06/04/2026
ዓለም እፎይ ልትል ይሆን?
📌በኢራን እና አሜሪካ መካከል የ45 ቀናት የተኩስ አቁም አንዲደረግ ጥሪ ቀረበ
| በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተፈጠረውን የጦርነት ውጥረት ለማርገብ፣ አሸማጋይ ሀገራት የ45 ቀናት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርበዋል። ፓኪስታን፣ ቱርክ እና ግብፅ ባመቻቹት በዚህ የሽምግልና ጥረት፣ ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች የቀረበላቸውን እቅድ ለመቀበል አዎንታዊ ፍላጎት ማሳየታቸው ተገልጿል።
ይህ የ45 ቀናት የተኩስ አቁም እቅድ፣ በቀጣይ ወደ ዘላቂ ሰላም እና ቋሚ የተኩስ አቁም ሊሸጋገር በሚችልበት መንገድ ላይ ለመምከር የተዘጋጀ ነው። በዚሁ ወሳኝ ውይይት ላይም የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ እንዲሁም የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ተሳትፈዋል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ቅዳሜ ለኢራን ሁለተኛውን የ48 ሰዓታት የጊዜ ገደብ መስጠታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ አሁን ላይ አሸማጋዮቹ ያቀረቡት ይህ አዲሱ የስምምነት ሀሳብም በቀጣዮቹ 48 ሰዓታት ውስጥ ወደ ትግበራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።
ምንጭ:-
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)