Adayro minerals and gemstones supplier plc

Adayro minerals and gemstones supplier plc Adayro Ethiopia supplies Gemstones i.e Opals,Quartzs,Axinite,Amethyst,Zircons,, Petrifiedwood,Jasper Minerals Copper,Sulfur,Bentonite,Rock salt e.t.c

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ስለ ኩርሙክ የወርቅ ፋብሪካ የተናገሩት…ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘውን የኩርሙክ ዘመናዊ የወርቅ ፋብሪካ የግንባ...
24/08/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ስለ ኩርሙክ የወርቅ ፋብሪካ የተናገሩት…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘውን የኩርሙክ ዘመናዊ የወርቅ ፋብሪካ የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጉብኝታቸው በኋላ ስለ ፋብሪካው የተናገሩት…

👉 በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ የወርቅ ፋብሪካ ይሆናል፤

👉 ከሚቀጥለው ዓመት አጋማሽ በኋላ ወደ ምርት እንደሚገባ ይጠበቃል፤

👉 በዚህ አካባቢ የሚመረተው ወርቅ በዓመት እስከ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ያስገኛል፤

👉 ከ20 ኪሎ ሜትር ራዲየስ በላይ ቦታ ይዟል፤

👉 ሦስት ግድቦች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚኖሩበት የመኖሪያ ካምፕ የያዘ ነው፤

👉 በዘርፉ ለኢትዮጵያ የእውቀት ሽግግር ያመጣ ፋብሪካ ነው፤

👉 ፋብሪካው የተገነባው ያለንን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም ባለን ፍላጎት መሰረት ነው፤

👉 በሁሉም ዘርፎች የተሟላ ልማት ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥል ስራ ነው፤ Via Ministry of Mines - Ethiopia

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 98 ሺህ ቶን የድንጋይ ከሰል ለማዕከላዊ ገበያ አቀረበበደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ባለፉት 9 ወራት 98 ሺህ ቶን የሚጠጋ የድንጋይ ከሰል ምርት ለ...
14/04/2025

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 98 ሺህ ቶን የድንጋይ ከሰል ለማዕከላዊ ገበያ አቀረበ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ባለፉት 9 ወራት 98 ሺህ ቶን የሚጠጋ የድንጋይ ከሰል ምርት ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገበረማርያም ሰጠኝ እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከውጭ ከምታስገባቸው ምርቶች መካከል የድንጋይ ከሰል አንዱ ሲሆን፤ በክልሉም በሰፊው ይገኛል።

ቀደም ሲል ሃብቱ ተገቢው ትኩረት ተነፍጎት በመቆየቱ ለአካባቢው እና ለሀገር ኢኮኖሚ የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ እንዳላበረከተ አስታውሰዋል።

ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከዘርፉ የሚፈለገውን ጥቅም ለማግኘት በተወሰዱ ርምጃዎችና ወደምርት ሥራ በመገባቱ የድንጋይ ከሰሉን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ መቻሉን ተናግረዋል።

በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት 200 ሺህ ቶን የድንጋይ ከሰል ለማዕከላዊ ከበያ ለማቅረብ ታቅዶ ባለፉት 9 ወራት 98 ሺህ ቶን የሚጠጋ የድንጋይ ከሰል ማቅረብ ተችሏል ብልዋል።

በዘርፉ ለመሰማራት ፍቃድ ከወሰዱ ከ20 በላይ ማህበራት መካከል በአሁኑ ወቅት ወደምርት የገቡት ስምንት ብቻ መሆናቸውንም ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

14/09/2022
30/08/2022

ይህንን ፎቶ ያነሳችው ነርስ እንዲህ ብላ ተናገረች፡-

እኚህ አዛውንት ታማሚ ሆስፒታል ከገቡ ሶስት ቀናት ቢቆጠርም ማንም ሊጠይቃቸው አልመጣም...!

ነገር ግን በመጀመሪያው እና በሁለተኛው ቀን አንዲት ርግብ ጎበኘቻቸው። በአልጋውም ላይ ለጥቂት ጊዜ ከጎናቸው ተቀመጠች..!

አዛውንቱ ብዙ ጊዜ ከሆስፒታሉ ጎን በሚገኝ መናፈሻ ወንበር ላይ ተቀምጠው ርግቧን ይመግቡ እንደነበር ታወቀ..!

በመካከላችሁ መልካምን ነገር አስፋፉ፤ መልካም ከዋላችሁለት አካል የምታገኙት ምንዳ ሳይሆን...
ይልቁንም እውነተኛው ምንዳ ፈጣሪ ለበጎ ሰዎች ሁሉ ከመልካም ነገሮች መልካሙን የሚከፍለው ነው..!

የብዙ ሰዎች ልብ ለታማኝነት እና ርህራሄ ምንም ቦታ ሳይኖረው እና እርስ በርስ ተነፋፍጎ ሳለ የርግብ ልብ የተሻለ ሆኖ መገኘቱ በጣም ያሳዝናል። ...!

አላህ ሀገራችንን እና ህዝባችንን ከችግር፣ ከመከራ እና ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቅልን። ግዜያችሁን ሁሉ በደስታና በሰላም ይባርክላችሁ።

يقال أن ‏الممرضة التي التقطت هذه الصورة ذكرت قائلة عنها :

لقد مرّت ثلاثة أيام منذ وصول هذا المريض المسنّ إلى المستشفى ، ولم يأت أحد لزيارته ..!

ولكن في اليوم الأول والثاني زارته حمامة وجلست إلى جانبه على السرير لفترة ..!

إتضح لاحقاً أن الرجل العجوز كان غالبا ما يجلس على مقعد في حديقة مقابل المستشفى ويطعم الحمامة ..!

إنثروا الخير بينكم ، فليس من الشرط أن تنالوا الجزاء ممن أحسنتم إليه ... وإنما الجزاء الحقيقي هو ما يجزي به الخالق من الخير كل الأخيار ..!

مؤسف ومحزن أن تضيق قلوب كثير من البشر على بعضها ولا تتسع لشيء من الوفاء والتراحم وتتسع لهما في المقابل قلبُ حمامة ...!

حفظ الله بلادنا وشعبنا من كل مكروه وسوء وفتنة وبلاء وأسعد الله أوقاتكم بكل خير وسعادة وسلام ،،،

‎ #اثيوبيا

‎ #ኢትዮጵያ

13/07/2022

Address

Addis Ababa

Telephone

+251925897040

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adayro minerals and gemstones supplier plc posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Adayro minerals and gemstones supplier plc:

Share