29/04/2020
ዶ/ር .
➡ ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ ይባላል. #የእመጓ፣ #የዝጎራና #መርበብት መፃሕፍት ደራሲ ነው። የሚኖረውን የሚያስተምር ብርቱ ሰው ነው።
1. በሚሰራበት መስሪያቤት ተብሎ በቦርድ የተወሰነለትን ደመወዝ አልቀበልም ብሎ በደብዳቤ መልሷል።
2. ከአንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ ለስራ ተወዳድሮ ካለፈ በኋላ፣ ደመወዙ ስለበዛ ቅጥሩን ሰርዞ ያውቃል(80,000 ብር)።
3. ከወር የቤትና የራሱ ወጪ ውጪ ያለውን የባንክ ገንዘቡን በየወሩ ለነዳያንና ለገዳማት ይሰጣል።
4. ዶ/ር አለማየዉ ዋሴ እመጓ መፀሀፍን መጀመሪያ ያሳተመዉ በቤተሰብ ወጪ ነበር
5. እመጓ የታተመበትን ዋና ብሩ ከመለሰ በኃላ ጠቅላላ ትርፉን መፅሀፉ ላይ ለተጠቁሱት project ሰጥቷል ዶ/ር አለማየዉ ዋሴ
⭕ የዶክተር አለማየሁ መርህ ምን መሰላችሁ? የራሱንና የቤተሰቡን ኑሮ ስታንዳርድ አበጅቷል።
"ቤት አለኝ" ይልህና፤ "የቤቴን አይነት ግን አትጠይቁኝ" ይልሀል።
"መኪና አለኝ" ይልህና፣ "የመኪናዬን አይነት ግን አትጠይቁኝ" ይልሃል።
"የምኖረው ከተማ ነው" ይልህና፣ "የት ከተማ ግን እንዳትለኝ" ይልሀል።
ምክንያቱም ይላል "ከቤት በላይ ቤት፣ ከመኪና በላይ መኪና፣ ከከተማ በላይ ከተማ አለ፤ ከቀበቶ በላይ እንኳን ቀበቶ አለ፣ የቀበቶ ስራው ግን ሱሪ እንዳይወልቅ ማድረግ ነው።" ይላል...
በአጠቃላይ ዶክተር አለማየሁ ምኞትን በጥልቅ ጉድጓድ ቆፍሮ የቀበረ፣ የገንዘብን አቅም ያሰነሰ ምርጥ ሰው ነው። ሲናገር እና ሲያስተምር ደግሞ አዝናኝ ነው። የፃፋቸው አስደማሚ መፃሕፍት የሱን ህይወት ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ።