Joyful መረጃ

Joyful መረጃ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Joyful መረጃ, Business service, Addis Ababa.

22/06/2022

ድንቄም #ማውገዝ
ቆይ እኔ የገረመኝ #ማውገዝ የሚለው አማርኛ ሌላ ፍቺ ይኖረው ይሆን?????
መንግስት ቀድሞ ዜጎቹን ከጥቃት ከመከላከል ይልቅ የሰውን ሞት እየጠበቀ #ለማውገዝ የሚሽቀዳደም ይመስላል!!!!
#ማውገዝማ እኛም በአቅምቲ እያወገዝን ነው!!! አሁን ባለው የፖለቲካ አካሔድ ጥሩ #ካወገዝክ ለአመራርነት ትመረጣለህ ......... #ከማውገዝ ውጪ ምንም ያልፈየደ መንግስት!!

16/09/2021

በመዲናዋ የድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ውል ለተጨማሪ ሶስት ወራት ተራዘመ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶችን ውል ከመስከረም 4/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት እስከ ታህሳስ 3/2014 ዓ.ም ተራዝሟል፡፡

በመዲናዋ ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ወደስራ ከገቡ በኋላ በአማካይ 3 መቶ 92 አውቶቡሶች በየቀኑ አገልግሎት እንዲሰጡ በመደረጉ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ እንዲሻሻል አስተዋጽኦ አበርክቷል ሲል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል።

ይህም በቀን በአማካኝ ለ 182 ሺህ ተጠቃሚዎች አገልግሎት በመስጠት የተሳፋሪ የጊዜ ቆይታን በአማካይ ከ60 ደቂቃ ወደ 12 ደቂቃ ዝቅ እንዲል አስችሏል ነው ያለው፡፡

በሁሉም አውቶቡሶች GPS በመግጠም የክትትልና ቁጥጥር ስራው የተጠናከረ ሲሆን፥ አገልግሎት አሰጣጡም እየተሻሻለ መምጣቱንም ጠቅሷል።

ማህበራትም በውሉ መሰረት የተቀመጡ የአሰራር ስርዓቶችን ስራ ላይ በማዋል ከዚህ የተሻለ አገልግሎት እንዲኖር ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ቢሮው አሳስቧል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከጥቅምት 9/2013 ዓ.ም ጀምሮ ሀገር አቋራጭ አውቶቡሶች በኪራይ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉ ይታወሳል፡፡

11/08/2021

በአህያ ተጭኖ ለህወሓት ሊደርስ ነበር የተባለ ከ5 ሺህ በላይ ጥይት መያዙን ሀገር መከላከያ አሳወቀ።

የምዕራብ ዕዝ ደጀን ጥበቃ ፣ ሽብርተኛ ተብሎ ለተፈረጀው የህወሓት ቡድን ሊደርስ የነበረ ከአምስት ሺህ በላይ የክላሽ ጥይት በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ጥይቱ በሁለት (2) ቋጠሮ ተደርጎ በአህያ ተጭኖ ለህወሓት ሊደርስ ሲል ጫካ ውስጥ እንደተያዘ ተጠቁሟል፤ ጥይቱ ወደ ቡድኑ ቢደርስ የሚያስከትለው ጉዳት የከፋ ይሆን ነበር ተብሏል።

መረጃውን ይፋ ያደረገው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ ጥይቱ የተያዘበትን ቦታ / ጫካ አልተገለፀም።

የህወሓት ቡድን የሚያገኛቸውን ሎጀስቲካዊ ይሁን ሌሎች ድጋፎች ተከታትሎ በአልታሰበ ጊዜ በቁጥጥር ስር ማድረግ ቡድኑን የበለጠ ያዳክመዋል ያለው ሰራዊቱ ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት እስከ መጨረሻው ቡድኑን ለመደምሰስ ያልተቋረጠ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

Joyful መረጃ

11/08/2021

መረጃ

: የደሴ ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ለመጡ ወገኖቻችን ጊዜያዊ ማረፊያ ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

1ኛ. ቅዳሜ ገበያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የማረፊያ "ጣቢያ አንድ ":-
ከወልድያ እና ከጉባላፍቶ አካባቢ የመጡ ተፈናቃዮች ማረፊያ።

2ኛ.ዳዉዶ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የማረፊያ "ጣቢያ ሁለት":-
ከባላ፡ከራያ አላማጣ እና ከኮረም አካባቢ የመጡ ተፈናቃዮች ማረፊያ።

3ኛ. ካራጉቱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የማረፊያ "ጣቢያ ሶስት"
ከመርሳ እና ከሀብሩ ወረዳ አካባቢ የመጡ ተፈናቃዮች ማረፊያ።

4ኛ. አድስ ፋና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ማረፊያ "ጣቢያ አራት"
ቆቦ ከተማና ከራያ ቆቦ አካባቢ የመጡ ተፈናቃዮች ማረፊያ እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን በክፍለ ከተማና በቀበሌ ደረጃ መላ ህዝባችንና አመራራችን በጎፍቃደኛ ወጣቶቻችን አስፈላጉውን ትብብር ሁሉ እንደሚያደርጉላች በማመን ከላይ በተመለከቱት የማረፊያ ጣቢያዎች በመሄድ እንድትመዘገቡ ጥሪ ቀርባል።

ከወቅታዊ ጉዳዮቻችን ጋር በተያያዘ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ያለውን የተፈናቃይ ቁጥር በመገንዘብ ልዩ እገዛ ለማድረግ ከወዲሁ ፍቃደኝነታችሁን በመግለፅ ወደተግባር የገባችሁ የንግዱ መሀበረሰብ ከተማ አስተዳደሩ ምስጋናውን ለመግለፅ ይወዳል።

የደሴ ከተማ አስተዳደር

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Joyful መረጃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share