Woyinshet

Woyinshet just life The need for finance manager arises whenever the oeganizations are in requirement of funds for their operations.

❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤Hulem kemdesetibachew negerochi wust yelijoche fikir❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
02/09/2024

❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤Hulem kemdesetibachew negerochi wust yelijoche fikir❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

08/07/2023
🤱ውዶቼ አንድ ያሣሠበኝን ነገር ላዋያችሁ አንዳንድ ጊዜ ባለማወቅ ልጆቻችን ላይ ምናደርሠው ፆታዊ ተፅኖ አለ:: ለምሣሌ:- 🎀ልጆቻችንን ያለፆታቸው  መጥራት, ማልበስ, መቀባባት የፀጉራቸው ስታ...
10/03/2023

🤱ውዶቼ አንድ ያሣሠበኝን ነገር ላዋያችሁ አንዳንድ ጊዜ ባለማወቅ ልጆቻችን ላይ ምናደርሠው ፆታዊ ተፅኖ አለ:: ለምሣሌ:-
🎀ልጆቻችንን ያለፆታቸው መጥራት, ማልበስ, መቀባባት የፀጉራቸው ስታይል ምናደርገው ነገር በጣም መስተካከል አለበት ይሄ ነገር ፆታዊ ተፅኖ ይባላል ልጅች ያንን ይለምዱና እውነተኛ የማንነታቸውን ፆታ መቀበል ሊያቅታቸው ይችላል:: ይሄ እያደገ ይሄዳል ብዙዎቹን ፆታ እስከመቀየር / ተመሣሣይ ፆታ ጋብቻ የፍቅር ህይወት ሚያደርስ ይሆናል ምክንያቱም ማንነታቸውን መቀበል ስለማይችሉ ስለዚህ እባካችሁ ወላጆች ለጨዋታ ሚደረግ ነገር ለልጆቹ የስነልቦና ተፅኖ ስለሚያመጣ እንደፆታቸው እናሣድጋቸው::
🎀ልጆችን ከንፈራቸውን መሣም:- ከጤንነት አንፃር ስናየው 🌸በጤናቸው ላይ ሚያመጣው ቀውስ ቀላል አይደለም ከባክቴርያ, ከአላርጅክ, ተላላፊ ህመሞች ... ብትችሉ ከአንገት በላይና እጃቸውንም አትሣሙ::
🌸ከስነልቦና አንፃር ልጆች ኖርማል ስለሚመስላቸው ሁሉንም መሣም ይፈልጋሉ::
🎀ሜካኘ :-አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸውን ሜካፕ ሊፒስቲክ ይቀባሉ :-
🌸ከጤናቸው አንፃር , ሜካፕ ኬሚካል አለው ለነሡ ቆዳ ሚስማማ አይደለም የህፃናት ቆዳ በጣም ስስ ነው እንደ አዋቂ አቅም የለውም የመጣውን ሁሉ ለመቋቋም ለዛነው ሣሙናም ቅባትም የህፃናት እያልን ምንገዛው::
🌸እይታ :- ከባህልም ለእይታም ደስ አይልም ህፃናት በራሣቸው ቫዝሊን ባይቀቡ እንኳን ውብ ናቸው::በተጨማሪ አለእድሜያቸው የሠው እይታ ውስጥ እንዲገቡ እያደረግናቸው ነው::
🎀አለባበስ:- ልጅ መልበስ ያለበት የልጅ ልብስ ነው ይመርባቸው, ፅድት ይበሉ ያቅማችንን እናድርግ ::
🌸ለሴቶች ልጆች ወጣ ብሎ የተገላለጠ አናልብስ ሁልጊዜም ቀሚስ ሲለብ ከስር ፖንት ቁምጣ/ታይት ይልበሡ:: ልጆቻችን ከአይናችን አይራቁ ት/ቤት ወይ ምናምነው የራሣቸን ቤተሠብ ጋር ካልሆነ ጊዜው ከፍቶዋል በተጨማሪ ሁለቱንም ፆታ ልጆቻችንን ከኛ ውጭ ማንም ሠዉ ልብሣቸውን መግለጥ እንደሌለበት ልክ እንዳይደለ ማስተማር አለብን::እንደምታውቁት ጊዜው ከፍቶዋል
🌸ወንዶች ልጆቻችንን በተቻለ ኖርማል ሱሪ መምረጥ, ወደላይ ከፍ አድርገው እንዲለብሱ ማስተማር ያስፈልጋል::
🎀የውጩው አለም ያደረገውን በጭፍን አንከተል እነሡ በእውነተኛው አለም ኑሮዋቸው እኛ በፊልም እንደምናየው አይደለም በጣም ይለያል አለባበሣቸው በጣም ስርአት አለው :: ወጣ ያለ ልብስ ሚለብሡና መደበኛ ልብሣቸው የሆነ ሠወች ደግሞ አብዛኛው ልብስ የራሡ ትርጉም አለው:: መጠራሪያም ነው:: ሆሊውድን ሣይሆን ራሣችንን መስለን እንኑር እኛ የራሣችን ማንነትና ባህል ወግ ደንብ ያለን ኩሩ ህዝቦች ነን::
ልጆች የፈጣሪ ስጦታና ከፈጣሪ የተሠጡን የአደራ ንብረቶቻችን ናቸው በጥንቃቄ እንጠብቃቸው
ለሀገራችን ብሎም ለራሣችን ሀገር ተረካቢ መልካም ዜጋን እናፍራ ❤
ፈጣሪ ልጆቻችንን ይጠብቅልን🙏
ስለምታነቡት በጣም አመሠግናለሁ❤ እወዳችሁዋለሁ❤❤❤❤

10/11/2022

ዘመነ ጽጌ (ጽጌ ጾም)
፧፧፧፧
ከአምስቱ የዘመነ መጸው ክፍሎች መካከልም የመጀመሪያው ክፍል ‹ዘመነ ጽጌ› ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህም ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ ቀን ድረስ ያሉትን ፵ ቀናት ያጠቃልላል፡፡ ‹ጽጌ› ቃሉ ‹ጸገየ አበበ› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ትርጕሙም አበባ ማለት ነው፡፡ ‹ዘመነ ጽጌ› ደግሞ ‹የአበባ ወቅት፣ የአበባ ጊዜ፣ የአበባ ዘመን› ማለት ነው፡፡ ይህ ወቅት ዕፀዋት በአበባ የሚያጌጡበት፣ ምድር በአበቦች ኅብረ ቀለማት የምታሸበርቅበት፣ ወንዞች ንጹሕ የሚኾኑበት፣ ጥሩ አየር የሚነፍስበት፣ አዕዋፍ በዝማሬ የሚደሰቱበት፣ እኛም የሰው ልጆች ‹‹አሠርጎካ ለምድር በሥነ ጽጌያት፤ አቤቱ ምድርን በአበቦች ውበት አስጌጥሃት›› እያልን የዘመናት አስገኚ እና ባለቤት የኾነውን ልዑል እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት፤ ከዚህም ባሻገር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ ጋር ከገሊላ ወደ ግብጽ ምድር መሰደዷን የምናስብበት ወቅት ነው፡፡

በተአምረ ማርያም እና በማኅሌተ ጽጌ ተጽፎ እንደሚገኘው ጌታችን በግብጽ ምድር በስደት ሳለ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አድርጓል፡፡ ከእነዚህ መካከልም እናቱን እመቤታችንን የዘለፏትን ትዕማንና ኮቲባ የሚባሉ ሴቶችን ከሰውነት ወደ ውሻነት መቀየሩ፤ ውኃ በጠማቸው ጊዜ ውኃ እያፈለቀ ማጠጣቱና ይህንንም ውኃ ክፉዎች እንዳይጠጡት ማምረሩ፤ ለችግረኞችና ለበሽተኞች ግን ጣፋጭ መጠጥና ፈዋሽ ጠበል ማድረጉ፤ ‹‹የሄሮድስ ጭፍሮች ደርሰው ልጅሽን ሊገድሉብሽ ነው›› ብሎ የዮሴፍ ልጅ ዮሳ እመቤታችንን በማስደንገጡ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ ድንጋይ ኾኖ እንዲቆይ ማዘዙ፤ መንገድ ላይ የተራዳቸው ሽፍታ ሰይፉ በተሰበረች ጊዜ ሰይፉን በተአምራት እንደ ቀድሞው ማደሱ፤ እንደዚሁም የግብጽ ጣዖታትን በአምላክነቱ ቀጥቅጦ ማጥፋቱ ተጠቃሾች ናቸው፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር በተሰደደች ጊዜ የደረሰባትን መከራ በማስታወስ ዘመነ ጽጌን በፈቃዳቸው የሚጾሙ ካህናትና ምእመናን ብዙዎች ናቸው፡፡ ኾኖም ግን የጽጌ ጾም #የፈቃድ ጾም እንጂ ከሰባቱ አጽዋማት ጋር የሚመደብ ስላልኾነ ጽጌን የማይጾሙ አባቶች #ካህናትንና ምእመናንን #ልንነቅፋቸው አይገባም፡፡ የጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ በሄሮድስ እጅ በግፍ የተሠዉ ሕፃናት በረከት አይለየን፡፡ አምላካችን በአበባ የሚመሰለው ሰውነታችን የጽድቅ ፍሬን ሳያፈራ እና ንስሐ ሳንገባ በሞት እንዳንወሰድ መልካም ፈቃዱ ይኹንልን፡፡
፧ሙሉውን ጽሑፍ ማህበረ ቅዱሳን ታገኙታላችሁ።

ለምጾሙ መልካምና የበረከት ጾም ይሁንላችሁ ።

ካነበብኩት ላካፍላቹ:በህይወት ውስጥ ትልቁን ለውጥ የሚፈጥሩት ትናንሽ ነገሮች ናቸው፤ ዝሆን ገጭቶት የሞተ ሰው ታውቃላችሁ? በትንሿ የወባ ትንኝ ግን ተነክሶ የሞተ ነፍ ነው። ታዲያ እንደ ቀላ...
27/10/2022

ካነበብኩት ላካፍላቹ:

በህይወት ውስጥ ትልቁን ለውጥ የሚፈጥሩት ትናንሽ ነገሮች ናቸው፤ ዝሆን ገጭቶት የሞተ ሰው ታውቃላችሁ? በትንሿ የወባ ትንኝ ግን ተነክሶ የሞተ ነፍ ነው። ታዲያ እንደ ቀላል የምታየው ቸልተኛ ፀባይህ ምን እንደሚያሳጣህ የምታውቀው ዘግይተህ ነው።

በቀን ውስጥ አደርጋለው ያልከውን ሳታደርግ ቀጣዩን ቀን አትጀምር! አለዛ ከነገ ላይ እየሰረክ ነው፤ ስንፍናን ማሸነፍ ቀንህን ከማሳመር ነው የሚጀምረው።

👏👏👏👏😊😊😊😊😊😊😊😊
መልካም አዳር ተመኘሁሁላቹ!!!?

03/08/2022

🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን !!!🙏

✍️ታገሱ!

የሰዎች ሁኔታና የነገሮች እልህ አስጨራሽነት እጅግ ፈታኝ የሆነበት አንድ ሰው እንዲህ ሲል ጸለዬ፤ “ፈጣሪ ሆይ እባክህን ትእግስትን ስጠኝ፤ ይህንን የለመንኩህን ትእግስት ደግሞ አሁኑኑ እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ” ይህ ሰው ፈጣሪ ትእግስትን እስከሚሰጠውም መታገስ አልቻለም፡፡

ትእግስትን እንማረዋለን እንጂ አንቀበለውም፡፡ ትእግስትን የመማሪያው ብቸኛ መንገድ ደግሞ እልህ አስጨራሽ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ በማለፍና አስቸጋሪ ሰዎችን ችሎ መንገድን በመቀጠል ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ስንጀምር የሚፈታተነን ነገር ቀስ በቀስ እየደከመ ይሄዳል፡፡

አያችሁ እኛ አመለካከታችንን በመለወጥ በልጠንና ተሽለን እንገኛለን እንጂ ትእግስት አስጨራሽ ሁኔታዎችና ሰዎች እስከወዲያኛው ድረስ ከአካባቢያችን አይጠፉም፡፡ ትእግስት ባጣንና እልኸኛ በሆንን ቁጥር ውስጣችን ያለውን የትእግስት መጠን አለአግባብ ስለምናቃጥለው ቀስ በቀስ በጥቃቅን ሁኔታዎችና አመላከከታቸው እጅግ አናሳ በሆኑ ሰዎችም ሳይቀር መፈተን እንጀምራለን፡፡ ሁሌም መታገስን ምረጡ!
🙌🙌

11/06/2022
20/05/2022
17/05/2022

Address

Robit
Addis Ababa

Telephone

99765439444

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Woyinshet posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share