23/08/2020
💠 ሳይንስን ለመማር እና ለማስተማር የሚጠቅሙ 5 የነፃ ድህረገፆች
1) Scitable
ዝንባሌዎ ስለ Natural science ማወቅ ከሆነ እንግዲያውስ ሳይቴብል ለርሶ የተከፈተ ድህረገፅ ነው፡፡ ይህ ድህረገፅ በማበብ ብቻ በግልዎ መማር የሚችሉበት ሲሆን ልክ እንደ ት/ቤት በጋራም ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በኦንላይን ክፍል ውስጥ መማር ይችላሉ፡፡ ይህ ድህረገፅ በዓለም ላይ የሳይንስ ነክ ፅሁፎችን በማሳተም በሚታወቀው በ Nature Publishing Group ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን በሌሎች ትልልቅ የሳይንስ ኩባኒያዎች ስለሚደገፍ ት/ቱን በነፃ ነው የሚያስተምረው፡፡
በዚህ የኦንላይን ት/ቤት ውስጥ በ 4 ብቁ ፕሮፌሰሮች የተዋቀረ ሲሆን ተማሪዎች ለሚጠይቁት ማንኛውም ጥያቄ ከ 48 ሰዓት ባነሰ የጊዜ ገደብ ውስጥ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡
2) iTunes U
ይህ ድህረገፅ ከ 600 በላይ በሆኑ ዩኒቨርስቲዎች የሚደገፍ ሲሆን ዓለም ላይ አሉ የተባሉ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎችን ማለትም የስታንፎርድ፣ የያሌ እና የኤም አይቲን ዩኒቨርሲቲዎችን የማስተማሪያ መፅኃፎችና ሌክቸር ኖቶች ሰብስቦ ይዟል፡፡ ይህ ድህረገፅ በተለይ ለመምህራን ትልቅ እፎይታን ያመጠጣ ሲሆን የማስተማሪያ መፅሀፎች፣ ቪዲዮዎችን እና ፈተናዎችን አካቶ ይዟል፡፡
ድህረገፁ ሰፋ ያለ ይዘት ያለው ሲሆን በውስጡ የግብርና፣ አስትሮኖሚ፣ ባዮሎጂ፣ ፊዚክስ፣ጂኦሎጂ ፣ ኬሚስትሪ እና የመሳሰሉ ሳይንሶችን በጥልቀት ይተነትናል፡፡
3) Space.com
በዚህ ድህረገፅ ውስጥ ስለ ሌሎች ዓለማት ስለፕላኔቶች እና ከነርሱ ስለተያያዙ ሌሎች ነገሮች በሰፊው ይተነተናል፡፡ ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን፣ ፎቶዎችን እና ቪዲዮዎችን "This Week in Space"(ሳምንቱ በስፔስ ውስጥ) በሚለው ፕሮግራማቸው ውስጥ ያስቃኛሉ፡፡
4) Scientific American
ስለጤና፣ ስለዝግመተለውጥ፣ እና ስለ ተለያዩ የሳይንስ ክፍሎች በሰፊው የሚተነተንበት እና ይበልጡን ለመማር ማስተማር ሂደት እንዲመች ተደርጎ የተሰራው ይህ ድህረገፅ በአሜሪካን ውስጥ በሳይንስ ምንጭነቱ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ከሆነው ከአሜሪካን ሜጋዚን ጋር በጥምረት የሚሰራ ሲሆን ወቅታዊ መረጃዎችን በተደራጀ መልኩም ያቀርባል፡፡
5) PhysicsCentral
የፊዚክስ አምሮትዎን የሚቆርጥና በሁሉም የእድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ፈጣን አዕምሮ ባለቤቶች የሚመች ድህረገፅ ን፡፡ በ American Physical Society ተዘጋጅቶ የሚቀርበው ይህ ድህረገፅ ተመራማሪዎችን እና ተማሪዎችን የሚያገናኝ መድረክ ነው፡፡
Share & joine us
https://t.me/yDtech
It’s all about technology 👉🏾Hacking and tips 👉🏾 setup 👉🏾App recommendations for android & ios 👉🏾Entertainment news ✅Contact us 🟡https://t.me/DaniTanash 🟡https://t.me/YaredTech