Ease of Doing Business and Development Service PLC

Ease of Doing Business and Development Service PLC Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ease of Doing Business and Development Service PLC, Consulting Agency, Addis Ababa.

13/03/2026
22/02/2026

82
#በአንድ ቀን፤ አንድ መልዕክት!

"ኑ እናገልግላችሁ!"
የላቀ አገልግሎታችንን አይታችሁ ለሌሎች ምስክር ሁኑ።

👉የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን የማህበራዊ ሚዲያ አድራሻዎች ከአስተያየት መስጫ ሳጥን ያገኛሉ፡፡
በደንበኞች ትምህርት ቡድን

22/02/2026

የዶላር የመሸጫ ዋጋ በ1.2 በመቶ ቅናሽ አሳየ፤ ብሔራዊ ባንክ ያቀረበው 500 ሚሊዮን ዶላር ሙሉ በሙሉ ገዢ አላገኘም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፣ የአንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ የመሸጫ ዋጋ ካለፈው ሳምንት የ1.21 በመቶ ቅናሽ በማሳየት 153.25 ብር መውረዱን አስታውቋል።

ባንኩ ለዚህ ልዩ ጨረታ እጅግ ከፍተኛ የሆነ 500 ሚሊዮን ዶላር ለገበያ ያቀረበ ቢሆንም፣ የንግድ ባንኮች የጠየቁት መጠን ግን ካቀረበው በታች ሆኖ ተመዝግቧል።

ይህም ባለፉት ሳምንታት በገበያው ላይ ይታይ የነበረውን ከፍተኛ የምንዛሬ ፍላጎትና የዋጋ ጭማሪ የገታ ክስተት ሆኗል።

ተጨማሪ ያንብቡ (https://capitalethiopia.com/2026/02/21/%e1%8b%a8%e1%8b%b6%e1%88%8b%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%88%b8%e1%8c%ab-%e1%8b%8b%e1%8c%8b-%e1%89%a01-2-%e1%89%a0%e1%88%98%e1%89%b6-%e1%89%85%e1%8a%93%e1%88%bd-%e1%8a%a0%e1%88%b3%e1%8b%a8%e1%8d%a4/)

22/02/2026
የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 842፡ አንድ ሰው ኑዛዜ ሳይተው ሲሞት፣ ንብረቱ ለልጆቹ (ለወራሾቹ) እኩል እንደሚከፋፈል የሚደነግግ መሠረታዊ ሕግ ነው።አዋጅ ቁጥር 1324/2016 (አዲሱ አዋጅ)፦...
21/01/2026

የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 842፡ አንድ ሰው ኑዛዜ ሳይተው ሲሞት፣ ንብረቱ ለልጆቹ (ለወራሾቹ) እኩል እንደሚከፋፈል የሚደነግግ መሠረታዊ ሕግ ነው።

አዋጅ ቁጥር 1324/2016 (አዲሱ አዋጅ)፦ ይህ አዋጅ የመሬት ባለቤትነት የመንግሥትና የሕዝብ ቢሆንም፣ "የመጠቀም መብት" ግን ልክ እንደ ማንኛውም ንብረት ሊወረስ እንደሚችል በግልጽ አስቀምጧል። በተለይ ወራሾች መሬቱን የማልማት ፍላጎትና አቅም ካላቸው፣ መሬቱ ሳይከፋፈል በጋራ ወይም በየተራ ሊጠቀሙበት የሚችሉበትን አሠራር ያበረታታል።

ይህ ፎርም ለክልል ፍርድ ቤት የሚቀርብ ከሆነ ክልሎች የራሳቸው የገጠር መሬት አዋጅ ስላላቸው የአዋጅ ቁጥሩን መቀየር ሊያስፈልግ ይችላል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 52ኛ መደበኛ ስብሰባ የግሉን ዘርፍ የሚመለከቱና ተያያዥነት ያላቸው፤▶️ የጉምሩክ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፤▶️ ለኢንቨ...
20/01/2026

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 52ኛ መደበኛ ስብሰባ የግሉን ዘርፍ የሚመለከቱና ተያያዥነት ያላቸው፤

▶️ የጉምሩክ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፤

▶️ ለኢንቨስትመንት ስለሚሰጥ የታክስና ቀረጥ ማበረታቻ ረቂቅ ደንብ

▶️ የኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ተወይይቶ ውሳኔ ሰጥቷል

(ለኢንቨስትመንት ስለሚሰጥ የታክስና ቀረጥ ማበረታቻ ረቂቅ ደንብ ምን ይዟል ? የመጀመሪያውን ረቂቅ ከላይ አያይዘናል)

ሌሎች የውሳኔዎች ዝርዝር
❇️❇️❇️❇️

1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የጉምሩክ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ በሥራ ላይ ያለው የጉምሩክ አዋጅ ለበርካታ ዓመታት ያገለገለ በመሆኑ፣ የአዋጁን ድንጋጌዎች ዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ ጋር ለማጣጣም፣ በአገራችን እያደገ የመጣውን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ለመደገፍ፣ እንዲሁም ሕጋዊ ንግድንና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ይቻል ዘንድ የማሻሻያ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በማሻሻያ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል አዋጁ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡

2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው ለኢንቨስትመንት ስለሚሰጥ የታክስና ቀረጥ ማበረታቻ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ለሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላላቸውና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው፣ እንዲሁም ከፍተኛ ካፒታል ለሚጠይቁ የኢንቨስትመንት መስኮች በሥራ ላይ የሚውለውን ካፒታል ከግምት ውስጥ የሚያስገባና በአፈጻጸም ላይ የተመሠረተ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል፣ ደንቡ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡

3. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ ፖሊሲው በኢንተርፕረነርሽፕ ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ቀጣይነት ኖሯቸው ለሀገራዊ የልማት ግቦች ስኬት ሚናቸውን እንዲወጡ፣ የፈጠራ ባህልን ለማጎልበትና እሴትን ለመጨመር የሚያስችል ምቹ የኢንተርፕረነርሽፕ ሥነ-ምህዳር ለመገንባት እንዲቻል ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል፣ ፖሊሲው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከጸደቀበት ከጥር 12 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡
❇️❇️❇️❇️❇️❇️
Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations
ስልክ፡ +251115514005
ፋክስ፡ + 251115517699
P. O. Box 517,
ኢ.ሜይል: [email protected]
ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com
ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber
X- https://x.com/EthiopiaChamber
ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber
Youtube:https://www.youtube.com/

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ease of Doing Business and Development Service PLC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share