GA Accountancy & Tax Consulting Firm in Eth

GA Accountancy & Tax Consulting Firm in Eth Accountancy & Taxation
GA የተፈቀደለት የሂሳብ አዋቂና የኦዲት ድርጅት
- ስለ ታክስና ግብር ማማከር
- አመታዊ የሒሳብ ስራ
- ቢዝነስ ፕላን 0926066262 / 0912803445
[email protected]

13/06/2024

*563 ነጥብ 6 ቢሊዮን ታክስና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ለመሰብሰብ ታቅዷል::*
‼️
*የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።*

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 31ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያደረገ ሲሆን ረቂቅ በጀቱ ከ2016 በጀት አንጻር የ21 ነጥብ 1 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል።

ምክር ቤቱ በስብሰባው የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ የፌደራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት መግለጫ አዳምጧል።

ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ረቂቅ በጀቱ ከሁለተኛው አገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር በተጣጣመ መልኩ መዘጋጀቱንና ጤናማ የፊስካል ስርዓት ማረጋገጥን አላማ ያደረገ መሆኑን አመልክተዋል።

ረቂቅ በጀቱ የተዘጋጀው ቅድሚያ ትኩረት የሚደረግባቸው የገቢና የወጪ የፊስካል ፖሊሲ አቅጣጫዎችን፣ ወቅታዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታንና የኢኮኖሚ ማሻሻያውን የትኩረት አቅጣጫ ባገናዘበ መልኩ እንደሆነም ተናግረዋል።

ለዚህም ገቢን በማሳደግና የወጪ ሽግሽጎችን ተግባራዊ በማድረግ የበጀት ጉድለትን ትርጉም ባለው መልኩ መቀንስንም ታሳቢ አድርጓል ነው ያሉት።

በዚሁ መሰረት የ2017 ዓ.ም ረቂቅ በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ሆኖ መቅረቡን ይህም ከተያዘው በጀት ዓመት አንጻር የ21 ነጥብ 1 በመቶ ወይም የ169 ነጥብ 56 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል።

ከዚህም ውስጥ 451 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ለመደበኛ፣ 283 ነጥብ 2 ቢሊዮን ለካፒታል ወጪዎች እና 236 ነጥብ 7 ቢሊዮን ለክልል መንግስታት የበጀት ድጋፍ የተመደበ ነው።

ለክልል መንግስታት ከተመደበው የበጀት ድጋፍ 14 ቢሊዮን የሚሆነው ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ እንደሚውልም አመልክተዋል።

ከተያዘው በጀት ውስጥ 502 ቢሊዮን ከገቢ ግብር ለመሰብሰብ መታቀዱንና በአጠቃላይ 563 ነጥብ 6 ቢሊዮን ታክስና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ለማሰባሰብ መታሰቡን ጠቁመዋል።

ከተመደበው በጀት 139 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብሩ ለእዳ ክፍያ እንደሚውልም ማብራራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል። የበጀት ጉድለቱን ትርጉም ባለው መልኩ መቀነሱን አመልክተዋል።

ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የተመደበላቸውን በጀት ለታለመለት አላማ በቁጠባና በላቀ ውጤታማነት ማዋል እንዳለባቸው አሳስበዋል። የመንግስት ግዢዎች ሕጋዊ ስርዓትን በተከተለ መልኩ መከናወን እንደሚገባቸውም ገልጸዋል።

ምክር ቤቱ በረቂቅ በጀቱ ላይ ከተወያየ ለዝርዝር እይታ ለፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ ይጠበቃል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ባደረገው 34ኛው መደበኛ ስብሰባ የ2017 ዓ.ም የፌደራል መንግስት በጀት ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ይታወቃል።

11/06/2024

በ2017 በጀት ዓመት 236.7 ቢሊዮን ብር ለክልሎች የበጀት ድልድል እንዲሆን ለፓርላማው ቀረበ

የገንዘብ ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም. ካቀደዉ ጠቅላላዉ በጀት 971.2 ቢሊዮን ዉስጥ ለክልሎች ብር 236.7 ቢሊዮን በጀት እንዲሆን መመደብን ለተወካዮች ምክርቤት አቅርቧል።

መንግስት ለ2017 ከመደበው በጀት ዉስጥ ለመደበኛ 451.3 ቢሊዮን ፣ ለካፒታል ወጪዎች 283.2 ቢሊዮን እንዲሁም ለክልላዊ የበጀት ድጋፍ ደግሞ 236.7 ቢሊዮን ብር መሆኑን ጠቁሟል።

ከዚህ በጀት ዉስጥ 14 ቢሊዮን የሚሆነው የዘላቂ ልማትን ለማስፈፀሚያ ለክልሎች የተመደበ ድጋፍ መሆኑ ነዉ የገንዘብ ሚኒስትር ዛሬ ለተወካዮች ምክርቤት ባቀረበዉ የ2017 በጀት ዓመት መግለጫ ላይ የገለፀው ።

ለክልሎች ከተመደበው በጀት ዉስጥ 215.3 ቢሊዮን የሚሆነዉ ከመንግሥት ግምጃ ቤት የሚሸፈን ቀሪዉ ከፕሮጀክት ርዳታና ብድር የሚሸፈን መሆኑን ካፒታል ሰምቷል።

የ2016 በጀት ለፌደራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች 369.6 ቢሊዮን፣ ለካፒታል ወጪዎች ብር 203.9 ቢሊዮን፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ብር 214.07 ቢሊዮን፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ ብር 14 ቢሊዮን በጠቅላላው ብር 801.65 ቢሊዮን ብር ሆኖ መፅደቁ ይታወቃል ።

11/06/2024

ምክር ቤቱ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ
-------------------
(ዜና ፓርላማ) ሰኔ 4፣ 2016ዓ.ም፤ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌዴራል መንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል::

ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጆ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

አዋጁ ከዚህ ቀደም በመንግስት የግዥና ንብረት አሰተዳደር ሂደትና ትግበራ ወቅት በአፈፃፀም ሲያጋጥሙ የነበሩ እና ለመልካም አሰተዳደር ችግር ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ የአሰራር ጉድለቶችን ለማረም ወሳኝ እንደሆነ ተገልጿል::

አዋጁ የመንግሥት የግዢና ንብረት አሰተዳደር ከቴክኖሎጂ ለውጥ ጋር መራመድ እንዲችል ለማድረግና የሀገር ውስጥ ተወዳዳሪዎች ያላቸውን ተሳትፎ ለማበረታታት የሚያስችሉ ድንጋጌዎችን ያካተተ ስለመሆኑም ተጠቁሟል::

ወጥ የሆነ ሀገራዊ የመንግሥት ግዢ እና የንብረት አሰተዳደር ስርአት ለመዘርጋት የሚያስችል አዋጅ እንደሆነም በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ተብራርቷል::

አዋጁ በመንግስት ልማት ድርጅቶች ላይም ተፈፃሚ እንደሚሆን ተጠቁሟል::

በግዢና ንብረት አሰተዳደር ሂደት የሚከሰት የህግ ጥሰት የሚያስከትለውን አስተዳደራዊ ተጠያቂነት ግልፅ የሚያደርግ አዋጅ እንደሆነም ተገልጿል::

የምክር ቤቱ አባላት በአዋጁ አተገባበር ላይ ሀሳብና አስተያየት ያቀርቡ ሲሆን፤ አዋጁ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ላይ ተፈፃሚ ሲሆን ተወዳዳሪነታቸውን ሊገድብ እንደሚችል ያላቸውን ስጋት አንስተዋል::

የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጆ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች እና የመንግሥት ሴክተር መስሪያ ቤቶች ወጥ የሆነ ሀገራዊ የግዢ ስርአት ሊኖራቸው እንደሚገባ በአለም አቀፍ ጥናት የተደገፈ ውሳኔ መሆኑን አስረድተዋል።

ይሁንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተወዳዳሪነታቸውን እና ትርፋማነታቸውን በማይነካ መልኩ የግዢ መመሪያ አዘጋጅተው መስራት እንደሚችሉ ነው የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ያብራሩት::

በመጨረሻም የፌዴራል መንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1333/2016 ሆኖ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል

Government organisation

09/06/2024

ዓለም ባንክ፣ በአውሮፓዊያኑ 2023 የዓለም የወደቦች የብቃት መለኪያ ለሶማሊላንዱ በርበራ ወደብ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ወደቦች ቀዳሚውን ደረጃ ሰጥቶታል። በድርጅቱ የደረጃ ምደባ መሠረት፣ በርበራ የካርጎ መርከቦችን በማስተናገድ አቅሙ ከዓለም 379 ወደቦች 106ኛ ደረጃ አግኝቷል። ጅቡቲ ወደብ በዓለም 348ኛ ደረጃ የተሰጠው ሲኾን፣ የኬንያው ሞምባሳ ወደብ ደሞ 328ኛ ደረጃ አግኝቷል። የጅቡቲ መንግሥት፣ ለጅቡቲ ወደብ የተሰጠውን ደረጃ "አድሏዊ" በማለት ውድቅ አድርጎታል። ዓለም ባንክ፣ የዓለም ወደቦችን ለማወዳደር የተጠቀመው መስፈርት፣ ካርጎ ጫኝ መርከቦች ወደቦች ላይ ጭነታቸውን ለማራገፍ የሚፈጅባቸውን ጊዜ ነው።

09/06/2024

የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም ከተዳከመ የዋጋ ንረት እንደሚባባስና የነዳጅና ማዳበሪያ ዋጋ እንደሚጨምር ማስጠንቀቁን ከአንድ የድርጅቱ ሰነድ ላይ መመልከቱን ሪፖርተር ዘግቧል። መንግሥት የውጭ ኩባንያዎች በአስመጭነትና ላኪነት እና በችርቻሮና ጅምላ ንግድ እንዲሳተፉ የፈቀደው፣ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅትና ከዓለም ባንክ ብድር ለማግኘት ሲል ሊኾን እንደሚችል ሰነዱ ማመልከቱን ዘገባው ጠቅሷል። ኹለቱ ተቋማት የብር የመግዛት አቅም እንዲዳከም እንደሚፈልጉና የእስካኹኑን የዋጋ ንረት ከአለመረጋጋትና ከዓለማቀፍ የሸቀጦች ዋጋ መጨመር ጋር እንደሚያያይዙት ሰነዱ ያብራራል ተብሏል። ብሄራዊ ባንክ፣ በተያዘው በጀት ዓመት ማብቂያ የመደበኛውንና የጥቁር ገበያውን የምንዛሬ ልዩነት ልዩነት ለማጥበብና ለ25 ቀናት የሚበቃውን የውጭ ምንዛሬ ክምችት ወደ አንድ ወር ለማሳደግ ማቀዱን ሰነዱ ይጠቅሳል ያለው ዘገባው፣ ባንኩ በቀጣዩ ዓመት ሰኔ የውጭ ምንዛሬ ክምችቱን ወደ ኹለት ወር ለማሳደግ ማሰቡንም እንደጠቆመ አመልክቷል። ኢትዮጵያ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ ከእያንዳንዳቸው 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማግኘት ድርድር ላይ ናት።

12/07/2023

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ለመነገድ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደረሰች
ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመታት ገደማ በፊት ሥራ ላይ በዋለው የአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ለመነገድ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሳለች። አገሪቱ በቀጠናው የምትነግዳቸውን ከስድስት ሺሕ በላይ ሸቀጦች ዝርዝር እና የታሪፍ አከፋፈል ሁኔታ በኬንያ በሚደረግ ስብሰባ ላይ ታቀርባለች። ይኸ ሒደት ኢትዮጵያ በቀጠናው እንድትነግድ መንገድ ይጠርጋል።
ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመታት ገደማ በፊት ሥራ ላይ በዋለው የአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ለመነገድ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሳለች። አገሪቱ በቀጠናው የምትነግዳቸው ሸቀጦች እና አገልግሎቶች ተለይተው ዝርዝሩ በመንግሥት መጽደቁን የተናገሩት የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ "ኬንያ ናይሮቢ በሚካሔደው የአፍሪካ ንግድ ሚኒስትሮች መድረክ ላይ ኢትዮጵያ ሥራ ለመጀመር የሚያስችላትን ዝግጅት ማጠናቀቋን ታበስራለች" ሲሉ ባለፈው ሰኔ 23 ቀን 2015 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለንግድ እና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ አባላት አስረድተዋል።
አቶ ካሳሁን የጠቀሱት የናይሮቢው ስብሰባ 54 የአፍሪካ የንግድ ሚኒስትሮች የሚሳተፉበት በአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና አተገባበር ላይ የሚያተኩር ነው። በዚህ ስብሰባ ኢትዮጵያ በቀጠናው የምትነግዳቸውን "ከስድስት ሺሕ በላይ" ሸቀጦች እና አገልግሎቶች ዝርዝር እንዲሁም የምትከተለውን የቀረጥ ሥርዓት ሥምምነቱን ለፈረሙ አገራት ታቀርባለች። "ከስድስት ሺሕ በላይ የዕቃዎች ምርት የስሪት ሀገር ልየታ" መከናወኑን ያስረዱት ሚኒስትር ድኤታው "የትኛው ምርት ነጻ ይሁን? የትኛውን ምርት ለተወሰነ ጊዜ እንያዝ? የትኛው ምርት እስከ ዝንተ ዓለም አንከፍተውም የሚለው ጉዳይ ሰፊ ክርክር ተደርጎበት" መጽደቁን ገልጸዋል።
ይኸ ሒደት የንግድ ቀጠናውን የሚመሠርተውን ሥምምነት በመጋቢት 2011 በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በማጽደቅ የተገለጠው የኢትዮጵያ "ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት" ወደ ተግባር የሚያሸጋግር ነው። የአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለ1.3 ቢሊዮን ሸማቾች ወጥ የገበያ ሥርዓት ለመፍጠር የተበጀ ነው። ከኤርትራ በቀር 54 የአፍሪካ አገራት ሥምምነቱን ፈርመዋል።
ሥምምነቱን ካጸደቁ 47 ገደማ አገራት መካከል 39 የሚሆኑት በቀጠናው የሚነግዷቸውን ሸቀጦች እና አገልግሎቶች አቅርበው ተቀባይነት እንዳገኘላቸው የንግድ ፖሊሲ አማካሪው አቶ ብሩህ ገመዳ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። አቶ ብሩህ እንደሚሉት የኢትዮጵያ ቀጣዩ እርምጃ በአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ለመነገድ ከተዘጋጁ ሌሎች አገሮች ጋር የሚደረግ ድርድር ይሆናል። ከሌሎች አገሮች ጋር የሚደረገው ድርድር ሸቀጦች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ሲገቡ የሚከፈልባቸው ቀረጥ ላይ ያተኮረ ነው።
አቶ ብሩህ ለአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ፈራሚዎች የሚከፈቱ የአገልግሎት ዘርፎች ላይ ጭምር ድርድር እንደሚደረግም አስረድተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት "ይኸን ይኸ እከፍታለሁ፤ ይኸን ደግሞ ለጊዜው ላቆይ እችላለሁ ወይም ቅድመ ሁኔታ ላስቀምጥ እችላለሁ" ብሎ ከሥምምነቱ ፈራሚዎች ይደራደራል። በቴሌኮም እና ፋይናንስ ዘርፎች ተግባራዊ የተደረጉ ማሻሻያዎች ነጻ የንግድ ቀጠናውን ሥራ ለማስጀመር አዎንታዊ እርምጃ እንደሆኑ የሚያስታውሱት አቶ ብሩህ "በእርግጥ ሥምምነቱን ፈርመው ካጸደቁ አገራት አንጻር ትንሽ ዘግይተናል። በርካታ አገራት በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ሥምምነት ውስጥ ንግድ እየጀመሩ ነው" ሲሉ አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ሸቀጦች በንግድ ቀጠናው አማካኝነት በሌሎች ገበያዎች ሲሸጡ አሊያም የሌሎች የሥምምነቱ ፈራሚ አገራት ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ የሚከፈልባቸው ቀረጥ ላይ ዝርዝር ድርድር ማድረግ ያሻል። ኢትዮጵያ ለድርድር በምታቀርበው የሸቀጦች እና አገልግሎቶች የቀረጥ ሥርዓት ላይ "ጥያቄ የሚያነሱ አገራት ወደ ኢትዮጵያ ምርቶቻችንን እንልካለን ብለው የሚያስቡ አገራት ናቸው።

12/07/2023

ብሄራዊ ባንክ እና የኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት ኹሉም የፋይናንስ ተቋማት በ2016 ዓ፣ም ደንበኞቻቸውን ወደ ዲጂታል መታወቂያ እንዲያስገቡ የሚያስችል መርሃ ግብር መቅረጻቸውን ይፋ እድርገዋል። የፋይናንስ ደኅንነትን ለማስጠበቅ "ደንበኛህን በኤሌክትሮኒክ ዘዴ እወቅ" የተሰኘ ሁለተኛ መርሃ ግብር ተግባራዊ እንደሚደረግም ተገልጧል። ሁለተኛው መርሃ ግብር፣ ማንኛውም ሰው በአካል መቅረብ ሳያስፈልገው የፋይናንስ ተቋማት በዲጂታል አማራጭ ብቻ ግለሰቡን ደንበኛ ለማድረግ የሚያስችላቸውና የገንዘብ ማጭበርበርን የሚቀንስ መርሃ ግብር ነው ተብሏል።

27/08/2022

የዴቢት፣ ክሬዲት እና ቅድመ ክፍያ ካርዶች ልዩነት
አሁን ላይ በአገራችን ካርዶችን ለግዢ፣ ለወጪ እንዲሁም በተወሰነ መልኩ ለኦንላይን ክፍያ መጠቀም ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ መምጣቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የካርዶቹም ዓይነት እየጨመረ እንዲሁም የብሔራዊ ባንክ ፈቃድን ተከትሎ ካርዶቹን የመስጠትም ሥራ ከባንኮች በተጨማሪ በሌሎች አካላት ወይም ድርጅቶች ጭምር እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ሆኖም ብዙ ሰዎች በክሬዲት ፣ ዴቢት እና ቅድመ ክፍያ ካርዶች መካከል ያለው መመሳሰልና ልዩነት በግልፅ አይታያቸውም፡፡፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ግልፅ ነው፡፡ እነዚህ ካርዶች ብዙ የሚያመሳስላችው ነገሮች (አገልግሎቱ የሚያበቃበት ቀን፣ የካርድ መለያ ቁጥሩ PAN፣ ሥም፣ የካርድ ሰጪውና የቪዛ ወይም ማስተር ካርድ መለያዎች አንዲሁም አሁን ላይ በተወሰኑት ላይ የኮንታክትለስ ምልክት) በካርዶቹ ላይ በተመሳሳይ መልኩ በመኖራቸው ምክንያት ሲሆን፣ ካርዶቹ ግን መሠረታዊ ልዩነት ያላቸው ናቸው፡፡
የካርዶቹን ተፈጥሮአዊ ልዩነት እንደሚከተለው በዝርዝር እንመለከት፡-
ቅድመ ክፍያ ካርድ
የቅድመ ክፍያ ካርድ የባንክ ሒሳብ መኖር ሳያስፈልግ ወይም ከባንክ ሒሳብ ጋር ሳይገናኝ በዲጂታል ክፍያ ዋሌት (Digital Payment Wallet) አማካኝነት በካርድ ገንዘብ እንዲንቀሳቀስ የሚያስችል ነው፡፡
እነዚህ ካርዶች አብዛኛውን ጊዜ በቪዛ ወይም ማስተር ካርድ የሚደገፉ በመሆናቸው ከአገር ውስጥ በተጨማሪ ዓለም አቀፍ ወይም በውጭ አገርም ሊሠሩ የሚችሉ ናቸው፡፡
የቅድመ ክፍያ ካርዶች አንድ ልዩ የሚያደርጋቸው በገንዘብ ወይም በክፍያ መጠን ላይ ገደብ ያላቸው መሆኑ ሲሆን፣ በካርዶቹ ላይ ያለው ገንዘብ ካለቀ በኋላ እንደገና እስኪጫንባቸው ድረስ መጠቀም አይቻልም፡፡
ለተለያዩ ዓላማ የሚውሉ የቅድመ ክፍያ ካርድ አይነቶች ያሉ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡
1-የቅድመ ክፍያ የሥጦታ ካርዶች
እነዚህ ካርዶች በሥጦታ መልክ ከተለያዩ አካላት ሊገኙ የሚችሉ ሲሆን፣ ካርዶቹ የያዙት የገንዘብ መጠን ካለቀ በኋላ ካርዶቹን መልሶ መጠቀም አይቻልም፡፡
2-የችርቻሮ ቅድመ ክፍያ ካርዶች/Retail Prepaid Cards
እነዚህ ካርዶች ከሥጦታ ካርዶች የተለዩ ሲሆኑ፣ ነዳጅ አቅራቢዎች፣ አየር መንገድ ወይም ሱፐር ማርኬቶች ከባንክ ጋር ወይም ከካርድ ሰጪ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ተጠቃሚዎች ክፍያ ወይም ግብይት በሚፈፅሙበት ወቅት የሽልማት ነጥቦችን ፣ የአየር ማይሎችን (Miles)፣ ቅናሾችን፣ ለመስጠት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡
3-የቅድመ ክፍያ የጉዞ ካርዶች
የቅድመ ክፍያ የጉዞ ካርዶች ወደ ውጭ ጉዞ ለሚያደርጉ ግለሰቦች፣ ትኬትና ቪዛ እንዲሁም የደንበኝነት ሁኔታ ታይቶ በባንኮች የሚሰጡ ሲሆኑ፣ የገንዘቡ መጠን በውጭ ምንዛሬ ተጭኖ በሄዱበት አገር ሆስፒታሎች፣ ሱቆች እንዲሁም ለኦንላይን ክፍያዎች ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡
በካርዶቹ ላይ የተጫነው ገንዘብ ሲያልቅና ተጨማሪ ገንዘብ ከተፈለገ እንደገና መሙላት ይጠይቃል፡፡ እንዲሁም አንዳንድ ካርዶች ፓን ቁጥርን በመጠቀም የተወሰነ ገንዘብ ሊተላለፍባቸው ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡ የአቢሲንያ ባንክ የጉዞ ቅድመ ክፍያ ካርዶች ከተጫነባቸው የመጀመሪያ የገንዘብ መጠን በላይ አስከ 3000 የአሜሪካን ዶላር ድረስ ከሌላ አካል ሊቀበሉ ወይም ሊተላለፍባቸው ይችላል፡፡
4-ለጠቅላላ አገልግሎት የሚያገለግሉ የክፍያና ግዢ ካርዶች
እነዚህ ካርዶች ለማንኛውም ዓይነት የዕለት ተዕለት ግዢና ክፍያዎች የሚያገለግሉ ሲሆን፣ የተጫነባቸው ገንዘብ ሲያልቅ እንደገና እየተሞሉ(Reloadable) ጥቅም ላይ የሚዉሉ ናቸው፡፡ የቅድመ ክፍያ ካርዶች ፣ ወጪዎች ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆኑ ከሌሎች የተለየ ጠቄሜታ አላቸው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት በካርዶቹ ላይ የተቀመጠው ገንዘብ መጠን አንድ ጊዜ ወጪ ከተደረገና ካለቀ፣ አለቀ ማለት ነው፡፡ ጥናቶችም እንደሚሳዩት ብዙ ሰዎች ከጥሬ ገንዘብ ይልቅ በካርዶች ከመጠን በላይ ማውጣት ይቀላቸዋልና፡፡
ዴቢት ካርድ
ዴቢት ካርዶች በአብዛኛው ከተንቀሳቃሽ ሒሳብ ጋር ግንኙ(Link) ሆነው የሚሠሩ ናቸው፡፡ በዚህም በቁጠባ ወይም በተንቀሳቃሽ ሒሳብ ውስጥ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን ያህል ወጪ ማድረግ፣ ግብይቶችን ማካሄድ ወይም ክፍያዎችን መፈፀም ያስችላሉ፡፡ በሌላ አገላለፅ በሒሳብ ውስጥ የሚገኘውን ገንዘብ በካርዶቹ አማካኝነት በቀላሉ ለተፈለገው አላማ መጠቀም ማስቻላቸው ነው፡፡
አሁን ላይ በዴቢት ካርድ ከአቅም በላይ ወይም በሒሳብ ከሚገኘው ገንዘብ መጠን በላይ ማውጣት ከአለመቻሉ ባለፈ፣ ተጨማሪ ወጪ ማድረግ ቢፈለግ እንኳን ተጨማሪ የወጪ ወይም የክፍያ ገንዘብ ማግኘት አይቻልም፡፡ በርግጥ፣ አሁን ላይ አገልግሎቱ ጥቅም ላይ አልዋለም እንጂ፣ አንዳንድ የዴቢት ካርዶች ከኦቨር ድራፍት ፋሲሊቲ ጋር ግንኙ ሆነው ሊሠሩ የሚችሉበትም ሁኔታ ይኖራል፣ ይህ ሲሆን ሒሳብ ውስጥ ከሚገኘው ገንዘብ መጠን በላይ ለመጠቀም ይቻላል፡፡
ክሬዲት ካርድ
ክሬዲት ካርድ በአጭሩ ለግብይት፣ ለሌሎች ክፍያዎች ወይም ወጪዎች የሚሆን ገንዘብን በብድር መልክ ማግኘት የሚቻልበት ሲሆን፣ በካርዱ ለመጠቀም የተፈቀደው የብድር መጠን ወይም የብድር ገደብ ድረስ መገልገል ያስችላል፡፡
የብድር መጠኑን ለማሳደግ፣ ጥሩ የብድር አጠቃቀም ወይም ክሬዲት ካርድን በኃላፊነት በመጠቀም የብድር ደረጃን (Credit Score) ማሻሻል ይፈልጋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ክሬዲት ካርድን ኃላፊነት በጎደለው መልኩ መጠቀም ከልክ በላይ ወጪ ማውጣትን ፣ የብድር መከማቸትን ፣ የብድር ክፍያ መዘግየትን ብሎም የብድር መበላሸትን ሊያሰከትል ይችላል፡፡
በመጨረሻም ከካርዶች ጋር በተገናኘ፣ በተለያዩ አገልግሎት በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ምድቦች በፕርሚየም፣ ፕላቲንየም፣ ጎልድ ወይም መደበኛ መልኩ የተለያዩ ጥቅሞች ያሏቸው ሲሆን፣ የጥቅሞቹ አይነት፣ መጠንና የአገልግሎት ክፍያቸው እንደ ካርድ ሰጪው ባንክ ወይም ድርጅት የሚወሰንና የሚለያይ ነው፡፡

1.3 ሚለዮን የሚጠጉ ተሽከርካሪዎች በመላ ሀገሪቱ አሉ የተባለ ሲሆን ከነዚህም 164,345 መኪኖች የነዳጅ ድጎማው ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል። ይህም ከሚጠበቀው የተጠቃሚ ቁጥር 94 በመቶ ነው።...
05/07/2022

1.3 ሚለዮን የሚጠጉ ተሽከርካሪዎች በመላ ሀገሪቱ አሉ የተባለ ሲሆን ከነዚህም 164,345 መኪኖች የነዳጅ ድጎማው ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል። ይህም ከሚጠበቀው የተጠቃሚ ቁጥር 94 በመቶ ነው። ኢትዮጵያ በአሁን ሰአት 140 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ እዳ ከአለም አቀፍ ነዳጅ አቅራቢዎች አለባት ተብሏል።

28/06/2022

14 ሚሊዮን ዩሮ በጀት የተያዘለት የቡና ልማት ፕሮጀክት ሊጀመር ነው

የቡና ልማትን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ምርታማነቱን ለማሳደግ 14 ሚሊዮን ዮሮ በጀት የተያዘለት “ኢዩ ካፌ” የተሰኘ ፕሮጀክት እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ለአዲስ ማለዳ እንደገለጸው፣ የቡና ልማትን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ምርታማነቱን ለማሳደግ የሚረዳ በአውሮፓ ኅብረት አማካኝነት 14 ሚሊዮን ዮሮ በጀት የተያዘለት “ኢዩ ካፌ” የተሰኘው ፕሮጀክት በሚቀጥለው ዓመት ይጀመራል።

ኘሮጀክቱን ለመጀመር ቅድሚያ መከናወን ያለባቸው የቅድመ ዝግጅት ሂደቶች አሁን ላይ እየተከናወኑ እንደሚገኙ እና በሚቀጥለው ዓመት ከመጀመሪያዎቹ ወራት ጀምሮ ግን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተመላክቷል።
ኘሮጀክቱ በኢትዮጵያ በሚገኙ አምስት ክልሎች ማለትም በኦሮሚያ ክልል፣ በአማራ ክልል፣ በደቡብ ክልል፣ በሲዳማ ክልል፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ዋና ዋና የቡና አብቃይ በሆኑ 28 ወረዳዎች እንደሚተገበር ተነግሯል።
ኘሮጀክቱ ለአምስት ዓመታት ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን፣ ዋናው ዓላማ በተጠቀሱት ጊዜያት ውስጥ በቡና ማልማት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች በየጊዜው ሥልጠና በመስጠት ቴክኖሎጂን ተጠቅመው እንዲሠሩ በማድረግ እና የሚያስፈልጓቸውን ቁሳቁሶች በመደገፍ ረገድ ይሠራል ተብሏል።
ከዚህ አኳያም የቡና ልማቱን በቴክኖሎጂ ከመደገፍ ባሻገር ምርታማነቱን ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንዳለው አዲስ ማለዳ ከባለሥልጣኑ ሰምታለች። በባለሥልጣኑ ስር የሚገኙ የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ሥልጠና እንደወሰዱ እና እነዚህ አካላትም በተጠቀሱት ክልሎች በተለያዩ አካባቢ ለሚገኙ ፍላጎት ላላቸው አርሶ አደሮች ከቴክኖሎጂ ጋር የተያያዘ ሥልጠና መስጠት ጀምረዋል ነው የተባለው።
ሥልጠናው በየወቅቱ እንደሚሰጥ እና አርሶ አደሮቹ የቡና ልማትን በምን ዓይነት መንገድ ተጠቅመው ቢሠሩ የተሻለ ምርት ማግኘት እንደሚችሉ ለማሳየት የሚረዳ ነው ተብሏል።

Tips for uየአንድ ሀገር ሀገራዊ ጠቅላላ ገቢ በዋናነት በሁለት መንገዶች ይለካል፡፡ እነሱም ጠቅላላ በሀገር ውስጥ ያለ የምርት መጠን (GDP ማለትም Gross Domestic Product)...
26/06/2022

Tips for u
የአንድ ሀገር ሀገራዊ ጠቅላላ ገቢ በዋናነት በሁለት መንገዶች ይለካል፡፡ እነሱም ጠቅላላ በሀገር ውስጥ ያለ የምርት መጠን (GDP ማለትም Gross Domestic Product) እና ጠቅላላ የሀገሪቷ ዜጎች የፈጠሩት የገቢ መጠን (GNP ማለትም Gross National Product) ነው፡፡
GDP፡- በአንድ ሀገር ድንበር ክልል ውስጥ በአንድ ዓመት ውስጥ ከኢንቨስትመንት፤ ከመንግስት ጠቅላላ ወጪ፤ ከጠቅላላ ፍጆታ ወጪ እንዲሁም ወደ ውጪ ከሚላክ ጠቅላላ አገልግሎት እና ቁሳቁስ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባውን አገልግሎት እና ቁሳቁስ በመቀነስ የሚገኝ ልዩነትን የሚያሰላ ሲሆን በሀገር ውስጥ የውጪ ዜጎችም ሆኑ የሀገር ውስጥ ዜጎች ያመረቱትን እና የሸጡትን ጠቅላላ ምርት ያጠቃልላል፡፡
GDP= Consumption + Investment + Government Expenditure + (Export-Import)
GNP፡- በሀገር ውስጥ እና በተለያየ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ የአንድ ሀገር ዜጎች ብቻ በማምረት እና አገልግሎት በመስጠት የሚገኝን ገቢ አጠቃሎ የሚያሰላ ነው፡፡ ነገር ግን በውጪ ሀገር ዜጎች የሚመረት ቅሳቁስ እና አገልግሎት ገቢ አይጠቃለልም (ምክንያቱም ወደ ውጪ የሚላክ ገቢ ተብሎ ስለሚታሰብ ነው)፡፡
#ለምሳሌ፡- አንድ ህንዳዊ በኢትዮጲያ አፓርታማ ገንብቶ ቢያከራይ (ለደሞዝ የተከፈለው፤ ለኪራይ የተከፈለው እና ትርፉ) በኢትዮጲያ GDP ላይ ሲመዘገብ (ምክንያቱም ገቢው የተገኘው በኢትዮጲያ መሬት ላይ ስለሆነ) ነገር ግን ባለቤቱ ወደ ህንድ የሚልከው ገቢ/ገንዘብ በኢትዮጲያ GNP ላይ ሳይሆን በህንድ GNP ላይ ነው የሚመዘገበው፡፡
GNP= GDP + Factor payments from abroad - Factor payments to abroad
ያደጉ ሀገራት የGDP እና GNP ልዩነት እያሰሉ የኢኮኖሚ የእድገት ሁኔታቸውን ይመዝናሉ ነገር ግን እንደ ኢትዮጲያ ላሉ ሀገራት GNP በሁሉም የዓለም ሀገራት በዜጎቿ በማምረት እና አገልግሎት በመስጠት የሚገኝን ገቢ አጠቃሎ ማስላት አስቸጋሪ ነው የሚሆነው፡፡ #ለምሳሌ፡- ኢትዮጲያዊያን የሚያገኙትን ገቢ በሚኖሩበት ሀገር ባንክ በማስቀመጠ ወደ ሀገር ቤት የማይልኩ ከሆነ ትክክለኛውን የኢትዮጲያ GNP ማስላት አስቸጋሪ ነው፡፡

Address

Kazanchis, Mulugeta Commercial Building
Addis Ababa

Telephone

+251926066262

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GA Accountancy & Tax Consulting Firm in Eth posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to GA Accountancy & Tax Consulting Firm in Eth:

Share