23/03/2023
🔑🔑ተስፋ ማጣት(hopelessness) እና መፍትሔው🔑🔑
ሰሞኑን በተለቀቀው አመታዊዉ አለም አቀፍ የደስታ ሪፖርት በዓለም ዙሪያ ካሉ 150 በላይ አገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ ደስታ ከሌለባቸው ሀገራት 14ኛ ደረጃን ይዛ የተቀመጠች ሲሆን፤ ይህም ደረጃ በ6 መመዘኛዎች የተለየ ነው። አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ፣ ማህበራዊ ድጋፍ፣ ጤናማ የህይወት ዘመን፣ የራስን የህይወት ምርጫ የማድረግ ነፃነት፣ የአጠቃላይ ህዝብ ልግስና እና የውስጥ እና የውጭ ሙስና ደረጃዎች።
የግለሰብ ደስታን ጠቋሚ ከሆኑት ውስጥ ደግሞ ተስፋ ዋነኛው አመላካች ነው።
ተስፋ መቁረጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እርዳታ ማጣት፣ ከመጠን በላይ የመጨናነቅ እና የተፈጠረውን ሁኔታ መቋቋም አለመቻል ስሜት ተደራርበው የሚፈጥሩት ከባድ ስሜት ነው።
የሚወዱት ሰው ሞት፣ ፍቺ፣ ስራ ማጣት፣ የአእምሮ ጤና መታወክ እንደ ድብርት፣ ጭንቀት፣ ድህረ-አሰቃቂ ክስትት ጭንቀት (PTSD)፣ስር የሰደዱ ህመሞች፣ እና ብቸኝነትን በህይወት ማስተናገድ ወደ ተስፋ መቁረጥ ስሜት ሊወስዱን ከሚችሉት ምክንያቶች ውስጥ ናቸው።
በአንድ ወቅት ይወዱት የነበረን ነገር መጥላት፣ አሉታዊ አስተሳሰቦች፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ድካም፣ የእንቅልፍ ስረአት መዛባትን የመሳሰሉ ምልክቶችን ልናይ የምንችል ሲሆን።፤ የመንፈስ መረበሽ፣ ጭንቀት፣ እና ራስን የማጥፋት ሀሳቦችን ሊያስከትል ይችላል።
በዚ ሁኔታ ውስጥ ከሆንን ምን እናርግ?
🎖 እርዳታ ለመጠየቅ አይዘግዩ : ምን እንደሚሰማዎት ከታመነ ጓደኛ፣ የቤተሰብ አባል ወይም የአእምሮ ጤና ባለሙያ ጋር ይነጋገሩ።
🎖 እራስዎን ይንከባከቡ፡ በቂ እንቅልፍ እያገኙ፣ ጤናማ ምግብ እየተመገቡ እና በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግዎን ያረጋግጡ።
🎖 ለመኖር የሚያጓጓዎትን ዓላማ ይፈልጉ፡ እንደ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ፣ በጎ ፈቃደኝነት ወይም ሥራ ያሉ የዓላማ እና ትርጉም ስሜት የሚሰጥዎትን ነገር ፈልገው ይተግብሩ።
🎖 አሉታዊ ሀሳቦችን ከራስ ማራቅ፡ አሉታዊ ሀሳቦች ከአዎንታዊ ሀሳቦች ይልቅ ሰዎች ላይ 10 እጥፍ ተጽእኖ ያሳድራሉ። መልካም ያልሆኑ ሀሳቦችዎን ይሟገቷቸው እና የበለጠ አዎንታዊ በሆኑ ይተኩዋቸው።
🎖 ምስጋናን መለማመድ፡ ተስፋ ከምንቆርጥበት 1 ምክንያት በላይ ልናመሰግን የምንችልባቸው ከ 1000 ምክንያቶች ይኖሩናል። ስለዚህ የምናመሰግንባቸውን ነገሮች መዘርዘር እና በእነዚያ ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ።
🎖 እርምጃ ይውሰዱ: ከመተኛት መቆም፣ ከመቆም መራመድ፣ ከመራመድ ደግሞ መሮጥ ይሻላል ይባላል። ግቦችዎን ለማሳካት እና በህይወትዎ ውስጥ አወንታዊ ለውጦችን ለማድረግ ትናንሽ እርምጃዎችን መውሰድ ለራስዎት የሚሰጡትን ግምት ከፍ ስለሚያደርግ እጅዎን አጣጥፈው አይቀመጡ።
ለበለጠ መረጃ ይቀላቀሉን።