Lij Mogese daily news

Lij Mogese daily news this page is info of think thank

18/10/2024

🔥🔥🔥🔥ታላቅ ዜና🔥🔥🔥🔥

Mogese Assignment Solutions
ጥራት ያለው እገዛ በሁለም የትምህርት ዘርፍ

🎓በትምህርቶ አስተማማኝ የሆነ እረዳት ይፈልጋሉ ፤ Mogese Assignment Solutions አለልዎት

🎓አላማችን ተማሪዎችን በሁሉም መስፈርት በፈለጉት መንገድ አስተማማኝ የሆነ እገዛ ማድረግ ነዉ🎓

📝ለዲግሪም ሆነ ለማስተርስ ተማሪዎች የምንሰጣቸው አገልግሎቶ📝

RESEARCH
🎓Title selection
🎓Proposal
🎓Literature review
🎓Research BA/BSc
🎓Thesis MA/MSc
🎓Research editing
🎓Research comment correction

ASSIGNMENT
📚 Article , Books & Chapter review 📚
📝Business Plan
📝Books in pdf
📄Case Study
📝Internship report & Practical Attachment
📝practice & exam questions
📝Project Work
📝Presentations Power point & Short note preparation
📝Term Paper and essays in any subject

Assignment Solutions:
- 🔄 Offers revisions until you are fully satisfied
- ✅ Guarantees 0% plagiarism(Chat gpt free)
- ⏰ Meets all deadlines

Get the Help You Need for Academic Success

🏦📝ለሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ቅናሽ አለን፨

Contact us:

✉️ [email protected]
📞 0965458645
Mogese Assignment solutions 📚

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምለአንድ ምእት አስር የቀረውን ረጅም ፍሬያማና ጠመዝማዛ የሕይወት ጉዞ አጠናቀው: ሊፋቅና ሊረሳ የማይችል ትሩፋታችውን በኢትዮጵያ የታሪክ ማህደር አስፍረው ተሻገሩ!...
30/09/2020

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
ለአንድ ምእት አስር የቀረውን ረጅም ፍሬያማና ጠመዝማዛ የሕይወት ጉዞ አጠናቀው: ሊፋቅና ሊረሳ የማይችል ትሩፋታችውን በኢትዮጵያ የታሪክ ማህደር አስፍረው ተሻገሩ!
ለቤተሰብ መፅናናት ይሁን!

28/09/2020

"አገሬን ፋና ላምሮት ላይ አየኋት፤ ፈራኋትም!"
(በዶክተር በድሉ ዋቅጅራ)
ለወትሮው ሪሞት ጥሎኝ ካልሆነ የፋና ላምሮትን የድምጻውያን ውድድር አልከታተል፡፡ ትላንት መጨረሻውን አየሁት፡፡ ውጤቱ ከታወቀ ጀምሮ የተወዳዳሪዎቹ አካባቢ ሰዎች በተለመደው መንገድ ጎጥ ለይተው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ውጊያ ገጥመዋል፡፡ አንዳንዶቹም ለሰፈራቸው ተወዳዳሪዎች የሽልማቱን ያህል ገንዘብ አዋጥተን እንሰጣለን እያሉ ነው፡፡ ይህ አይደንቅም፣ ቅኝታችን ሁሉ የጎጥ ነው፡፡ በጎጥ ሰው በሚገደልበት ሀገር በጎጥ መሸለም ከጽድቅ ይቆጠራል፡፡ ሰዎች ስለዚህ ነገር ሲያወሩ ያሳዝነኛል፡፡
ትልቁ ልናወራበት፣ ልናወግዘው የሚገባው ጉዳይ ፋና የህዝብን ድምጽ የተጠቀመበት መንገድ ነው፡፡ ለ27 አመታት በድብቅ በአስተዳዳሪዎቹ እየታዘዘ ያካበተውን ልምድ በቀጥታ ስርጭት ሲጠቀምበት ማየት ተስፋ ማስቆረጥ ብቻ አይደለም - ያስፈራል፡፡
እውን ቴሌ ለስድስት ተወዳዳሪዎች የሚሰጥ ድምጽ መሰብሰብ አቅቶት ነው? እንዳሉት አቅቷቸው ከሆነ ለምን እስከደረሱበት ደረጃ ያለውን አልወሰዱም? እኔ እስካየሁት እንኳን በቴሌቪዥን ስክሪን ላይ ከፍተኛው 26 000፣ ዝቅተኛው5000 ነበር፡፡ ለምን ችግር ካለ ሌላ ጊዜ አይካሄድም? መልሱ ቀላል ነው፤ እነሱ የህዝብ ድምጽ አያስጨንቃቸውም፤ ለእነሱ የህዝብ ድምጽ ፕሮፓጋንዳና የገቢ ምንጫ ነው፡፡ ያሳዝናል፡፡
ለመሆኑ ፋናና ቴሌ ስንት ስንት ሚሊየን ደረሳቸው? ፋና2ኛ እና 3ኛ ለወጡ ተወዳዳሪዎች እዚያው ላይ ሽልማት ማዘጋጀቱን ስናይ ገቢው ምን ያህል እንዳስፈነደቃቸውና ስሜታዊ እንዳደረጋቸው መገመት አያስቸግርም፡፡ ፋና ያላግባብ የሰበሰበውን የህዝብ ገንዘብ መመለስ አለበት፤ በንቀት ለወረወረው የህዝብ ድምጽም በግልጽ ህዝብን ይቅርታ መጠየቅ ይገባዋል፡፡
ሀገሬ ውስጥ ምርጫ ከተጀመረ ጀምሮ ድምጽ ይጭበረበራል፤ ህዝብ ድምጼን ብሎ ይነሳል፤ በዚህ የተነሳ ሰዎች ይሞታሉ፡፡ በፋና የተደረገው ይኸው ነው፤ ከህዝብ ድምጽና ገንዘብ መሰብሰብ ጀመረ፣ ገንዘቡን ወስዶ ድምጹን አይናችን እያያ ወረወረው፡፡ በዚህ የተነሳ ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ ጦርነት ተጀመረ፡፡
በመሰረቱ እኔ ትላንት ስድስቱምን ተወዳዳሪዎች ወድጃቸዋለሁ፡፡ በእርግጠኝነት ማሸነፍ አለበት የምለው አልነበረኝም፡፡ በዳኞችና በህዝብ ድምጽ የሚያሸንፈውን ለማወቅም ጉዋግቼ ነበር፡፡ የሆነው ግን እንዳያችሁት ነው፡፡
ሁለት ጥያቄ አለኝ!
አንደኛ፣ ለዲሞክራሲ ግንባታና ለህዝብ ድምጽ መከበር ታላቁን ድርሻ የሚጫወቱት የብዙሀን መገናኛዎች ናቸው፤ እንደፋና ያሉ ከሀያ ሰባት አመት በሽታ ያላገገሙ ተቋማትን ይዘን (እኔ አሁን ሌሎቹም ተቋማት ተመሳሳይ ናቸው የሚል አመለካከት እያሳሰበኝ ነው) እንዴት ነው የህዝብ ድምጽ የሚከበርበት ዲክራሲያዊ ምርጫ የምናካሂደው? ያስፈራል፡፡
ሁለተኛ፣ በየአካባቢው፣ ‹‹እገኔ (የጎጣችን ተወዳዳሪ) ነበር ማሸነፍ ያለበት›› ብሎ ከመሟገትና በህዝብ ድምጽ ላይ ከተፈጸመው ንቀት የትኛው ነው መሰረታዊ? አንድ ሰው እንደሚያሸንፍ ይታወቅ ነበር እኮ! ውሳኔው ተቀባይነት እንዳያገኝ ያደረገው የህዝብ ድምጽ አለመከበሩና እስኪቋረጥ ድረስ ከፍተኛ ድምጽ ያገኙ ተወዳዳሪዎች አለማሸነፋቸው ነው፡፡ (በነገራችን ላይ ከፍተኛየህዝብ ድምጽም አግኝተው ሊሸነፉ ይችሉ ይሆናል፤ የህዝብ ድምጽ ምን ያህል ዋጋ እንደተሰጠው አላውቅም) ይም ሆነ ይህ ግን የህዝብ ድምጽ አልተከበረም፡፡ በአጠቃላይ የህዝብ ድምጽ አለመከበር ነው ችግሩን የፈጠረው፤ እና ይህ አያሳስብም? ነገ በድምጻችን መንግስትችንን መምረጥ ስለመቻላችን ምን ዋስትና አለ? እባካችን እንደህዝብ ትልቁን ጥያቄ ቀድመን እንመልስ፡፡

28/09/2020

Akmonlink College envisions being the most Renowned Private Higher Education Institution in terms of Outstanding Quality Education, Research, Training, and Community Outreach services in East Africa and beyond.

24/09/2020

ሁለቱ ተኩላዎች፤
===========
አንድ አዛውንት በእያንዳንዳችን ውስጥ በሁለት ተኩላዎች መካከል ሁልጊዜ ስለሚካሄደው ጦርነት ለልጁ እንዲህ ሲል ይነግረዋል።
"የመጀመሪያው ተኩላ የክፉ ባህርይ ተኩላ ነው። በአዕምሯችን ውስጥ ቁጣን፣ ሀዘንን፣ ስግብግብነትን፣ እብሪትን፣ ውጥረትን፣ ጭንቀትን፣ ይፈጥራል። ሁለተኛው ተኩላ ደግሞ የጥሩ ባህርይ ተኩላ ነው። ይህኛው በአዕምሯችን በልባችንና በነፍሳችን ውስጥ ተስፋን፣ ሰላምን፣ ደስተኝነትን፣ እውነትን፣ ለጋስነትንና መልካም ሥነ ምግባርን ይፈጥራል።"
ልጁም ጠየቀ፣ "ስለዚህ ጦርነቱን ማን ያሸንፋል?"
አባትዮውም መለሰ፣ "አንተ በደንብ የምትመግበው።"
ታሪኩ ራሳችንን እንድንመረምር ያደርገናል። ጥያቄው በየቀኑ የትኛውን ተኩላ እና ምን ያህል ነው የምንመግበው? የሚለው ነው። አሉታዊ ባህርይ ባላቸው ሰዎች ራሳችንን ከከበብን ሀሜትን፣ ማደናቀፍን፣ መሸወድና ማታለልን እንዲሁም አፍራሽ ሀሳቦችን እያሳደግን ነውና ያለምንም ጥርጥር የክፉ ባህርይውን ተኩላ እያጠነከርንው ነው። በአንጻሩ ጊዚያችንን ከመልካምና ቀና ሰዎች ጋር ካሳለፍን፣ ጥሩ መጽሐፎችን ካነበብን፣ መፍትሔ ላይ ካተኮርን እና ሰዎች ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ ካገዝን የጥሩው ባህሪ ተኩላ በክፉው ላይ ድል እንዲቀዳጅ እያበረታታንው ነው። በረጅሙ የሕይወት ጉዟችንን ውስጥ ተኩላው የእኛን ባህርይ ይወክላል። ምክንያቱም በመጨረሻ ባህርያችን ወይ በጥሩው ወይ በክፉው ተኩላ ይቀረጻልና ነው።

Address

Adiss Ababa
Addis Ababa
2204

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lij Mogese daily news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share