጵያ _ከፍታ_ድርሻችንን_እንወጣ!!!      ኢትዮጵያ ሠላሟን በመጠበቅ ፀጋዎቿን በማልማት የዉስጥና የዉጭ ፈተናዎቿን በመመከት ኢትዮጵያን ወደከፍታ ማማ እንድትወጣ የበኩላችንን ድርሻ...
21/02/2023

#ለኢትዮጵያ _ከፍታ_ድርሻችንን_እንወጣ!!!
ኢትዮጵያ ሠላሟን በመጠበቅ ፀጋዎቿን በማልማት የዉስጥና የዉጭ ፈተናዎቿን በመመከት ኢትዮጵያን ወደከፍታ ማማ እንድትወጣ የበኩላችንን ድርሻ የማበርከት ኃላፊነት የሁላችንም ነዉ።ኢትዮጵያን ከፍ የሚያደርጋት የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጥረትና ትጋት ነዉና ለኢትዮጵያ መፃኢ ዕጣፈንታ ማማር ሁሉም የየበኩሉን ማበርከት ይጠበቅበታል ።

💦ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ሃላፊነት መጥተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ ወደ አገልግሎት የገባው የአዲስ አበባ ፈርጥ የሆነው የአንድነት ፓርክ የአፍሪካ ህብረት 36ኛ የመሪዎች ጉባኤ እንግዶ...
20/02/2023

💦ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ሃላፊነት መጥተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ ወደ አገልግሎት የገባው የአዲስ አበባ ፈርጥ የሆነው የአንድነት ፓርክ የአፍሪካ ህብረት 36ኛ የመሪዎች ጉባኤ እንግዶች እራት ተጋብዘውበት ደምቀውበታል።

💧"አንድ ሰው በደሉን በሁለት መንገድ ሊሽር ይችላል። አንድም በይቅርታ፤ አልያም በፍትሕ ወይም በበቀል። እኛ በይቅርታ በደሎቻችንን ረስተን በመደመር ፣ በወንድማማችነት፣ በፍቅር፤ በይቅርታ እ...
18/02/2023

💧"አንድ ሰው በደሉን በሁለት መንገድ ሊሽር ይችላል። አንድም በይቅርታ፤ አልያም በፍትሕ ወይም በበቀል። እኛ በይቅርታ በደሎቻችንን ረስተን በመደመር ፣ በወንድማማችነት፣ በፍቅር፤ በይቅርታ እንሻገር፤ ያለፈውን በደል እንተው ይቅር አልን። ያለውን በደል ካነሣን እግሩ የተቆረጠ ጥፍሩ የተነቀ አባት እናቱን ያጣ አh። በመንግሥት ምሬት ተሰድደው በየባሕሩ የቀሩ ሰዎች አሉ። ይህ ሁሉ በደለኛ በየአካባቢው እያለ የበቀል እርምጃ ከወሰደ መተላለቅ ስለሚያመጣ በደሉን አፍነን ዕርቅ፣ ሰላም፣ ፍቅር እንዲኖር ብንሰራ ይሻላል።"
🇪🇹ጠቅላዩ

  ሰው ነው ስንል በምክንያት ነው‼️ለሀገሪቱ ሰላም ሊከፈል የሚችል ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል የግድ እንደ አብይ አህመድ አይነት ረቀቅ ያለ አዕምሮ ያስፈልጋል! የሚሆነውን ያውቃል መሆ...
16/02/2023

ሰው ነው ስንል በምክንያት ነው‼️

ለሀገሪቱ ሰላም ሊከፈል የሚችል ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል የግድ እንደ አብይ አህመድ አይነት ረቀቅ ያለ አዕምሮ ያስፈልጋል! የሚሆነውን ያውቃል መሆን ያለበትንም ጊዜ ያውቃል ሰላም ለአንድ ሀገር ወሳኝ ነገር እንደመሆኑ ለሰላም ማንኛውንም መስዋዕትነት ይከፍላል። ሀገር ትቀጥላለች🙏

💧ዲፕሎማሲ እና የሀገር ክብር ከፍታ መልክ ቢኖረዉ ከነ ሞገሱ አባመላን ነበር የሚገልጸው !!   እና የአህጉሪቱን ዜጎች ከረሃብና ድንቁርና ከጦርነት እና ስደት የማላቀቅ፣ አፍሪካን የጥይት ድ...
14/02/2023

💧ዲፕሎማሲ እና የሀገር ክብር ከፍታ መልክ ቢኖረዉ ከነ ሞገሱ አባመላን ነበር የሚገልጸው !!

እና የአህጉሪቱን ዜጎች ከረሃብና ድንቁርና ከጦርነት እና ስደት የማላቀቅ፣ አፍሪካን የጥይት ድምጽ የማይሰማባት አህጉር የማድረግ ተልእኮን ይዞ እየሰራ የሚገኘው መሪያችን👊

አፍሪካ ላለፉት አስርት አመታት ነቅታ፣ ጥንካሬዋን አውቃ ብዙ ስኬቶችን ብታስመዘግም አሁንም ተቆጥረው የማያልቁ ችግሮችና ፈተናዎች አሉባት። ምንም እንኳ አፍሪካ ሙሉ በሙሉ ከአውሮፓዊያን የቅኝ ግዛት ነፃ ቢወጡም የአፍሪካ ነፃነት እና አንድነት ሙሉ በሙሉ ሆነ የምንለው ዜጎቿ ሙሉ በሙሉ በሰላምና በነፃነት ሲኖሩ፣ ሁሉም አፍሪካዊ ትምህርት ሲያገኝ፣ የአካል እና የአዕምሮ ጤንነት ሲያገኝ፣ የስራ እድል ሲፈጠርለት፣ ማህበራዊ እሴቱ ሲለማና ዲሞክራሲያዊ ስርአት ሲገነባ ነው።
እነዚህ መሰረታዊ ጉዳዮች እስከሚሟሉ ድረስ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሁሉም አፍሪካዊ ተግቶ መስራት አለባቸው።

💧“ግሪን ሌጋሲ ስንል፣ ህዳሴን እንጨርሳለን ስንል፣ ፕሮጀክቶችን ጀምረን እንጨርሳለን ስንል ከነበረው ፈተና በላይ ‘ኢትዮጵያ ካሁን በኋላ ስንዴ ከውጭ አታስገባም’ የሚለው ራዕይ ለብዙዎች በቀ...
13/02/2023

💧“ግሪን ሌጋሲ ስንል፣ ህዳሴን እንጨርሳለን ስንል፣ ፕሮጀክቶችን ጀምረን እንጨርሳለን ስንል ከነበረው ፈተና በላይ ‘ኢትዮጵያ ካሁን በኋላ ስንዴ ከውጭ አታስገባም’ የሚለው ራዕይ ለብዙዎች በቀላሉ የሚቀበሉት እና የሚዋጥላቸው አልነበረም። ኢትዮጵያ ከልመና ወጥታ፣ ገዝታ አስገብታ ከመብላት ወጥታ፣ አርሳ ራስዋን አብልታ፣ ከዚያም አልፋ ኤክስፖርት ማድረግ ትችላለች ወይ’ የሚለው በህዝባችን ብቻ ሳይሆን በርካታ አመራሮችም ይህን ሃሳብ ተጋርተው ለመስራት ተቸግረው ነበር።”

ጠ/ሚር አብይ አህመድ በስንዴ ኤክስፖርት ማስጀመሪያ ላይ

Address

Addis Abeba
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yefeker hager posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share