Wondyefraw Abayu Authorized Accountant and Tax Consultant Firm

Wondyefraw Abayu Authorized Accountant and Tax Consultant Firm Prepare financial statements based IFRS and Consultant any TAX issues

ሮያሊቲሮያሊቲ ማለት፡-1. ማንኛውንም የሥነ-ጽሑፍ፣ የሥነ-ጥበብ፣ ወይም የሳይንሳዊ ሥራ የቅጂ መብት ሲሆን፣ የሲኒማቶግራፊ ፊልሞችና ለሬድዮ፣ ለቴሌቪዥን ወይም ለኢንተርኔት ሥርጭት የሚውሉ ፊ...
25/12/2023

ሮያሊቲ

ሮያሊቲ ማለት፡-

1. ማንኛውንም የሥነ-ጽሑፍ፣ የሥነ-ጥበብ፣ ወይም የሳይንሳዊ ሥራ የቅጂ መብት ሲሆን፣ የሲኒማቶግራፊ ፊልሞችና ለሬድዮ፣ ለቴሌቪዥን ወይም ለኢንተርኔት ሥርጭት የሚውሉ ፊልሞችና፣ ቴፖችን መጠቀም ወይም ለመጠቀም መብት ማግኘት፣
2. ከቴሌቪዥን ወይም ከሬዲዮ ወይም ከኢንተርኔት ሥርጭት ጋር ተያይዞ በሳተላይት፤ በኬብል፤ በኦፕትክ ፋበር ወይም በሌላ ተመሳሳይ ቴክኖሎጂ የሚተላለፉ ወይም የሚታዩ ምስሎችን ወይም ድምፆችን ወይም ሁለቱን መቀበል ወይም ለመቀበል መብት፤
3. ማንኛውንም የፈጠራ ባለቤትነት መብት፤ ፈጠራ፤ የንግድ ምልክት፤ ንድፍ ወይም ሞዴል፤ ፕላን የሚስጥር ቀመር ወይም ሂደት ወይም ሌላ፤ ወይም ተመሳሳይ ሀብት ወይም መብት መጠቀም ወይም የመጠቀም መብት ማግኘት ፤
4. ማንኛውንም ኢንዲስትሪያዊ፤ የንግድ ወይም ሳይንሳዊ ተሞክሮ የሚመለከት መረጃ መጠቀም ወይም የመጠቀም መብት ማግኘት ፤
5. እነዚህ ሀብቶች ወይም መብቶች መጠቀም እንዲቻል በተጨማሪነትና በተቀጽነት የሚሰጥ ድጋፍን ያጠቃልላል፡፡

በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
በፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/.../featured
በቲክቶክ፡- tiktok.com/
በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ማታ ከ 2፡30 ጀምሮ ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኃላ ኢቲዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ በወርሃዊ ጋዜጣችን፡- ገቢያችን ህልውናችን እንዲሁም በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡ - 8199 በመደወል መረጃዎችን በመጠየቅ ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን!

15/06/2022
06/11/2021

ታክስ የመጣልና የማስተዳደር ስልጣን
ክፍል አንድ
ታክስ/ግብር የመጣልና የማስተዳደር ሥልጣን የፌዴራልና የክልል መንግስታት ነው፡፡ ይህንኑ በተመለከተ ገቢ፤ የፌዴራል፣ የክልልና የሁለቱም (የፌዴራል እና የክልል) የጋራ ገቢ ተብሎ በሕገ መንግስት ተቀምጧል፡፡ በዚህ በክፍል አንድ የፌዴራል መንግስት ብቻ እንዲሰበስብ እና እንዲያስተዳድር የተሰጠውን የገቢ ዓይነቶች ስንመለከት፡-
የፌዴራል መንግስት ስልጣን

1. በወጪና ገቢ እቃዎች ላይ የሚጣል የጉምሩክ ቀረጥ፣ ታክስና ሌሎች ክፍያዎች፤
2. በፌዴራል መንግስት ባለቤትነት ስር ከሆኑ የልማት ድርጅቶች ላይ የሚሰበሰብ የንግድ ትርፍ ግብር፣ የስራ ግብር፣ የተጨማሪ አሴት ታክስና የኤክሳይዝ ታክስ፤
3. ከብሔራዊ ሎተሪ እና ሌሎች የአድል ሙከራ ገቢዎች ላይ የሚሰበሰብ ታክስ፣
4. ከአየር፣ ከባቡርና ከባህር ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የሚሰበሰብ ታክስ፤
5. በፌዴራል መንግስት ባለቤትነት ስር ከሚገኙ ቤቶችና ሌሎች ንብረቶች ገቢ ላይ የሚሰበሰብ ታክስ፣
6. የሞኖፖል ታክስ፣ የፌዴራል የቴምብር ሽያጭና ቀረጥን መሰብሰብ ለፌዴራል መንግስት ከተሰጠው ሥልጣን መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡
… ይቀጥላል

06/11/2021

ታክስ የመጣልና የማስተዳደር ስልጣን
ክፍል ሁለት …ካለፈው መረጃ የቀጠለ
ታክስ/ግብር የመጣልና የማስተዳደር ሥልጣን የፌዴራልና የክልል መንግስታት ነው፡፡ ይህንኑ በተመለከተ ገቢ፤ የፌዴራል፣ የክልልና የሁለቱም (የፌዴራል እና የክልል) የጋራ ገቢ ተብሎ በሕገ መንግስት ተቀምጧል፡፡ በክፍል አንድ መረጃችን የፌዴራል መንግስት ብቻ እንዲሰበስብ እና እንዲያስተዳድር የተሰጠውን የገቢ ዓይነቶች ላይ መረጃዎችን አድርሰናል፡፡ በዚህ ሁለተኛ ክፍል ደግሞ የክልል መስተዳድሮች እንዲሰበስቡ እና እንዲያስተዳድሩ የተሰጣቸውን ስልጣን እና የገቢ ዓይነቶቹን አቅርበንላችኋል፡-

የክልል መስተዳድሮች ስልጣን

1. ከክልል መስተዳድርና ከድርጅት ተቀጣሪዎች ላይ የሚሰበሰብ የስራ ግብር፤
2. የመሬት መጠቀሚያ ክፍያ እና በግል ከሚያርሱና በህብረት ስራ ማህበር ስር ከተደራጁ ገበሬዎች ላይ የሚሰበሰብ የንግድ ትርፍ ግብርና የተርን ኦቨር ታክስ፤
3. በክልል ከሚገኙ ግለሰብ ነጋዴዎች ላይ የሚሰበሰብ የንግድ ትርፍ ግብርና የተርን ኦቨር ታክስ፤
4. በክልል ውስጥ በውሃ ላይ ከሚደረግ ትራንስፖርት ከሚገኝ ገቢ ላይ የሚሰበሰብ ግብር፤
5. በክልል መስተዳድር በግል ባለቤትነት ስር ካሉ ቤቶችና ሌሎች ንብረቶች ከሚገኝ ገቢ ግብር፤
6. በክልል መስተዳድር ባለቤትነት ስር ካሉ ቤቶችና ሌሎች ንብረቶች ከሚገኝ ገቢ ግብር፤
7. በክልል መስተዳደር ባለቤትነት ስር ከሚገኙ የልማት ድርጅቶች የሚሰበሰብ የንግድ ትርፍ ግብር፣ የስራ ግብር፣ የተርን ኦቨርና ኤክሳይዝ ታክስ፤
8. በክልል መስተዳድር አካላት ከሚሰጡት ፍቃዶችና አገልግሎቶች የሚመነጩ ክፍያዎች፣
9. ከደን የሮያሊቲ ክፍያ፤
10. ከአነስተኛ የማዕድን ሰራዎች ላይ የሚሰበሰብ የማእድን ገቢ ግብር እና የሮያሊቲና የመሬት ኪራይ ክፍያዎች የክልል መስተዳድሮች ከሚሰበስባቸው እና ከሚስተዳድሯቸው ገቢዎች ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው።
ይቀጥላል …

Address

Ahemed Comercial Center Lideta
Addis Ababa

Telephone

+251912022627

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wondyefraw Abayu Authorized Accountant and Tax Consultant Firm posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wondyefraw Abayu Authorized Accountant and Tax Consultant Firm:

Share