አፍማ የአደጋ መከላከያና የደህንነት መገልገያ እቃዎች ጅምላ ንግድ AFMA safety & security

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • አፍማ የአደጋ መከላከያና የደህንነት መገልገያ እቃዎች ጅምላ ንግድ AFMA safety & security

አፍማ የአደጋ መከላከያና የደህንነት መገልገያ እቃዎች ጅምላ ንግድ AFMA safety & security our company supply & install any safety and security equipments. also refill fire extinguishes. call

19/05/2026
የሃገሪቱ  Import & export  ደም ስር የሆነው የኢትዮጲያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የእሳት አደጋ መከላከል ስራውን ሙሉ በሙሉ በኮንትራት ለድርጅታችን ሰጥቷል። ሃላፊነታችንን ለ...
15/05/2026

የሃገሪቱ Import & export ደም ስር የሆነው የኢትዮጲያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የእሳት አደጋ መከላከል ስራውን ሙሉ በሙሉ በኮንትራት ለድርጅታችን ሰጥቷል።
ሃላፊነታችንን ለመወጣት እኛም በትጋት እየሰራን እንገኛለን።

Check out afma fire sefty and security’s video.

15/05/2026

ከማናቸውም አደጋ አስቀድመው ይጠንቀቁ!

ህይወትዎን እና ንብረትዎን መጠበቅ የሚጀምረው በጥንቃቄ ነው! አደጋዎች ድንገተኛ ቢሆኑም፣ አብዛኞቹን ግን በቅድመ ጥንቃቄ መከላከል ይቻላል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከማናቸውም አደጋ አስቀድሞ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ያሳስባል፦

🏡 በቤትዎ ውስጥ የሚደርሱ አደጋዎች፦

👉የኤሌክትሪክ ደህንነት፦ ያረጁ ገመዶችን ይቀይሩ፣ ሶኬቶችን ከልክ በላይ አይጫኑ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎችዎን ከተጠቀሙ በኋላ ይንቀሉ።

👉የእሳት ምንጮች፦ ስቶፍ፣ ምድጃ እና ምጣድን ከረጅም ሙቀት በኋላ ያጥፉ፣ የጋዝ ምድጃዎችን ከእሳት አደጋ ነጻ ያድርጉ።

👉ሻማና ክብሪት፦ የተለኮሱ ሻማዎችን ያለ ክትትል አይተዉ፣ ክብሪትና ላይተርን ህፃናት በማይደርሱበት ቦታ ያድርጉ።

👉የሲጋራ ጫፎችን ከማጥፋትዎ በፊት በደንብ ማጥፋትዎን ያረጋግጡ።

👉የነዳጅ እቃዎች፦ ቤንዚን፣ ጋዝ እና ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮችን ከእሳት ምንጮች ርቀው እና ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ያከማቹ።

🚧 ከቤት ውጭ እና በአካባቢዎ የሚደርሱ አደጋዎች፦

👉የመንገድ ደህንነት፦ በእግረኛ መንገድ ሲጓዙ መጠንቀቅ፣ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ደንቦችን ማክበር።

👉የህዝብ ስብሰባ ቦታዎች፦ በአደባባይ እና ብዙ ሰው በሚሰበሰብበት ቦታ የጥንቃቄ ደንቦችን መከተል፣ የአደጋ መውጫ መንገዶችን ማወቅ።

👉የተፈጥሮ አደጋዎች፦ ከባድ ዝናብ፣ ጎርፍ ወይም የመሬት መንቀጥቀጥ በሚከሰትበት ጊዜ የአደጋ ጊዜ መመሪያዎችን መከተል።

የእርስዎ አንድ ጥንቃቄ፣ የብዙዎችን ህይወት እና ንብረት ያድናል!

አደጋ ሲያጋጥም፣ ሳይዘገዩ ለ939 ይደውሉ!
#ጥንቃቄ #ደህንነት #939

13/05/2026

Watch, follow, and discover more trending content.

13/05/2026

የኢትዮጵያ እሳትና ሌሎች ቅጽበታዊ አደጋዎች አገልግሎት ተቋቋመ

​በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ላይ በወጣው ደንብ ቁጥር ፭፻፺፩/፪ሺ፲፰ (591/2026) መሰረት፣ "የኢትዮጵያ እሳትና ሌሎች ቅጽበታዊ አደጋዎች አገልግሎት" በይፋ ተቋቁሟል።

👉​የደንቡ ስም፡ የኢትዮጵያ እሳትና ሌሎች ቅጽበታዊ አደጋዎች አገልግሎት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ።

👉​የወጣበት ቀን፡ ሚያዝያ ፳፮ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ.ም (May 4, 2026)።

👉​ሕጋዊ መሠረት፡ ይህ ደንብ የወጣው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሲሆን፣ የኢፌዴሪ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፲፪፻፷፫/፪ሺ፲፬ (1263/2021) አንቀጽ ፻፫ መሠረት ነው።

ለብዙ ዓመት የታገልነልት ህግ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀደቀ። እንኳን ደስ አለን።
13/05/2026

ለብዙ ዓመት የታገልነልት ህግ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀደቀ። እንኳን ደስ አለን።

ማንኛውም የእሳት ማጥፍያ ለማዘዝ 0925243301
29/03/2026

ማንኛውም የእሳት ማጥፍያ ለማዘዝ 0925243301

Check out afma fire sefty and security’s video.

08/01/2026

እሳትን በማጥፋት ግንዛቤ ይኑሮት! ትንሽ መሳሪያ ሕይወትን ከእሳት አደጋ ያድናል!

በመስሪያ ቦታዎች ት/ቤቶች እና እንኳን በቤት ውስጥም የእሳት አጥፊ ከቀላሉ ነገር ግን እጅግ ውጤታማ የደህንነት መሳሪያዎች አንዱ ነው፤ ብዙ ጊዜ ግን እንደ ተራ ነገር እንመለከተዋለን። ምንም እንኳን እንዳንጠቀምበት እንመኛለን፣ ነገር ግን ስለ አጠቃቀሙ መረዳት አነስተኛ ክስተትን ከታላቅ አደጋ ለመለየት ያግዛል።

🧯 የእሳት አጥፊ ምንድን ነው?
የእሳት አጥፊ በአደጋ ጊዜ ትንሽ እሳቶችን ለመቆጣጠር ወይም ለማጥፋት የተነደፈ ተንቀሳቃሽ መሳሪያ ነው። በቅጥር ላይ የተሰቀለ ቀይ ሲሊንደር ብቻ አይደለም ። ከእሳት አደጋ የመጀመሪያ መከላከያ መሳሪያ ነው።

🧯 የእሳት አጥፊዎች አይነቶች
• የውሃ እሳት አጥፊ — ለእንጨት፣ ወረቀት እና ተመሳሳይ ነገሮች
• የፎም እሳት አጥፊ — ለነዳጅ ፈሳሾች (flammable liquids)
• ደረቅ ኬሚካል እሳት አጥፊ — በብዙ ቦታ የሚጠቀምና ተግባራዊ
• CO₂ እሳት አጥፊ — ለኤሌክትሪክ እሳቶች በጣም ተስማሚ

🧯 እንዴት ይጠቀማል? — የPASS ቴክኒክ
ይህን ቀላል አጭር ቃል አስታውሱ — PASS፦
• P – Pull ፒኑን አውጡ
• A – Aim ወደ እሳቱ መሠረት አነጣጥሩ
• S – Squeeze መያዣውን ጫኑ
• S – Sweep ከግራ ወደ ቀኝ እያንቀሳቀሱ እረጩ

🧯መቼ መጠቀም አለብዎት?
እሳቱ ትንሽና መቆጣጠር የሚቻል ሲሆን ብቻ የእሳት አጥፊ ይጠቀሙ። በፍጥነት እየተስፋፋ ከሆነ ግን፣ ወዲያውኑ ይውጡ እና የአደጋ አገልግሎትን #939ይደውሉ።

🧯ጥገና አስፈላጊ ነው
የእሳት አጥፊዎች በየዓመቱ መመርመር እና እንደ አስፈላጊነቱ መጠገን አለባቸው (ብዙውን ጊዜ ከ5–12 ዓመት ውስጥ)። የግፊት መለኪያው (pressure gauge) ሁልጊዜ ዝግጁ መሆኑን ያረጋግጣል።

🧯 ቦታ መምረጥ ወሳኝ ነው
የእሳት አጥፊዎች በቀላሉ የሚደረሱና የሚታዩ ቦታዎች ላይ ፥ በተለይ ከመውጫ በአቅራቢያ፣ በኩሽና፣ በወርክሾፕ፣ እና ቢሮዎች — መቀመጥ አለባቸው። የእሳት ደህንነት ህግን መከተል ብቻ አይደለም ፤ ኃላፊነት ነው። ትክክለኛው ለማጥፋት መኖር አለበት፣ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ማወቅ አለቦት፣ እና በደንብ መጠገን ሕይወት ሊያድን ይችላል።

❓ልብ አድርጉ አስታውሱ በዓል እያከበሩ ነው። የቀሮት ነገር እሳት ማጥፊያ በመስሪያ ቦታዎ ወይም በቤትዎ የእሳት አጥፊዎች በትክክለኛ ቦታ ተቀምጠዋልን? እንዴት መጠቀም እንደሚቻልስ ያውቃሉን?

✨ ሁሌም ደህና ይሁኑልን። ደህንነቱ የተጠበቀ ማኅበረሰብ በሰላም ወቶ በሰላም ይገባል። ራሱን፣ ቤተሰቡን ከሞትና ከንብረት መጥፋት ይታደጋል። ከእሳት አደጋ ይህን ቤተሰባዊ፣ ወዳጃዊ መልእክት ለእርሶ ሰዷል። #አደራ #አደራ #አደራ
፣ ፣ ።








🙏መልካም የገና ዋዜማ ይሁንሎት🙏

🤳ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች 🤳 #በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ! ይደውሉ!
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የኮሚሽኑን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

Address

Kality Near To Sheger Tower
Addis Ababa

Telephone

+251925243301

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አፍማ የአደጋ መከላከያና የደህንነት መገልገያ እቃዎች ጅምላ ንግድ AFMA safety & security posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አፍማ የአደጋ መከላከያና የደህንነት መገልገያ እቃዎች ጅምላ ንግድ AFMA safety & security:

Share