Green Time

Green Time Forgive is More Than Every Thing!!

አይቀርም ይነጋል
12/04/2023

አይቀርም ይነጋል

Watch, follow, and discover more trending content.

Brand           New sandisk     Flash Size            #32 GBPrice               500Phone +251930399323በራሳችን ትራንስፖርት ባሉበት...
28/05/2022

Brand New
sandisk Flash
Size #32 GB
Price 500
Phone +251930399323
በራሳችን ትራንስፖርት ባሉበት እናደርሳለን

28/05/2022

https://fias777.com/ #/pages/register?invite_code=lVFZVhjg&t=1653774929440

please join FIAS and upgrade your income!!

ስራዎችህ ሁሌም አዝናኝና አስተማሪ ነበሩ ነፍስህ በሠላም ትረፍ!!
20/05/2022

ስራዎችህ ሁሌም አዝናኝና አስተማሪ ነበሩ ነፍስህ በሠላም ትረፍ!!

18/03/2022

ኬንያዊው ሯጭ አቤል ሙታይ ለፍጻሜው መስመር ጥቂት ሜትሮች ብቻ ቢቀርም በምልክቶቹ ግራ በመጋባት ውድድሩን እንዳጠናቀቀ በማሰብ ቆመ። ኢቫን ፈርናንዴዝ የተባለ ስፔናዊ ሰው ከኋላው ሆኖ ምን እየተካሄደ እንዳለ ሲረዳ ኬንያዊው እንዲሮጥ ይጮህ ጀመር። ሙታይ ስፓኒሽ አያውቅም እና አልተረዳም። ኢቫን ፈርናንዴዝ ምን እየተካሄደ እንዳለ ስለተገነዘበ ሙታይን ወደ ድል ገፋው። አንድ ዘጋቢ ኢቫንን "ለምን ይህን አደረግክ?" ኢቫን መለሰ

የኔ ህልም አንድ ቀን ራሳችንን የምንገፋበት እና የምንረዳዳበት የማህበረሰብ ህይወት እንዲኖረን ማድረግ እንችላለን።” ዘጋቢው “ግን ለምን ኬንያዊውን እንዲያሸንፍ ፈቀድክለት?” ኢቫን መለሰ፡ “እንዲያሸንፍ አልፈቀድኩም። , ሊያሸንፍ ነበር. ውድድሩ የእሱ ነበር"

ጋዜጠኛው አጥብቆ ጠየቀ "እና ግን ማሸነፍ ትችል ነበር!" ኢቫን ተመልክቶ እንዲህ ሲል መለሰ: - "ግን የእኔ ድል ምን ጥቅም ይኖረዋል? የዚህ ሜዳሊያ ክብር ምን ይሆን? እናቴ ስለሱ ምን ታስባለች?"

ለልጆቻችን ምን አይነት እሴቶችን እናስተምራለን እና እናንተ አጠገባችሁ ላለ ሰዉ ተጠቃሚነት እድል መንገድ ከፍታችዋል ረድታችዋል ሌሎችን ታበረታታላችሁ? ብዙዎቻችን የሰዎችን ድክመቶች ለማጠናከር ከመርዳት ይልቅ እንጠቀማለን።

ከዚህ ታሪክ እንደምንማር ተስፋ አደርጋለሁ። ብዙ ጊዜ ሜዳሊያውን ማሸነፍ የመጨረሻው ዋጋ አይደለም.
ሰዉነት( ሰብአዊነት) አሸንፏል።

06/03/2022

#ከፍታህን #ጠብቅ!!
________=______

🇪🇹💚💛❤️ሀገርህን ትወዳለህ አይደል? መገለጫው ብዙ ነው ለምትወዳት ሀገር የምትሰጠው ያንተን ውዴታ ብቻ አይደለም፣ ...“የሚጠሏት” እንኳን ከገጠሙህ #ጨዋነትህን ትፈልጋለች፣ ማን ያውቃል ያንተ ስብዕና እነሱን የመቀየር አቅም ይኖረው ይሆናል

✍️✍️መሰልጠንን አንተ በምትረዳው ልክ ሰልጥን፣ በተቃራኒ ነው ያልከው ከገጠመህ አንተ የተሻለውን ማንነትህን ማሳየት ይኖርብሃል ...ማን ያውቃል አንድ ሰው ባንተ ስልጡን ማንነት ይለወጥ ይሆናል ....

🤔😓አይሰማህ፣ አትናደድ አትበሳጭ አልልህም፣ እኔ ስበሳጭ ብታየኝ የሚስቀው ነው ሌላ ነው ማለትህ አይቀርም 😊 ...ትልቁ ነጥብ ብስጭትህ ውስጥ ፍረጃ እንዳይኖር ማሰብ ነው፣ አንድን ጉዳይ በጉዳዩ ምንነት ብቻ መመዘኑ ነው፣፣ ...እና ደግሞ ብስጭት የልብ ጓደኛ ሆኖ እንዲኖር አለመፍቀድ ነው አይመስልህም? ...ማን ያውቃል ባንተ የብስጭት አገላለፅ ውስጥ የሆነ የምትለውጠው ሰው ይኖርሃል፣

😝😛ባለጌ ሆኖ ሲመጣብህ ጨዋ ሆነህ አስቀይመው!!! በስነስርዓት ማስተናገድ ያለብህ የሚወድህን አልያም የሚቀርብህን ብቻ አይደለም ፣ በተቃራኒው የሆነውንም በስብዕናህ መብለጥ አለብህ፣ ካልሆነ ጉዳዩ የመሽቀዳደም ብቻ ይሆናል፣፣ ...ባስ ካለ ሽሽት፣ርቀትን መጠበቅ ብሎም መሰል አማራጮች መጠቀም የተሻሉ ናቸው፣፣ ....ዘረኝነትን እየተፀየፍክ ሌላውን በዘሩ የምትፀየፍ ከሆነ ትርጉም የለውም!!!

🤝🤝ስብዕናችንን የሚመጣው የሚሄደው ሁሉ የሚወስነው ከሆነ የምንኖረው የራሳችንን ሳይሆን የሌሎችን ይሆናል ማለት ነው፣

🇪🇹🇪🇹ሀገር እንደሀገር እንድትቀጥል ፣ተቆራርሳ በተለያየ ስሜት እና ድባብ ውስጥ እንዳትገኝ ቆም ብሎ ማሰብ ሸጋ ነው፣፣ ...ሀገሪቷ ስላለች ነው በያለንበት አረፍ ብለን እየተሰዳደብን ያለነው፣ የከፋ ነገር ሲመጣ አይደለም ለመሰዳደብ የራስን ልብስ ዞር ብሎ ለማየት ፈጣሪን በተደጋጋሚ ማስጨነቅ እና መለመን ይመጣል!!!አይቶ መማር አልፈልግም ፣ አስቦ ከመራመድ እንጂ

#የትኛውንም ሰው ፣ማንኛውንም ክቡር ሰው፣ እሱ ይጠብቅልን!!!
_
ሌሎች እንዲሰጡን የምንመኘውን ከመስጠት እንጀምር፣ ማክበርን እና ጨዋነትን ...
………ለሀገርህ ደምህ ብቻ ሳይሆን ጨዋነትህም ያስፈልጋታል!!!!

#ከፍ ካልክ ሰው ሁን፣ ዝቅ ካልክ ጨካኝ አትሁን፣ ከዚህ በታች ግን አትውረድ!!

#መልካም ሰምበት!!!!

እስቲ የእስካሁኑ ይብቃንና እንዲህ ይመርብን
29/12/2021

እስቲ የእስካሁኑ ይብቃንና እንዲህ ይመርብን

ወፍ ዘራሽ አይደለሁም! ወፍ ዘራሽ አይደለሁም! የበቀልኩበትን፣ ያጌጥኩበትን፤ ደግሞም ያሸበረቅኩበትን አውቃለው።በራሱ ቀለም ነክሮ የገዛ ቀለሙን ያዋሰኝን አሳምሬ አውቃለው። ዛሬ ደረሶ ፊደል ...
09/12/2021

ወፍ ዘራሽ አይደለሁም!

ወፍ ዘራሽ አይደለሁም! የበቀልኩበትን፣ ያጌጥኩበትን፤ ደግሞም ያሸበረቅኩበትን አውቃለው።በራሱ ቀለም ነክሮ የገዛ ቀለሙን ያዋሰኝን አሳምሬ አውቃለው። ዛሬ ደረሶ ፊደል ብቆጥር፤ ባህር ተሻግሬ፣ አድማስ አሳብሬ የጎረቤት አደራረግን ብቀስም የእውቀት ቀንዲል አያደርገኝም።

ከኖረበት ምድር ጥበብ የተዋሰ፤ ከሰንበተበት መስክ ማስተዋል የቀዳ፤ ከፈለቀበት ሸንተረር ወግ እና ልማድ ያዋደደ፤ ከጠጣው ኩሬ የኑባሬን ጠሊቅ ሚስጢር የቀመረ፤እትብቱን ከቀበረበት አፈር ብሂል ያዋለደ፤ ካደመጠው የንጋት ዜማ ኪነት ያበለጸገ፤ እውነቱን፣ ገድሉን፣ ሰቀቀኑን፣ ናፍቆቱን በልሳን የከተበ ፤በዜማ የሰደረ ህዝብ ነው ያፈለቀኝ። እርሻን ከሚያውቅ ገበሬ፣ ከብትን ከሚያውቅ እረኛ፣ ሰብራት ከሚጠግን ወጌሻ፣ ቅጥል ከሚጨፈልቅ ቀማሚ ነው ልደቴ። እድገት መሰረቴ። አፈርን ከሚያውቅ ሸክላ ሰሪ፣በገናን ከሚቃኝ ባለ ቅኔ፣ ህልምን ከሚፈታ አዋቂ ነው ስሪቴ። የህይወት ትምህርቴ።

ያበቀለኝ ህዝብ ፍጹም ባይሆንም በሁሉ የነሆለለም አይደለም። እክል እና ግድፈት ባያጣውም ከእውቀት ተፋቶ ጨለማ ብቻ የተጣባውም አይደለም።እጅና ጉልበት ስሞ፣እግር አጥቦ ሰውነትን ያስተማረኝ ይኽ ህዝብ ነው። ፊደሉን፣ ዜማውን፣ ፈሊጡን፣ ብሂሉን ላዋሰኝ፤ ሰው አድርጎ ለሰራኝ ህዝብ የእድሜ ዘመን ባለእዳ ነኝ። ወፍ ዘራሽ አይደለሁማ!!!

💚💛❤️ አንዳንዱ ሃገር በገንዘብ ስቀይር ሌላው ቁጭ ብሎ ስለ ነገ ሴራውን ያሴራል ያውም አሉን ብለን የምንመካባቸው::  ስለ እነዚህ ምርጦች ምስክሮች እኛ መሆን ስገባን ከእኛ ውጭ ያለው ይመ...
26/11/2021

💚💛❤️ አንዳንዱ ሃገር በገንዘብ ስቀይር ሌላው ቁጭ ብሎ ስለ ነገ ሴራውን ያሴራል ያውም አሉን ብለን የምንመካባቸው:: ስለ እነዚህ ምርጦች ምስክሮች እኛ መሆን ስገባን ከእኛ ውጭ ያለው ይመለከታል ብቻ ግራም ነፈሰ ቀኝ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ምሳሌ ናት።💚💛❤

Address

Addis Ababa

Telephone

+251930399323

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Green Time posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Green Time:

Share