06/08/2021
በከተማዋ አምስቱም በሮች በሦስት ቢሊዮን ብር የመገበያያ ማዕከላትና መጋዘኖች እንደሚገነቡ ተጠቆመ
***************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለማቃለል እና የሸማቾችን ጥቅምና ፍላጎት ያማከሉ ግዙፍ የመገበያያ እና የማከማቻ መጋዘኖች በከተማዋ አምስቱም የመግቢያና መውጫ በሮች እንደሚገነቡ የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ አረጋ አስታወቁ።
አቶ ሲሳይ በተለይም ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ የፌደራል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ እና በአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኤጀንሲ በጋራና በተጠና ጥናት በአምስት ዋና ዋና የአዲስ አበባ መግቢያና መውጫዎች ላይ ዘላቂ የሆኑ ትልልቅ የገበያ ማእከላትና መጋዘኖች ለመገንባት ታቅዷል።
ግንባታዎቹ ዓመቱን ሙሉ ያለማቋረጥ አገልግሎት የሚሰጡ የገበያ ማዕከላት መገንባት አለባቸው ተብሎ ታምኖ አምራቹ ያመረተውን ምርት በፈለገው ጊዜ አምጥቶ አስመዝግቦ የሚያስገባበትና መሸጥ በሚፈልግበት ጊዜ የሚሸጥበት የከተማው ማህበረሰብም በፈለገ ጊዜ መገብየት አለባቸው ተብሎ የገበያ ማዕከላት ግንባታ የቦታ ርክክብ እየተከናወነ ነው።
በዋናነት በጥናት የተለዩት ሦስት ችግሮች አሉ፤ አንደኛው የመጋዘን ችግር ሁለተኛው የፋይናንስ ችግር ሶስተኛው የምርት እጥረት ናቸው ያሉት አቶ ሲሳይ፣ ችግሮቹን ለመፍታት ሰፊ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን አመልክተዋል። የምርት እጥረት እንዳያጋጥም ከክልል አምራች ዩኒዮኖች እና ከፌደራል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ ጋር ተደጋጋሚ የምክክር መድረኮች መካሄዳቸውን ገልጸዋል።
https://www.press.et/ama/?p=52949
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን ‼
ዩቲዩብ 👇
https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
ቴሌግራም 👇
https://t.me/ethpress
ትዊተር 👇
https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ 👇
https://www.press.et/
Featured በከተማዋ አምስቱም በሮች በሦስት ቢሊዮን ብር የመገበያያ ማዕከላትና መጋዘኖች እንደሚገነቡ ተጠቆመ — August 5, 2021 comments off አዲስ አበባ፡- በአዲስ አበባ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለ...