ACT PLC: Coaching & Consulting

ACT PLC: Coaching & Consulting Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ACT PLC: Coaching & Consulting, Consulting Agency, Addis Ababa.

✨ Act with Purpose!
🧠 Personal Development | Soft Skills | Leadership
📈 Sales & Marketing Excellence
🎓 CPD Certified Coaches & Trainers
​Work with us:
📲 +251 964 21 77 77
📲 +251 964 21 88 88

12/04/2026
 #እምቢ በላቸው❗️💥አልጋ በአልጋ የሆነ ስኬት የለም። ካለም  ጤነኛ  ስኬት አይደለም።  ስለሆነም ስኬትህ ከመውጣትም ፣ከመውረድም፣ ከመደሰትም፣ ከመከፋትም ፣ከመውደቅም ከመነሳትም፣ከማግኘትም...
10/06/2025

#እምቢ በላቸው❗️
💥
አልጋ በአልጋ የሆነ ስኬት የለም። ካለም ጤነኛ ስኬት አይደለም። ስለሆነም ስኬትህ ከመውጣትም ፣ከመውረድም፣ ከመደሰትም፣ ከመከፋትም ፣ከመውደቅም ከመነሳትም፣ከማግኘትም ከማጣትም ፣... ሁኔታዎች በኋላ ነው።
💥
ከዚህም ያለፈ እልህ አስጨራሽ መሰናክሎች ሊገጥሙህ ይችላሉ። ይህ ሁሉ ፊልም መሰል ክስተት አንተ ላይ ሲፈራረቅ በጣም ጥቂቶች ከጎንህ ሆነው ያበረታቱሃል፣ብዙዎች ይርቁሃል፣አንዳንዶች ያሾፉብሃል፣ሌሎች ያሙሃል፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ጭራሽ ችግር ይጨምሩብሃል።
💥
መካሪ መስለው 'አትችለውም እኮ ይከብድሃል'' ቢሉህም ዝም በላቸው፤ 'አይሳካልህም'' ካሉህም አትስማቸው ፤' መንገድ የለም' ቢሉህም መስሚያዬ ጥጥ ነው በላቸው።
💥
ስትነሳ ወዴት እንደምትሄድ አላማህን ካወክ በአንተ እና በስኬትህ መሀል ያለውን ርቀት ስለማታውቅ ዝም ብለህ ወደፊት ቀጥል። 'ያምሃል እንደ'' ካሉህም አዎ ! ከስኬቴ መንገድ ወደ ኋላ ከተመለስኩ ወይንም ከቆምኩ ያመኛል በላቸው።
🎯
የታየህን፣ ያለምከውን፣ የጀመርከውን ፣የምትሮጥለትን ፣ የምትደክምለትን እና እንቅልፍ የምታጣለትን አላማ ሊያስቱህ
ከሞከሩ ግን ግጥም አርገህ #እምቢ🙅‍♂️ በላቸው።
💥❤️
https://t.me/ACT_LIFE_COACHING_AND_CONSULTING

✍️ለደስተኛ ትዳር ዋናዎቹ 7 ምርጥ ምክሮች፡-❤️1. ከትዳር አጋርዎ ጋር ግልጽነት እና ሐቀኝነት የተሞላበት ውይይት ያድርጉ።❤️ግልጽነት፣ አክብሮት እና መደማመጥ  የተሞላበት የጥንዶች የሐሳ...
04/06/2025

✍️
ለደስተኛ ትዳር ዋናዎቹ 7 ምርጥ ምክሮች፡-
❤️
1. ከትዳር አጋርዎ ጋር ግልጽነት እና ሐቀኝነት የተሞላበት ውይይት ያድርጉ።
❤️
ግልጽነት፣ አክብሮት እና መደማመጥ የተሞላበት የጥንዶች የሐሳብ ልውውጥ አለመግባባትን ይከላከላል ፤ መተማመንን ይፈጥራል።

2. አድናቆት እና ምስጋና ማሳየት።
❤️
የሚናቅ ስጦታ የለም ይባላልና የትዳር አጋርን ቢያንስ በቋሚነት ማመስገን ።

3. ለትዳር አጋርዎ ፍቅር፣ክብር እና እንክብካቤ ይስጡ።
❤️
ፍቅር እና ክብር ለአጋርዎ የሚሰጡት ትልቁ ስጦታ መሆኑን ያስተውሉ።

4. ልዩነቶችን ያክብሩ።
❤️
የአመለካከት፣ የስብዕና ፣ የልምድ ፣ የሙያ እና ሌሎች ተፈጥሯዊ ልዩነቶችን መቀበል እና ማክበር።
አስታውሱ❗️
✅ የጋራ መከባበር የዘላቂ ግንኙነት መሰረት ነው።

5. ለግጭቶች/ለአለመግባባቶች ሳይውሉ ሳያድሩ መፍተሔ ይስጡ።
❤️
አለመግባባቶች የተለመዱ በመሆናቸው በመረጋጋት እና ነቀፋን በማስወገድ መፍትሄዎች ላይ ማተኮር።

6. የትዳር አጋርዎን እድገት/ለውጥ ይደግፉ።
❤️
የአጋርዎን ግቦች እና ህልሞች ያበረታቱ። ጤናማ ትዳር ሁለቱም ግለሰቦች እንዲያድጉ እና ለትዳሩ ብሎም ለቤተሰቡ ዘላቂ ህይወት ቅድሚያ ይሰጣል።

7. የጋራ ደስታ ፣ጨዋታ እና መዝናኛ ጊዜ ይስጡ።
❤️
ይህም ጠንካራ ዕምነት ፣ የአዕምሮ መታደስ ፣ውስጣዊ ሐሴት እና ልባዊ ትስስርን ይፈጥራል።
❤️ መልካም የትዳር ሕይወት!😄
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ❗️👇
https://t.me/ACT_LIFE_COACHING_AND_CONSULTING

🎯 አምስቱ ዋና ዋና የትኩረት ጥቅሞች፡- ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️1.ምርታማነት(ውጤታማነትን) ይጨምራል፦ትኩረት ማድረግ ሀሳብን የሚከፋፍሉ ነገሮችን በመቀነስ ተግባራትን በፍጥነት እና በብ...
03/06/2025

🎯 አምስቱ ዋና ዋና የትኩረት ጥቅሞች፡-
✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️
1.ምርታማነት(ውጤታማነትን) ይጨምራል፦
ትኩረት ማድረግ ሀሳብን የሚከፋፍሉ ነገሮችን በመቀነስ ተግባራትን በፍጥነት እና በብቃት ለማጠናቀቅ ይረዳል።
🎯
2.የተሻለ የስራ ጥራት፦ በትኩረት መስራት ስህተቶችን በመቀነስ ከፍተኛ ጥራት ያለው ውጤት ለማስመዝገብ ይረዳል። በተጨማሪም ትኩረት ተጨማሪ የፈጠራ እና ችግር የመፍታት ችሎታን ይጨምራል።
🎯
3.ከመጠን በላይ መጨናነቅ እና ውጥረትን ይከላከላል፦ ትኩረት *አንድ ጉዳይ* በአንድ ጊዜ እንዲፈቱ ያግዛል፣ ይህም የአዕምሮ መጨናነቅን ይቀንሳል።
🎯
4.የተሻለ የማወቅ እና የማስታወስ ችሎታ እንዲኖረን ያስችላል፦
ትኩረት መረጃን የመቅሰም እና ሳይረሱ የማቆየት ችሎታን ያጠናክራል። በማጥናት፣ በማንበብ ወይም አዲስ ክህሎት በመማር፣ ጥልቅ ግንዛቤን እንድናዳብር ያደርጋል።
🎯
5.ፈጣን የግብ ስኬት፦ ትኩረት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ተግባራት ከእቅዳችን ጋር እንዲጣጣሙ ያደርጋል።አስፈላጊ ባልሆኑ ስራዎች ላይ የሚባክን ጊዜን ይከላከላል።
🎯
https://t.me/ACT_LIFE_COACHING_AND_CONSULTING

Address

Addis Ababa
11724

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ACT PLC: Coaching & Consulting posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share