Tadele Kasse

ሰበር ዜና የካቲት 5 መላው ህዝበ ክርስቲያን ከቅዳሴ በኃላ ከአጥቢያው ወደ መስቀል አደባባይ ድረስ በሚሄድ ድምፁን እንዲያሰማ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል!
04/02/2023

ሰበር ዜና

የካቲት 5 መላው ህዝበ ክርስቲያን ከቅዳሴ በኃላ ከአጥቢያው ወደ መስቀል አደባባይ ድረስ በሚሄድ ድምፁን እንዲያሰማ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል!

 #ሩሲያ!ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የሩስያን ፌዴሬሽን የፓርላማ አባል እና የሩስያ ...
03/02/2023

#ሩሲያ!
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የሩስያን ፌዴሬሽን የፓርላማ አባል እና የሩስያ አምባሳደር በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
የጉብኝታቸው ዋና ዓለማ በተፈጠረው የቤተክርስቲያኒቱ ወቅታዊ ችግር መፍትሔ ለማግኘትና ሓሳብ ለመለዋወጥ የጠቀሱት ሲሆን እንዲሁም ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን አብሮነቻውና ድጋፋቸውን ለመግለጽ መሆኑን ገለፀዋል።

ጾመ ነነዌን ምእመናን ጥቁር ልብስን ብቻ በመልበስ በጸሎትና በምሕላ እንዲጾሙ  ቅዱስ ሲኖዶስ አዘዘ!ሙሉ መግለጫው ከታች ቀርቧል!"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን! ከኢ...
03/02/2023

ጾመ ነነዌን ምእመናን ጥቁር ልብስን ብቻ በመልበስ በጸሎትና በምሕላ እንዲጾሙ ቅዱስ ሲኖዶስ አዘዘ!
ሙሉ መግለጫው ከታች ቀርቧል!
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን! ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የጾምና የምሕላ አዋጅ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
"የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ!
ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።"
ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 5
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በተከሰተው ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮቿን በመጣስ መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ኤጲስ ቆጶስነት ሢመት በሰጡትና በተሾመ ግለሰቦች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥር 18 ቀን 2015ዓ.ም. ቃለ ውግዘት ማስተላለፉ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ እነዚህ ሕገወጥ ቡድኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ካለመቻላቸውም በላይ በመንግሥት ኃይሎች በመታገዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተዳድራቸውን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረርና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረጉ ከመሆኑም በላይ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ሠራተኞች ካህናትና ምእመናን በማሰርና በማንገላታት ላይ ይገኛል፡፡ መንግሥትም ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር ስላልቻለ ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን በመማፀን ጸሎትና ምሕላ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተረድቷል።
በመሆነም ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ጥቁር ልብስ የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው፡፡
እንደሚታወቀው ጥቁር የእውቀት ምልክት ነው ተማሪዎች አውቀናል ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛ ከእውቀት በላይ የሆነውን አምላካችንን በመማፀን ከዚህም ማንም ሊያናውጽን እንደማይችል የምናረጋግጥበት፤ ጥቁር የእውነት ምልከት ነው ዳኞች እውነት እንፈርዳለን ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛም መከራው የሚያሰቅቀን ሳይሆን ይበልጥ ልንጸናና ልንበረታ የሚገባ መሆኑን ለዓለም ሕዝብ የምናሳይበት በመሆኑ ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን፡፡"

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምእመናንንም አንድነታቸውን እንዲያስጠብቁና ይህ ባይሆን በቀጣይ ትውልድ ሁሉ የሚያስጠይቅ ይሆናል "በዚሁ ሂደትም ከጎናችሁ እንደምንቆም ...
02/02/2023

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምእመናንንም አንድነታቸውን እንዲያስጠብቁና ይህ ባይሆን በቀጣይ ትውልድ ሁሉ የሚያስጠይቅ ይሆናል "በዚሁ ሂደትም ከጎናችሁ እንደምንቆም ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ" በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረው ድርጊት እንዳስጨነቃቸውና በቤተ ክርስቲያኗ የውስጥ ሕግ ብቻ መፈታት እንዳለበት እንደሚያምኑ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን ገለጹ::
ከማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ያደረጉት አምባሳደሩ ሩሲያ እና ኢትዮጵያ የረጅም ዓመታት ግንኙነት እንዳላቸውና ለዚህም ጥንካሬ መንፈሳዊ ትስስሩ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።
አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን አክለውም በአሁኑ ሰዓት ያለችበት ሁኔታ እንዳሳዘናቸውና እንደኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይነታቸውም እንዳስጨንቃቸው ገልጸዋል።
በቀጣይም በራሷ በቤተ ክርስቲያኗ ሕግ መሰረት በውይይት እንዲፈታ ፍላጎታቸው መሆኑን ገልጸዋል። ይቺን ቤተ ክርስቲያን ማፍረስ ማለት ሀገር ማፍረስ በመሆኑ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ሲሉ አጽንዖት የሰጡት አምባሳደሩ ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናትም እንደቀደመው ጊዜ በመተባበር እንደሚቀጥሉም አሳውቀዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምእመናንንም አንድነታቸውን እንዲያስጠብቁና ይህ ባይሆን በቀጣይ ትውልድ ሁሉ የሚያስጠይቅ ይሆናል "በዚሁ ሂደትም ከጎናችሁ እንደምንቆም ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ" በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።
ማኀበረ ቅዱስ ቴሌቪዥን

ሰበር ዜና ቅዱስ ሲኖዶስ መንግስት የቤተ ክርስቲያኒቱን መብት የማያስከብር ከሆነ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ መላው ኦርቶዶክሳውያን የሚሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ በመጥራት በደሉን ለዓለምዓቀፉ ማኅበ...
01/02/2023

ሰበር ዜና

ቅዱስ ሲኖዶስ መንግስት የቤተ ክርስቲያኒቱን መብት የማያስከብር ከሆነ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ መላው ኦርቶዶክሳውያን የሚሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ በመጥራት በደሉን ለዓለምዓቀፉ ማኅበረሰብ እንደሚገልጽ አስታወቀ።

"ነፍሴ ከሥጋዬ ስትለይ ስጋዬ በአራት ኪሎ እንዲያርፍ አልፈልግም፤ በጅማ ሀገረ ስብከት ባለች በአንዲቷ የገጠር ቤተ ክርስቲያን እንጂ። ምክንያቱም የሊቀ ጳጳሱ አጽም ያረፈበት ሥፍራ ተብሎ ምና...
01/02/2023

"ነፍሴ ከሥጋዬ ስትለይ ስጋዬ በአራት ኪሎ እንዲያርፍ አልፈልግም፤ በጅማ ሀገረ ስብከት ባለች በአንዲቷ የገጠር ቤተ ክርስቲያን እንጂ። ምክንያቱም የሊቀ ጳጳሱ አጽም ያረፈበት ሥፍራ ተብሎ ምናልባት በኔ ምክንያት ያቺ የገጠር ቤተ ክርስቲያን ጧፍ እና ዘቢብ ታገኝ ይሆናል

"የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ የሚያደናቅፍ ነገር ሲገጥም መሞት ግዴታ ነው። ሌላ የምናድርገው ነገር ባይኖርም፤መሞት ግን እንችላለን!"                     ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ
01/02/2023

"የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ የሚያደናቅፍ ነገር ሲገጥም መሞት ግዴታ ነው። ሌላ የምናድርገው ነገር ባይኖርም፤መሞት ግን እንችላለን!"
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ

♦ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ “ብትቀር ማርያምን እቀየምሀለሁ” በሚል በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከትጥር 24 (February 1) ለማካሄድ የታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲና አካ...
30/01/2023

♦ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ “ብትቀር ማርያምን እቀየምሀለሁ” በሚል በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት

ጥር 24 (February 1) ለማካሄድ የታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት የተዘጋጀ ሲሆን ሀገረ ስብከቱ እና ምእመናኑ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጎን መሆናቸውን በአደባባይ ለማሳየት የሚደረግ መሆኑን ታውቋል፡፡

መንግሥት የሕጋዊው ሲኖዶስን ውሳኔ እንዲያከብርም በዕለቱ ጥሪ ይቀርባል ተብሏል።

በዕለቱ ምእመናን ክርስቲያናዊ አለባበስ በመልበስ እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።

😁አማራ ባንክ ልዩ ነው!!! 😁================ባንኩ የትውል ባለውለታና አርቆ አሳቢ፣ አገር ገንቢ፣ እውነተኛ የኢትዮጵያ ህዝብ ተቋምና የምሁራንና የባለሀብቶች ስብስብ ነው!!! ስለሆ...
30/01/2023

😁አማራ ባንክ ልዩ ነው!!! 😁
================
ባንኩ የትውል ባለውለታና አርቆ አሳቢ፣ አገር ገንቢ፣ እውነተኛ የኢትዮጵያ ህዝብ ተቋምና የምሁራንና የባለሀብቶች ስብስብ ነው!!! ስለሆነም አማራ ባንክ በሀገር አቀፍ ፈተና ከ600 በላይ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ወጭ እንደሚሸፍን አስታወቀ።
የአማራ ባንክ ማኀበረሰባዊ አገልግሎቱን
ለማስፋት በዘንድሮው ዓመት በሀገር አቀፍ ፈተና በመላ ሀገሪቱ ከ600 በላይ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው በወር 750 ብር እየከፈለ እንደሚያስተምር አስታውቋል::

Address

Addis Ababa
1221

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tadele Kasse posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tadele Kasse:

Share