Ethiopian Law Business and Investment Consultancy and Information

Ethiopian Law Business and Investment Consultancy and Information የሕግ እና ቢዝነስ ጉዳዩች ቀለል ባለ መልኩ የሚቀርብበት

24/08/2022

#አስቸኳይ

በአሁን ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጨማሪ አሃዶችን የመፍጠር ቴክኖሎጂዎች (Blockchain technologies) ላይ የተመሰረቱ የክሪፕቶ ምርቶችና አገልግሎቶች ሁኔታ በመስፋፋት እና ጥቅም ላይ በመዋል ላይ ይገኛሉ፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ የክሪፕቶግራፊ ውጤት/ምርትንና አገልግሎትን በተመለከተ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 808/06 አንቀጽ 6 (9) በተሰጠው ስልጣን መሰረት " የክሪፕቶ ምርትና ዝውውርን የመቆጣጠር እና አስፈላጊውን መስፈርት ማውጣትና የአጠቃቀም ስርዓት መዘርጋት " ሃላፊነት ተሰጥቶታል።

በዚህም ዘርፉን በአግባቡ ለመግራት ይቻል ዘንድ ፦የክሪፕቶ ምርት፤ አገልግሎት፣ ዝውውርና ማይኒንግን በተመለከተ ስራዎችን የሚያከናውኑ እና መምዝገብ ለሚፈልጉ ወይም ለመመዝገብ ጠይቀው ሂደት ላይ ያሉ በአስተዳድሩ ድረ-ገጽ በተቀመጠው ቅጽ መስረት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እንዲመዘገቡ አስተዳደሩ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ይህንን ተግባራዊ በማያደርጉ እና በዚህ ስራ ያለምዝገባ ተሰማርተው በሚገኙ አካላት ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።

ለተጨማሪ መረጃ የአስተዳደሩን ድረ-ገጽ www.insa.gov.et/Crypto ወይም https://crypto.insa.gov.et መጎብኘት ይቻላል ተብሏል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የሀገራችንን የኢንፎርሜሽንና የኢንፎርሜሽን መሰረተልማቶች ከጥቃት በመከላከል ብሔራዊ ጥቅሞችን እንዲያስጠብቅ በሚል ዓላማ ለመጀ...

ለሽያጭ የቀረበ 76% ያለቀ 200 ካ.ሜ G+3  ህንፃ ለመኖርያም ሆነ ለንግድ ምቹ የሆነ፣ በጥራት የተሰራ፣ ውሀና መብራት ያለው አድራሻ:- ፉሪ ዳርፉር ሰፈርባቡር ተርሚናሉ አካባቢ ወደ ጋር...
20/05/2022

ለሽያጭ የቀረበ 76% ያለቀ 200 ካ.ሜ G+3 ህንፃ ለመኖርያም ሆነ ለንግድ ምቹ የሆነ፣ በጥራት የተሰራ፣ ውሀና መብራት ያለው
አድራሻ:- ፉሪ ዳርፉር ሰፈር
ባቡር ተርሚናሉ አካባቢ ወደ ጋርመንት ከሚወስደው መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ
ፈጥነው ይደውሉ +251911282490

ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኮንፈረንስ በኢትዮጲያ ሊካሄድ ነውበኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ዓለም አቀፉ የቴሌኮም ኮንፈረንስ  ለስኬታማነቱ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ  ...
02/10/2021

ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኮንፈረንስ በኢትዮጲያ ሊካሄድ ነው

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ዓለም አቀፉ የቴሌኮም ኮንፈረንስ ለስኬታማነቱ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለፀ
*******************
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ዓለም አቀፉ የቴሌኮም ኮንፈረንስ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካንም የሚወክል በመሆኑ ለስኬታማነቱ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ(ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

የአለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ልማት ጉባኤ አዘጋጅ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ኮሜቴ ዝግጅቱን የተመለከተ ስብባውን አካሂዷል።

በአፍሪካ ለመጀሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ኮሚቴው አንስቷል።

የብሄራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኮንፈረንስ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካንም የሚወክል በመሆኑ ለስኬቱ በትኩረት እየሰራን ነው ብለዋል።

ከተለያዩ የኢትዮጵያ ተቋማት የተዋቀረው የዓለም አቀፉ የቴሌኮም ልማት ጉባኤ አዘጋጅ ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ኮሚቴ ዝግጅቱን በበላይነት የሚመራ ሲሆን ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ 11 ኮሚቴዎችንም ያስተባብራል።

የዓለም አቀፉ የቴሌኮም ልማት ጉባኤ በየአራት ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን 8ኛው ጉባኤ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከግንቦት 27፣2014 ጀምሮ እንደሚካድ ሚ/ር መስሪያ ቤቱ አሳውቋል።

20/09/2021

በዚህ ቻናል የሚቀርቡ ትምህርትና መረጃዎች ጠቃሚ ናቸው ብለው ካመኑ ወዳጅ ዘመዶቾን በመጋበዝ እንዲጠቀሙ ያድርጉ።

የኢትዮጲያ የቴሌኮም ገበያ በከፍተኛ ዶላር የአለም አቀፍ ጥምረት ለኢትዮጲያ ለተባለ ድርጅት ፈቃድ በመስጠት ተከፍቷል።
10/06/2021

የኢትዮጲያ የቴሌኮም ገበያ በከፍተኛ ዶላር የአለም አቀፍ ጥምረት ለኢትዮጲያ ለተባለ ድርጅት ፈቃድ በመስጠት ተከፍቷል።

በኢትዮጵያ ከኢትዮ ቴሌኮም በተጨማሪ የቴሌኮም አገልግሎቶችን ለመስጠት በወጣው ጨረታ 850 ሚሊዮን ዶላር በማቅረብ ያሸነፈው ዓለም አቀፍ ጥምረት ለኢትዮጵያ የተባለው የአገልግሎት ሰጪዎ....

የገንዘብ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችና ቀጠናዊ ደህንነት ዙሪያ ከኢጋድ ዋና ፀሃፊ ጋር ተወያዩአዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ ...
17/03/2021

የገንዘብ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችና ቀጠናዊ ደህንነት ዙሪያ ከኢጋድ ዋና ፀሃፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በአባል ሃገራቱ ውስጥ ማሻሻያዎችን እና ተቋማዊ አቅምን ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያዩ፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ከኢጋድ ዋና ፀሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሞች እና የአባል ሃገራቱን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያይተዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት በቀጠናው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና በደህንነት ጉዳዮች ላይ ትስስርን በሚያጠናክር መልኩ ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ማጎልበት አስፈላጊ ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡
ትብብሩ ለሁሉም አባል ሃገራት ተጠቃሚነትና በተለይም ለአካባቢያዊ ሰላምና ደህንነት ወሳኝ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል፡፡
የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው የኢጋድን ፕሮግራሞች በአግባቡ ለመተግበር ተቋማዊ አቅምን መገንባት ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
አያይዘውም ተቋሙ ለቀጠናው እድገትና መረጋጋት ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት መስራቱን ይቀጥላልም ብለዋል፡፡

https://www.fanabc.com

ሁለት የቢራ ፋብሪካዎች የዋጋ ጭማሪ በማድረጋቸው እርምጃ ተወሰደባቸው።መንግስት ከዳቦና ቢራ ለየትኛው ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት በማስተዋል እርምጃ ቢወስድ። https://www.facebook....
10/03/2021

ሁለት የቢራ ፋብሪካዎች የዋጋ ጭማሪ በማድረጋቸው እርምጃ ተወሰደባቸው።

መንግስት ከዳቦና ቢራ ለየትኛው ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት በማስተዋል እርምጃ ቢወስድ።

https://www.facebook.com/123960474361367/posts/3835631303194247/?app=fbl

የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ሁለት ኢንዱስትሪዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ሁለት የቢራ ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን በዓለም ዓቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተለያዩ የድጋፍ ማዕቀፎችን ዘርግቶ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

ሆኖም የማምረቻ ተቋማት አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል ሲሉ የጥራት የንግድ አሰራርና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ እሸቴ አስፋው ተናግረዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ በተደረገ ክትትል ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ አድርገው በተገኙ ሁለት የቢራ ፋብሪካዎች ላይ የማሸግ እርምጃ መወሰዱን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት የቢዝነስ ዕቅድ ማዘጋጀት እንደነበረባቸውም ተገልጿል፡፡

በዚህም የራሳቸውን የትርፍ ህዳግ ለማስፋት ሲሉ እንደፈለጉ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ ተገቢነት የሌለው እና ወንጀል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አቶ እሸቴ ሁሉም የማምረቻ ተቋማት እንደዚህ ያለ ተግባር ከመፈጸም መቆጠብ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

በቀጣይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሰል ስርዓት አልበኝነትን ለመቆጣጠር የቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አክለው መግለጻቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶች
02/02/2021

የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶች

Address

Addis Ababa

Telephone

+251940354290

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Law Business and Investment Consultancy and Information posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share