Yoseph Land and Real Estate consultants

Yoseph Land and Real Estate consultants land and real estate consulting agency would like to inform you that its dedicated to consult you on

The renewal of the Bole-Atlas artery.👏
19/02/2026

The renewal of the Bole-Atlas artery.👏

24/01/2026

የንግድ ቤት የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው በተጠናቀቁ የ40/60 የጋራ ህንጻዎች ላይ የሚገኙ 1471 ንግድ ቤቶችን ለ8ተኛ ዙር እንዲሁም በካፒታል ፕሮጀክት የተገነቡ በጀርመን ሳይት ላይ የሚገኙ 32 ንግድ ቤቶችን በ2ተኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጩ ማስተላለፍ ይፈልጋል።

በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ በግልጽ ጨረታ ያቀረባቸውን ንግድ ቤቶች ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከጥር 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 21 ቀናት በአንሊይን በዌብሳይት https://housebid.aahdc.gov.et/ በመግባት አስፈሊጊውን ምዝገባ በማድረግ የማይመለስ ብር 1,000/አንድ ሺህ/ በቴሌ ብር አማካኝነት ክፍያ በመፈጸም የጨረታ ሰነድ በሶፍት ኮፒ መግዛት የምትችሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ (ቅዳሜን ሙለ ቀን ጨምሮ) ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሽት 11፡30 ድረስ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ በተገለጹት ቦታዎች ላይ እገዛ ማማኘት እንደሚቻል እናሳውቃለን።

አድራሻ
1. አዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮፖሬሽን (ምስራቅ ቅርንጫፍ)
ቦታ 49 ማዞሪያ ቦሌ አያት 2 ሰይት(ሎሚ ከለር)

2. የካ ክ/ከተማ አስተዳደር ቤቶች አስ/ጽ/ቤት ቦታ መገናኛ

3. አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ቤቶች አስ/ጽ/ቤት
አቃቂ መናኸሪያ ፊት ለፊት

4. አዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት
ባምቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት አጠገብ

17/01/2026

የመሬት ሊዝ ጨረታ ተራዘመ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 8ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለተጨማሪ 10 ቀናት መራዘሙን የጨረታ ኮሚቴ አሳውቋል፡፡

220 ፕሎቶች በዘጠኝ ክፍለ ከተሞች በተሰናዱበት በዚህ ጨረታ የኦንላይን ሰነድ ሽያጩ ከታህሳስ 25/2018 እስከ ጥር 12/2018 ዓ.ም በተመቻቸው የተቋሙ ድረ-ገፅ ሲሸጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ሆኖም በተለያየ ምክንያት የጨረታ ሰነድ ላልገዙ አካላት ተጨማሪ እድል ለመስጠትና የተሳታፊዎችን ቁጥር ለማሳደግ እንዲያግዝ በደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀፅ 20 በተደነገገው መሰረት የሰነድ ሽያጩን ከጥር 13/2018 ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት እንዲራዘም ተደርጓል፡፡

ስለሆነም ፍፁም ፍትሐዊና ግልፅ በሆነው የከተማችን የመሬት ሊዝ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ አካላት የጨረታ ሰነዱን ከጥር 13/2018 እስከ ጥር 26/2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ የቴሌ ብር አካውንታችሁን ተጠቅማችሁ ሰነዱን ከተቋሙ ድረ-ገፅ (landlessdocument.aalb.gov.et) በመገዛት እንድትወዳደሩ ቢሮው በድጋሚ ጥሪ እያቀረበ የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ ጥር 26/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 መሆኑን እንገፃለን፡፡

በተጨማሪም ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በወጣው አዲስ ልሣን ጋዜጣ ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የጨረታ ቁጥር አ/ቃ/ክ/ከ/27/18 የቦታ ኮድ LDR-AKI-MIX-00014927 የቦታ ስፋት 992 ካሜ ተብሎ የተጠቀሰው 233 ካ.ሜ በሚል የተስተካከለ ሲሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ለሚኩራ፣ልደታ እና ኮልፌ ቀራኒዬ ክ/ከተማ በድምሩ 82 ቦታዎች ከጨረታ ተሰርዘዋል ።

የተሰረዙ ቦታዎችን ኮድና ዝርዝር መረጃ ነገ ጥር 09/2018 ታትሞ በሚወጣው አዲስ ልሳን ጋዜጣ ላይ ይመልከቱ።

 ቀን፡- 23/04/2018 ዓ.ም                               የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ7 ክፍለ ከተሞች የሚገኙና ለተለያዩ አገልግሎ...
14/01/2026



ቀን፡- 23/04/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ7 ክፍለ ከተሞች የሚገኙና ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ጥቅምት 01 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ በማውጣትና የጨረታ ሂደቱን ተከትሎ ግልጽ ጨረታ በማካሄድ ከህዳር 20ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ ለአንደኛ አሸናፊዎች ጥሪ ተደርጎላቸዉ አብዛኞቹ የሊዝ ዉል የተዋዋሉ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ የቦታ ኮዳቸው ከዚህ በታች የተገለጸ የሊዝ ቦታዎች አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡ ተጫራቾች ውል ስላልፈጸሙባቸው በሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀፅ 25 ንዑስ አንቀፅ 6 መሰረት ሶስተኛ የወጣችሁና ስማችሁ ከቦታ ኮዱ ጋር የተገለጸ ተጫራቾች አንደኛ አሸናፊ ባቀረበዉ ዋጋ እና ቅድመ ክፍያ በመክፈል መዋዋል የምትፈልጉ ከሆነ ከቀን 23/04/2018ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000004337631 ቅድመ ክፍያዉን ገቢ በማድረግና የከፈላችሁበትን የባንክ ስሊፒ በመያዝ በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርባችሁ የሊዝ ዉል መዋዋል የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

19/12/2025
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በ7 ክፍለ ከተሞች የሚገኙና ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በ...
13/12/2025

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በ7 ክፍለ ከተሞች የሚገኙና ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ጥቅምት 01 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ በማውጣት ከህዳር 01 ቀን 2018ዓ.ም እስከ ህዳር 05 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ በይፋ ተከፍቶ አሸናፊዎች መለየታቸው ይታወሳል። ይህን ተከትሎ አሸናፊዎች በተቋማችን በመቅረብ የሊዝ ዉል እንድትፈጽሙ ህዳር 20 ቀን 2018ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ጥሪ ባስተላለፍነው መሰረት በሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 በተቀመጠው የአስር ቀን ገደብ ውስጥ በርካታ የሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ቢሮ ቀርበው የሊዝ ዉል ፈጽመዋል፡፡

ይሁን እንጂ ስማችሁ ከዚህ በታች የተገለጸ የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች በደንቡ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀርባችሁ ውል አልፈፀማችሁም።

በመሆኑም የሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀጽ 25 ንኡስ አንቀፅ 4 በግዜ ገደብ ዉል ያልፈፀሙ አንደኛ የወጡ አሸናፊ ተጫራቾች በሶስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው ውል እንዲፈጽሙ የማስጠንቀቂያ ጊዜ እንዲሰጣቸው በሚደነግገው መሰረት ከ06/04/2018ዓ.ም እስከ 08/04/2018 ባሉት 3/ሶስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቀርባችሁ የሊዝ ዉል እንድትፈጽሙ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቢቀር በሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀጽ 25 ንኡስ አንቀፅ 5 መሰረት አሸናፊነታችሁ ተሰርዞ ያስያዛችሁት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ በማድረግ ሁለተኛ ለወጡ ተጫራቾች እድሉ የሚሰጥ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ለአልሚዎች
01/12/2025

ለአልሚዎች

Address

22 Mazoria
Addis Ababa
120833

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yoseph Land and Real Estate consultants posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share