04/06/2026
ኮሌጁ ለሠላም ማስከበር ማዕከል ከፍተኛ መኮንኖች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ ለሰላም ማስከበር ማዕከል ከፍተኛ መኮንኖች በተንቀሳቃሽ የትምህርት መርሃ-ግብር ሲሰጥ የቆየውን የአመራር ስልጠና አጠናቋል።
በስልጠናው ተለዋዋጭ የሆነው የአለም ፖለቲካ በአፍሪካ ቀንድ ያለው ቀጠናዊ ሁኔታ ኢትዮጵያ ሃገራችን ከጎረቤት ሃገራት የምትጠብቀውና የሚጠበቅባትን መረዳት የሚችል አመራር እየተፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።
የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል ሃላፊ ሜጄር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ በሚያስችል መልኩ በስትራቴጂክ ደረጃ ትምህርት በመስጠት በቴክኖሎጂና በኢኮኖሚ የበለፀገች ሀገር ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እየተሰራና ዘመናዊ ሠራዊት እየተገነባ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ኮሌጅ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ጥላሁን ደምሴ በበኩላቸው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ለበርካታ ሀገራት አገልግሎት እየሠጠች መምጣቷን ገልፀው የከፈለችውን ዋጋ ምላሽ መስጠት በሚያስችል ደረጃ ተጠቃሚ እየሆነች አይደለም ብለዋል።
ለዚህም የወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ አቅም ለማጠናከር በስልጠና የታገዘ አመራር መፍጠር ያስፈልጋል ሲሉ አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ አሰፉ ግርማይ
ፎቶግራፍ ኢፍቱ ቢራቱ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official