Ela Elias Dese Mamo

Ela Elias Dese Mamo The fear of the Lord is the beginning of knowledge

28/05/2025
ስኬት!አሁን ዋጋ ከፍለህ ከጣፋጭ እንቅልፍህ ስትነሳ ስኬማ ሆነሀል፤ ምክንያቱም ስኬት በየቀኑ የምትኖረው ህይወት ነው እንጂ አሳደህ የምትይዘው ጭራ አይደለም!ስለዚህ ለፈጣሪህ ምስጋናህን ስታቀ...
26/05/2025

ስኬት!

አሁን ዋጋ ከፍለህ ከጣፋጭ እንቅልፍህ ስትነሳ ስኬማ ሆነሀል፤ ምክንያቱም ስኬት በየቀኑ የምትኖረው ህይወት ነው እንጂ አሳደህ የምትይዘው ጭራ አይደለም!

ስለዚህ ለፈጣሪህ ምስጋናህን ስታቀርብ ስኬታማ ነህ፣ ስፖርቱን ስትሰራ ስኬታማ ነህ፣ ሺወሩን ወስደህ ቁርስህን በልተህ ወደ ስራ ስትገባ ስኬታማ ነህ፤ ወዳጄ ራስህን ለማሳደግ በየቀኑ ዋጋ ስትከፍል በየቀኑ ከፍ የሚል የስኬት ፎቅ እየገነባህ ነው!

ጥረትህን አታቁም!

አንዳንዴ ከጓደኞችህ ወይ በዙሪያህ ካሉ ሁሉ ኋላ መቅረትህን አትጥላው፤ ምክንያቱም ረጅም ርቀት ለመወርወር ወደ ኋላ በደምብ መንደርደር ወሳኝ ነው።

እየታሸህ ያለኸው በደምብ እንድትበስል ነው፤ እድል ጓዟን ጠቅልላ እጅህ እስክትገባ ጥረትህን እንዳታቆም! የዚህ አለም እድለኞች አብዝተው የሚለፉ እንጂ አብዝተው የሚመኙ አይደሉም።

መልካም ቀን🙏
Negn

በተቃውሞህ እደግ!ከጅማሬህ ማግስት ስኬትን ብትፈልግም የሚገጥምህ ግን ቅስም ሰባሪ፣ ተስፋ አስቆራጭ፣ ሚዛን የማይደፋ ተቃውሞ ሆኖ ታገኘዋለህ። ምናልባትም አንዳንድ ተቃውሞዎች ምክንያታቸው መጀ...
25/05/2025

በተቃውሞህ እደግ!

ከጅማሬህ ማግስት ስኬትን ብትፈልግም የሚገጥምህ ግን ቅስም ሰባሪ፣ ተስፋ አስቆራጭ፣ ሚዛን የማይደፋ ተቃውሞ ሆኖ ታገኘዋለህ። ምናልባትም አንዳንድ ተቃውሞዎች ምክንያታቸው መጀመርህ ብቻ ሊሆን ይችላል። ለምን ጀመርክ? ለምን ተሽለህ ተገኘህ? ለምን የእራስህን መንገድ መረጥክ? ለምን ተለይተህ ትወጣለህ? የሚልቱ ጥያቄዎች በተቃርኖ በኩል ይመጡብሃል። ስለጉዞህ ማስረዳት ትችላለህ፣ ስለውሳኔህ ትክክለኛነት አስረግጠህ መናገር ትችላለህ፣ የህልምህን አዋጭነት፣ የአላማህን ትርጉም ሰጪነት በሚገባ መግለፅ ትችላለህ፣ ነገር ግን ተቃዋሚህ ይህን ሁሉ መስማት አይፈልግም። ያንተ ከማትጠብቀው ተቃውሞ ጋር መጋፈጥ ለጊዜው ቢያስደነግጥህም ወደፊት እስከሄድክ ድረስ ግን የማይቀርልህ ጉዳይ ነው። የምርም እየሰራህ ከሆነ የምርም ጊዜ ወስዶ፣ ባጀት መድቦ፣ እራሱን ሰጥቶ፣ ስሜቱን አስገዝቶ፣ ሽንጡን ገትሮ፣ አንገቱን አቅንቶ የሚከራከርህና የሚሞግትህ ሰው አታጣም።


አዎ! ጀግናዬ..! በተቃውሞህ እደግ!

በሚሰነዘርብህ ሃይለኛ ቃላት የወሳኙ ጉዞህን መሰረት አፅና፣ በሚሰነዘርብህ የትቺት ሃሳብ የተሻለውን ማንነትህን ገንባ። ማንም ሊቃወምህ ቢመጣ አትታገለው፣ ማንም አደናቅፎ ሊጥልህ ቢለፋ ከእርሱ ጋር አታካራ ውስጥ አትግባ፣ የትኛውም የማያውቅህ ሰው ስምህን ለማጥፋት ቢሽቀዳደም ሲደክመው ይተዋልና ትኩረትህን እራስህ ላይ አድርግ። የሚሰጥህ ጥሩ አስተያየትና አድናቆት ያዘናጋል፣ የሚጣልብህ ተቃውሞና ትቺት ግን እራስህን በየጊዜው እንድትመለከት ያነሳሳሃል። ተቃውሞ ባይኖር እድገትህ ባሰብከው ልክ እንደማይሔድ ተረዳ። የሰው ልጅ እንዳይጠፋ ትንሽም ቢሆን ጉሸማና አስደንጋጭ ቃላት ያስፈልጉታል። አንድም ለፈተና ሁለትም ለንቃት። "ተቃውሞ በርተቶብኛል፣ እኔ መስራት ብፈልግም የሚቀበለኝ ሰው የለም፣ እኔ ባምንበትም የሚያምንብኝ የለም" ብለህ ብታቆም ገና ከጅምሩ ፈተናውን ወድቀሃል።

አዎ! እይታህን ካስተካከልክ የትኛውንም ተቃውሞህን ወደ ብርታትና ለላቀው ክፍታ ወደሚያደርስህ መሸጋጋሪያ ድልድይ መቀየር ትችላለህ። ዛሬ ተቋቁመህ የምታልፈው ጫና ነገ ይገነባሃል፤ ዛሬ ተቃውሞህን እንደምንም ችለህ ብትሻገረው ነገ እራስህን በልበሙሉነት ታመሰግናለህ። እንቅፋቶቹን መሸጋጋሪያ፣ መሳናክሎቹንም መወጣጫ ላደረገ ሰው ኩራቱ ውሳኔው ነው። ማንም ምንም ማለት ይችላል፣ አንተም ከተባለው ውስጥ የምትፈልገውን መርጠህ መውሰድ ትችላለህ። ህይወት የምርጫ ጉዳይ እንደሆነች እንዳትረሳ። አንተ ህልምህን እንደመረጥከው ሁሉ ሌላውም ነቃፊነትና አቃቂር አውጪነትን መምረጥ እንደሚችል እመን። ያንተ ደግነት ለሌላው ንፉግነት ሊሆን ይችላል፣ ያንተም መልካምነት ለአንዳንዱ ክፋትና አጥፊነት ሊሆን ይችላል። "ለምን ተተቸው" ማለቱን አቁምና "ከትቺቴ ምን ልውሰድ? ብልህ እራስህን ጠይቅ። በሚያሳድጉህ ተቃውሞህ ላይም የእራስህን ስኬት መገንባቱን እወቅበት።

መልካም ቀሪ ለሊትና ቀን🙏
Ella

13/05/2025

2895 Followers, 5945 Following, 374 Likes - Watch awesome short videos created by El@ ሚሊየነር

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ela Elias Dese Mamo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share