Ethio-Terit Credit Societies

Ethio-Terit Credit Societies አልመው ይቆጥቡ አቅደው ይበደሩ! Kaayyoon qusadhaa, karooraan liqeeffadhaa! Save purposely, borrow strategically! For Details:-
0957073701/0957076716
or
Short code:- 9124

28/05/2026
ከመኪና ብድር እስከ ግብርና ብድር እንሰጣለን፤ ከደሞዝ ዋስትና እስከ ቤት ካርታ ድረስ የተለያዩ የብድር ዋስትና አይነቶችም አሉን። ገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ የሚገኘው ዋና መስሪያ ቤታችንን ...
28/05/2026

ከመኪና ብድር እስከ ግብርና ብድር እንሰጣለን፤

ከደሞዝ ዋስትና እስከ ቤት ካርታ ድረስ የተለያዩ የብድር ዋስትና አይነቶችም አሉን።

ገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ የሚገኘው ዋና መስሪያ ቤታችንን ጨምሮ ከመርካቶ እስከ አምቦ፤ ከሳሪስ እስከ ጎሮ፤ ከፉሪ እስከ አዳማ እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች ባሉን 11 ቅርንጫፎች እንጠብቃችኋለን።

9124 ላይ ወይም 0957 07 37 01 እንዲሁም 0957 07 67 16 ላይ ደውሉልን።

ኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መ/ኅ/ስ/ማ

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ በድምቀት ከሚከበሩ ኃይማኖታዊ በዓላት መካከል የኢድ አል አድሃ በዓል ዋነኛው ነው። ይህ ታላቅ ኃይማኖታዊ በዓል፣ በመላው ዓለም በሚገኙ የእምነቱ ...
27/05/2026

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ በድምቀት ከሚከበሩ ኃይማኖታዊ በዓላት መካከል የኢድ አል አድሃ በዓል ዋነኛው ነው።

ይህ ታላቅ ኃይማኖታዊ በዓል፣ በመላው ዓለም በሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ይከበራል።

የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ዘንድሮ ለ1,447ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን ኢብራሂም አንድያ ልጃቸው ኢስማኤልን በአላህ ትዕዛዝ ለመስዋዕትነት ማቅረባቸውን በማሰብ የሚከበር እንደሆነ የእምነቱ አስተምህሮ ያስረዳል።

ኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበርም ለዚህ የታማኝነትና የታዛዥነት መገለጫ ለሆነው ኃይማኖታዊ በዓል መላውን የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ይወዳል፡፡

በዚህ አጋጣሚም የሸሪዓ ህግጋቱን የጠበቁ የተሟሉ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ አገልግሎቶችን እየሰጠ መሆኑን ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

እናንተም ዱኒያ የተሰኘውን ከወለድ ነጻ የፋይናንስ አገልግሎታችንን እንድትጠቀሙ እየጋበዝን
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞታችንን እንገልጻለን፡፡

የበለጠ መረጃ ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመራችን 9124 ላይ ወይም በመደበኛ ስልክ ቁጥሮቻችን 0957 07 37 01 እንዲሁም 0957 07 67 16 ላይ ይደውሉልን፡፡

አልመው ይቆጥቡ አቅደው ይበደሩ!

ኢትዮ-ጥሪት ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር

የድርጅቶች ስኬት የሚወሰነው በሚሰጡት መሰረታዊ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ሰራተኛ ዘወትር ወደ ስራ ቦታው ይዞት በሚመጣው ውስጣዊ የስራ ተነሳሽነትና  አቅም ጭምር መሆኑ ተነግሯል፡፡አ...
25/05/2026

የድርጅቶች ስኬት የሚወሰነው በሚሰጡት መሰረታዊ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ሰራተኛ ዘወትር ወደ ስራ ቦታው ይዞት በሚመጣው ውስጣዊ የስራ ተነሳሽነትና አቅም ጭምር መሆኑ ተነግሯል፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17/2018 ዓ.ም

ከልብ እና አዕምሮ አሰራር ጋር በተገናኘ ለሰራተኞችም ሆነ ለኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ድንቅ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችል ስልጠና በዛሬው እለት ተሰጥቷል፡፡

ዘወትር ሰኞ ማለዳ ሲሰጥ የቆየው የኢትዮ ጥሪት የCEO የጥበብ ምክር ሳምንታዊ ስልጠና ዛሬም ሲቀጥል ሰዎች እንዴት አዕምሮና ልባቸውን በአንድነት አቀናጅተው መጠቀም ይችላሉ? ይህስ እንዴት ባለ መልኩ ይጠቅማል? በሚሉት ሀሳቦች ላይ ትኩረቱን አድርጓል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የማህበሩ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ እንዳሻው ተገኘ
ብዙ ሰዎች ስራዎቻቸውን የሚሰሩት በተለመደው የስኬት መንገድ መሆኑን አንስተው ይህም በአዕምሯዊ ዕውቀት ላይ ብቻ የተመሰረተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን የሰዎች አቅም ውስጣዊ ሰላም እና የስራ ተነሳሽነት የሚወሰነው በልብና አዕምሮ የአንድነት ቅንጅት ደረጃ ወይም ስለ አንድ ነገር በተመሳሳይ ሰዓት ማሰብ በመቻላቸው እንደሆነ ሳይንሳዊ ጥናቶች ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል፡፡

የዕለቱ ስልጠና ዋና ዓላማም ሰራተኞች ጥልቅ የሆነ ውስጣዊ ሰላም ኖሯቸው የላቀ የደንበኞች አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ የአባላትን እርካታ መጨመር እና የማህበሩን ህልም ማሳካት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው ለማህበሩ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ሰው ህይወት ትልቅ አበርክቶ አለው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው ሰዎች ስኬታማ ለመሆን የልብና አዕምሮ አንድነታቸው ላይ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት፡፡

አቶ እንዳሻው አክለውም የልብ እና አዕምሮን ቅንጅት ለማዳበር የሚጠቅሙ አራት ዋና ዋና ልባዊ ምሶሶዎች መኖራቸውን ጠቅሰው እነኚህም ምስጋና፣ አድናቆት፣ ርህራሄ እና ፍቅር መሆናቸውን ዘርዝረዋል፡፡

እነዚህ ከድርጅትም ሆነ ከግለሰብ ስኬት አንጻር ጉልህ ሚና የሚጫወቱት ነጥቦች ታዲያ የልብና የአዕምሮ አሰራር ቅንጅትን በማጎልበት ከሰዎች ጋር በሚኖረን ተግባቦት ላይም ታላቅ አበርክቶ ያላቸው መሆኑ ነው በስልጠናው ላይ የተነገረው፡፡

ይህ የሚሆነው ደግሞ የልብ ኃይሎች የሚሰኙት አራቱ ምሶሶዎች ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው በቀላሉ የመጋባት አቅም ያላቸው በመሆኑ ነው በተባለበት በዚህ ስልጠና ላይ የዚህን ውስጣዊ ኃይላችንን ወሳኝነት ተረድተን በአግባቡ ልንጠቀምበት እንደሚገባ ምክር ተሰጥቶበታል፡፡

51ኛው ዙር የኢትዮ-ጥሪት ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ስራ ማህበር የአዳዲስ አባላት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15/2018 ዓ.ምበ51ኛ ዙር ቀጥሎ በተካሄደው የ...
25/05/2026

51ኛው ዙር የኢትዮ-ጥሪት ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ስራ ማህበር የአዳዲስ አባላት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15/2018 ዓ.ም

በ51ኛ ዙር ቀጥሎ በተካሄደው የኢትዮ ጥሪት የአዳዲስ አባላት ስልጠና ላይ እንደተለመደው የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ከነዚህ ጥያቄዎች መካከልም ብድር ለመበደር 6 ወር እየቆጠቡ መጠበቅ ግዴታ ነው ወይ የሚለው ጥያቄ አንዱ ነበር፡፡

እንዲሁም ከማህበሩ የተገዛ እጣ ወይም አክሲዮንን እንደ ዋስትና በማስያዝ ብድር መበደር መቻል አለመቻሉን የተመለከተ ጥያቄም እንዲሁ ተነስቷል፡፡

የእለቱን ስልጠና የሰጡት የማህበሩ የስልጠናና አቅም ግንባታ ክፍል ኃላፊ አቶ ተሾመ በቀለ በመጀመሪያ ማህበሩ የሚሰጣቸውን የአገልግሎት አይነቶች እንዲሁም የአባላት መብትና ግዴታዎችን ብሎም ተያያዥ ጉዳዮችን ለአዳዲስ አባላቱ አብራርተዋል፡፡

ቁጠባ፣ ብድርና የቢዝነስ ማማከር በዋነኝነት በማህበሩ የሚሰጡ አገልግሎቶች መሆናቸውን የጠቀሱት ኃላፊው ማህበሩ የተለያዩ የቁጠባና ብድር አይነቶች እንዳሉትና እነዚህም ለአሰራር ምቹ እንዲሆኑ መቀመጣቸውን አስረድተዋል፡፡

ከዚህ አኳያ አባላት በማህበሩ ውስጥ 6 ወር እየቆጠቡ መቆየት ግዴታቸው አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከማህበሩ የተገዛ እጣ ወይም አክሲዮንን እንደ ዋስትና በማስያዝ መበደር መቻል አለመቻልን በሚመለከተ ለተነሳው ጥያቄ ደግሞ የአክሲዮን ድርሻ ለትርፍ ክፍፍል የሚውል እንጂ ለዋስትና የሚያዝ አለመሆኑ ተጠቅሶ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

ነገር ግን አንድ አባል የሌላ ባለአክሲዮንን 90 በመቶ ያህል ድርሻ እንደዋስትና በመጠቀም መበደር የሚችልበት አማራጭ ያለው መሆኑም ነው የተብራራው፡፡

በመጨረሻም የኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር የስልጠናና አቅም ግንባታ ክፍል ኃላፊው አቶ ተሾመ በቀለ አባላት የወሰዱትን ስልጠና ወደ ተግባር ለውጠው በሚገባ እንዲጠቀሙበት በማሳሰብ መሰሉ ስልጠና በየሳምንቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

በኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ውስጥ ወጥነት ያለው የኦፕሬሽን ስራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር ለቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ለ2 ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል፡፡  አዲስ...
22/05/2026

በኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ውስጥ ወጥነት ያለው የኦፕሬሽን ስራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር ለቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ለ2 ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተሞች እንዲሁም በክልል ከተሞች ከሚገኙ 11 ቅርንጫፎች ለተውጣጡ 24 ያህል የኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆችና ኦፊሰሮች ለ2 ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ሲጠናቀቅ የአባላት ቁጠባ አሰባሰብን ቀልጣፋ ማድረግ እንደሚገባ ተነግሮበታል፡፡

ወጥነት ያለው የኦፕሬሽን ስራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር አልሞ በተዘጋጀው በዚህ ስልጠና ላይ የላቀ የደንበኞች አገልግሎት እንዲሁም ዘመናዊ የቁጠባና ብድር ሥርዓትን የሚያጎለብቱ ሀሳቦችም ተነስተውበታል፡፡

የዛሬው የመጨረሻ ቀን ስልጠና እነዚህን ውጥኖች ለማሳካት በሚያግዙ የተለያዩ ሀሳቦች ላይ አተኩሮ በማህበሩ የቢዝነስ ዴቨሎፕመንት እና ማርኬቲንግ ም/ክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አትክልት ኃይሉ ፣ በማህበሩ የቅርንጫፍ ዳይሬክተር አቶ አበበ ጋዲሳ እና በማዕከላዊ ፋይናንስ ክፍል ኃላፊ ረ/ፕሮፌሰር አስቴር ከተማ ተሰጥቷል።

ማህበሩ በሁሉም ረገድ የተሻለ አፈፃፀም እንዲያስመዘግብ እና እንዲያድግ የቅርንጫፎች ሚና ላቅ ያለ መሆኑም የስራ ኃላፊዎቹ አንስተዋል።

በቅርንጫፎች ለሚመጡ አባላት የላቀ የደንበኞች አገልግሎት በመስጠት ፍላጎታቸውን ማሟላት እንደሚገባ ያሳሰቡት ኃላፊዎቹ ስልጠናው በአግባቡ ከተተገበረ የተሻለ ለውጥ እንደሚያመጣም ጨምረው አስረድተዋል።

በመሆኑም የተለያዩ የደንበኞች ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ዘዴዎችን በመጠቀምና የአባላት ቁጠባ አሰባሰብን ቀልጣፋ በማድረግ አባላት በአግባቡ እንዲቆጥቡና ቆጥበውም እንዲበደሩ ማስቻል እንደሚገባ ገልፀዋል።

ከወጣቶች መረዳጃ ዕድር ተነስቶ ደረጃውን የጠበቀ የቁጠባ የብድር እና የማማከር አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ቅርንጫፎችን ከፍቶ ደንበኛ ተኮር አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ይህን አገልግሎቱን ይበልጥ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግም ከቅርንጫፎች ጋር የሚያደርገው መሰሉ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።

በኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ውስጥ ወጥነት ያለው የኦፕሬሽን ስራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር ለቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ስልጠና ተሰጥቷል። አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2018 ...
21/05/2026

በኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ውስጥ ወጥነት ያለው የኦፕሬሽን ስራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር ለቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ስልጠና ተሰጥቷል።

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተሞች እንዲሁም በክልል ከተሞች ከሚገኙ 11 ቅርንጫፎች ለተውጣጡ 24 ያህል የኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆችና ኦፊሰሮች በዛሬው እለት ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል።

ለሁለት ቀናት የሚቆየው ይህ ስልጠና ወጥነት ያለው የኦፕሬሽን ስራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ሲሆን የላቀ የደንበኞች አገልግሎትና ዘመናዊ የቁጠባና ብድር አሰራሮችንም ያማከለ መሆኑ ተነግሯል።

የዛሬውን ስልጠና የሰጡት የማህበሩ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙላቱ በዕደ ማህበሩ በሁሉም ቅርንጫፎቹ ለአባላት የተጠናከረና ወጥነት ያለው አገልግሎት መስጠቱን አጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ እንዲህ አይነቱ ስልጠና አስፈላጊ አንደሆነ ጠቁመዋል።

ጥራቱን የጠበቀና ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ በመሆኑ ብዙሃን የመሰከሩለት ይህ ማህበር የአገልግሎት ተደራሽነት አድማሱን እያሰፋ ይገኛል ያሉት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚው ይህንን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የሚረዱ የተለያዩ አሰራሮችንም ለሰልጣኞች አብራርተዋል።

አቶ ሙላቱ አክለውም ብዙዎችን ጥሪት ያስቋጠረው ማህበሩ የአባላቱን እርካታ በፍጥነት ለመጨመር የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሚገባቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል።

የተለያዩ የደንበኞች ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ዘዴዎች እንዲሁም ምቹ የአሰራር ስልቶች በቀረቡበት በዚህ ስልጠና ላይ ማህበሩ የላቀ አገልግሎት በመስጠትና አባላቱን ወደተሻለ ኢንቨስትመንት በማሸጋገር ጥሪት እንዲቋጥሩ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተነግሯል።

ከወጣቶች መረዳጃ ዕድር ተነስቶ ደረጃውን የጠበቀ የቁጠባ የብድር እና የማማከር አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ቅርንጫፎችን ከፍቶ ደንበኛ ተኮር አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

Marsaa 5’niif geggeeffamaa kan ture,  Sagantaan  Waldorgommii Gaaffiif Deebbii Barattootaa, Dhaabbanni Tola Ooltummaa It...
19/05/2026

Marsaa 5’niif geggeeffamaa kan ture, Sagantaan Waldorgommii Gaaffiif Deebbii Barattootaa, Dhaabbanni Tola Ooltummaa Itiyoo Xirriit qopheessuun Mana Barumsaa Yaadannoo ArtistiI Haacaaluu Hundeessaatti geggeessaa ture haalaa hoo’aa ta’een xummurame.

Finfinnee; Caamsaa 10/2018 A.L.I

Sagantaan Sagantaan Waldorgommii Gaaffiif Deebbii Barattootaa, Dhaabbanni Tola Ooltummaa Itiyoo Xirriit Waajjira Barnootaa Bulchiinsa Magaalaa Aqaaqii Qaallittii fi Waajjira Faayinaansii Bulchiinsa Magaalaa Aqaaqii Qaallittii waliin waliigaltee mallatteessuun Mana Barumsaa Yaadannoo ArtistiI Haacaaluu Hundeessaatti Sad’ 1ffaatti qopheeessi bifa bareedaa ta’een xummurame.

Sagantaa Xummuraa kanaan walumaa galatti barattoota kutaa 6ffaa fi 8ffaa baay’inaan 12 ta’an gidduutti dorgommiin ajaa’ibsiisaa taasifamuun sadarkaan isaanii adda baafamee gara badhaafamaa badhaasa sagantichaatti darbaniiru.

Haaluma kanaan dorgommii waaree dura taasifameen barattoota sadarkaa qabachuuf waldorgoman 6 keessaa 3 kan kan barnoota isaanii sagantaa Afaan Oromootiin hordofan yoo ta’u, 3 ammoo kan Afaan Amaariffaatiin hordofaniidha.

Haaluma wal fakkaatuun waaree booda dorgommii barattoota kutaa 8ffaa itti fufe keessatti, barattoota Afaan Amaaraatiin baratan keessaa barattoonni dhiiraa 2 fi dubartiin 1 sadarkaa 1ffaa irraa hanga 3ffaa qabachuun xumuruun isaanii ibsameera.

Akkasumas barattoota Afaan Oromootiin baratan keessaa dubartiin 1 fi barattoonni dhiiraa 2 sadarkaa 1ffaa irraa hanga 3ffaa qabachuun xummuruu danda’aniiru.

Dorgommiin gaaffii barnoota Ingiliffaa fi Herregaan gaggeeffamaa ture kun barattoota qormaataaf qopheessuun, dandeettii dubbisuu isaanii guddisuun, akkaataa qo’annoo isaanii fooyyessuu fi miira dorgommii gaarii akka horatan taasisuuf kan isaan gargaaru ta’uu isaa haalaan ibsameera.

Walumaa galatti sagantaa kanaan barattoota kutaa 6ffaa fi 8ffaa sagantaa barnoota isaanii Afaan Oromoo fi Afaan Amaariffaatiin hordofan gidduutti jalqabaa kaasee hanga dhumaatti dorgommii cimaatu taasisifamaa ture.

Barattoota jalqabaa kaasanii hanga dhumaatti turuun sadarkaa 1 hanga 3 bahaniif sagantaa cufiinsa bara barnootaa irratti dhaabbatichaan badhaasni kan gummaachamuuf ta’uun ibsame.

Barattoota kallattiin waltajjiirratti bahanii dorgomaa turaniin alatti, dhaabbatichi gaaffilee shaakaltii qopheessuun barattoota kaawwanis dorgomsiisuun badhaasaa kan ture yoo ta’u, sagantaa cufiinsa bara barnootaarrattis barattoota gaaffilee shaakaltii kanniin haalaan hojjetan keessaa motii, moo’attootaa adda baasuun kan badhaasu ta’uu ifoomeera.

Dhaabbanni kun dhaabbata geggeessitoonni, raaewwattoonni, miseensonnii fi hawaasni Waldaa Hojii Gamtaa Qusannoo fi Liqii Itiyoo Xirriit hundeessan yoo ta’u, gara fuulduraatti hojiilee tola ooltummaa hedduu hojjetuuf kan jiru akka ta’e, ifoomeera.

ለተከታታይ 5 ዙሮች ሲካሄድ የቆየውና የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለክልል አቀፍ የሚኒስትሪ ፈተና የማዘጋጀት ዓላማን ያነገበው የኢትዮ ጥሪት የበጎ አድራጎት ድርጅት የተማሪዎች ጥያቄና ...
19/05/2026

ለተከታታይ 5 ዙሮች ሲካሄድ የቆየውና የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለክልል አቀፍ የሚኒስትሪ ፈተና የማዘጋጀት ዓላማን ያነገበው የኢትዮ ጥሪት የበጎ አድራጎት ድርጅት የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር በታላቅ ድምቀት ተጠናቋል።

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2018 ዓ.ም

የኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር እህት ድርጅት የሆነው የኢትዮ ጥሪት በጎ አድራጎት ድርጅት ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ከሚመለከታቸው የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጽህፈት ቤቶች ጋር በመተባበር ያስጀመረው የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር በታላቅ ድምቀት ተፈፅሟል ።

ትምህርታቸውን በአማርኛ እንዲሁም በፋን ኦሮሞ በሚከታተሉ በአጠቃላይ 12 የስድስተኛ እና የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ብርቱ የፉክክር መንፈስ የታየበት የፍጻሜው ውድድሩ አሸናፊ ተማሪዎችን በመለየት ነው የተጠናቀቀው፡፡

በዚህ መሰረት ትምህርታቸውን በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ የሚከታተሉ 6 ተማሪዎች ለደረጃ በተወዳደሩበት የጠዋቱ የውድድር ጊዜ በአማርኛ የሚማሩ 3 ወንድ ተማሪዎች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ሆነው ውድድሩን ሲያጠናቅቁ በአፋን ኦሮሞ የሚማሩ 3 ሴት ተማሪዎችም በተመሳሳይ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን ይዘው ውድድሩን ፈጽመዋል፡፡

በተመሳሳይ ከምሳ ሰዓት በኋላ በቀጠለው የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ውድድርም ትምህርታቸውን በአማርኛ ከሚከታተሉ ተማሪዎች መካከል ሁለት ወንድና 1 ሴት ተማሪዎች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል፡፡

እንዲሁም በአፋን ኦሮሞ ትምህርታቸውን ከሚከታተሉ ተማሪዎች መካከል 1 ሴትና ሁለት ወንድ ተማሪዎች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ማግኘት ችለዋል፡፡

በእንግሊዝኛ እና በሒሳብ ትምህርት ጥያቄዎች ሲካሄድ የነበረው ውድድሩ ተማሪዎቹን ለፈተና በማዘጋጀት፣ የንባብ ክህሎታቸውን በማሳደግ፣ የጥናት ዘይቤያቸውን በመቀየስ እና በመልካም ፉክክር ሀሳብ እንዲለወጡ በማድረግ ለተማሪዎቹ ድጋፍ ማድረጉም ተገልጿል።

በአጠቃላይ በ5ቱም ዙሮች በሁለቱም የትምህርት ደረጃዎችና የቋንቋ ምድቦች ተማሪዎች ጠንካራ ፉክክር ያደረጉ ሲሆን ከ1ኛ እስከ 3ኛ የወጡ ተማሪዎች በቀጣይ ትምህርት ቤቱ በሚያዘጋጀው የመዝጊያ ፕሮግራም ወላጆች እና አመራሮች በተገኙበት ልዩ ሽልማት እንደሚሰጣቸው ተነግሯል።

ከዚህ ባሻገር እስከ ዛሬ ውድድሩ ላይ ሲታደሙ ለነበሩ ተማሪዎች በፍፃሜው ውድድር መግቢያ ላይ ወርክሽት ተከፋፍሎ ሰርተው እንዲመልሱ ሲደረግና በየዙሩ ሲሸለሙ የነበረ ሲሆን ዋናዎቹ ተወዳዳሪዎች በሚሸለሙበት ልዩ መርሃ ግብር ላይ ወክሽቶቹን በመስራት የተሻሉ የነበሩ ታዳሚ ተማሪዎችም እንደሚሸለሙ ነው የተጠቀሰው፡፡

ከወጣቶች መረዳጃ እድር ተነስቶ ቢሊዮን ብሮችን ወደሚያንቀሳቅስ ተቋምነት ያደገው ኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር የኅብረት ስራ ማህበር በእህት ድርጅቱ የኢትዮ ጥሪት በጎ አድራጎት ድርጅት በኩል ውድድሩን እስከፍፃሜው ሲደግፍ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ለአሸናፊ ተማሪዎቹም በቀጣይ በሚዘጋጀው ልዩ መርሃግብር ላይ ሽልማት የሚያበረክት ይሆናል።

ሰዎች ራሳቸውን ከአሉታዊ አስተሳሰብና ድርጊቶች ነጻ ማድረጋቸው በህይወታቸው ባሳካቸው ብለው የሚመኟቸውን ትልልቅ ህልሞቻቸውን ለማሳካት በእጅጉ እንደሚያግዛቸው ተነግሯል፡፡ አዲስ አበባ፤ ግንቦ...
18/05/2026

ሰዎች ራሳቸውን ከአሉታዊ አስተሳሰብና ድርጊቶች ነጻ ማድረጋቸው በህይወታቸው ባሳካቸው ብለው የሚመኟቸውን ትልልቅ ህልሞቻቸውን ለማሳካት በእጅጉ እንደሚያግዛቸው ተነግሯል፡፡

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2018 ዓ.ም

ሳምንታዊው የኢትዮ-ጥሪት ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ስልጠና መሰጠቱን የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ትኩረቱን ራስን ከአሉታዊ ነገሮች ማጽዳት ለስኬት ያለው አበርክቶት ምን ይመስላል በሚለው ዙሪያ ላይ አድርጎ ተሰጥቷል፡፡

የተለያዩ አስቻይ ዘዴዎች በተዳሰሱበት በዚህ ስልጠና ላይ ፈጣሪን እና በዙሪያችን ያሉ ሰዎችን በተደጋጋሚ ማመስገን የመጀመሪያው ራስን ከአሉታዊ ነገሮች ማጽጃ መንገድ መሆኑ ነው የተነሳው፡፡

የዕለቱን ስልጠና የሰጡት የማህበሩ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ እንደሻው ተገኝ ያልተገደበ ምስጋና ከቅሬታ እና ቁርሾ ወደ ተትረፈረፈ ሰላም ያሻግራል ብለዋል፡፡

ራሳችንን የተለያዩ አሉታዊ የሆኑ ነገሮችን ከማየትም ሆነ ከመስማት መከልከል እና ራዕያችንን ለማሳካት በሚጠቅሙን ነገሮች ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ መልመድ እንደሚገባ ያስረዱት ዋና ስራ አስፈጻሚው ለዚህም እያሰብን ያለነውን ሀሳብ ምንነት በየ30 ደቂቃው መፈተሽ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሰዎችን መውደድ እንዲሁም ከመጥፎ ነገሮች መካከል ጥሩውን ነገር ብቻ መርጦ ማየት መቻል የአዕምሮ ኃይልን እንደሚገነባ እና ፍጹም የይቅርታ ሰው መሆንም ራዕያችንን ለማሳካት በሙሉ ጉልበት እንድንሰራ እንደሚያደርግም አክለዋል፡፡

ታዲያ ሰዎች እነኚህን ማድረግ ለምን ይከብዳቸዋል የሚለውን ጥያቄ ዋና ስራ አስፈጻሚው ሲያብራሩም የሰዎች አዕምሮ ሁልጊዜም የሚፈልገው ከዚህ በፊት የለመደውን ነገር ስለሆነ ከምቾት ቀጠና መውጣት ባለመፈለጉ ነው ሲሉ መልሰዋል፡፡

በተጨማሪም ሰዎች ይዘውት በመጡት ልማዳቸው ምክንያት የግል ማንነታቸውን ማስነካት አለመፈለጋቸው ሌላው ምክንያት ነው ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

አክለውም ሰዎች የአሉታዊ ስሜቶቻቸው ሱሰኛ እንደሆኑ ሳይንሳዊ ጥናቶች የሚያሳዩ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን ይህም ማለት ለማማርር፣ ለቁጣ እና ለጭንቀት ተገዥ መሆናችንን አውቀን ልንሰራባቸው እንደሚገባ በጥልቀት አብራርተዋል፡፡

እንዲህ ያለው የኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር የኅብረት ስራ ማህበር የማለዳ ስልጠና በየሳምንቱ ሰኞ ጠዋት ጠዋት የሚሰጥ ሲሆን ዓላማውም የማህበሩ ፈጻሚዎች ለስራቸውም ሆነ ለግል ህይወታቸው የሚሆናቸውን ስንቅ በመስጠት ውጤታማ ህይወት እንዲመሩ ማስቻል ነው፡፡

Waldaan Hojii Gamtaa Qusannaa Fi Liqii Itiyo-Xiriit Miseensota Haaraaf  Leenjii  Kennu Marsaa 50ffaaf Har’as Itti Fufee ...
16/05/2026

Waldaan Hojii Gamtaa Qusannaa Fi Liqii Itiyo-Xiriit Miseensota Haaraaf Leenjii Kennu Marsaa 50ffaaf Har’as Itti Fufee Kenneera

​Finfinnee; Ebla 8/2018 A.L.I

​Leenjiin miseensota haaraa Waldaa Hojii Gamtaa Qusannaa fi Liqii Itiyo-Xiriit torban torbaniin kennamu har’a 8/2018 A.L.I marsaa 50ffaan itti fufee yeroo gaggeeffametti, haaluma baratameen miseensonni gaaffilee garaa garaa gaafataa turan.

​Gaaffilee miseensonni leenjii fudhatan kunniin kaasaan keessaa, “Itiyo-Xiriit qoodiinsa bu’aa akkamiin raawwata?” kan jedhu isa tokko ture.

​“Waldaan kun daangaa aksiyoonaa namni tokko bituu danda’u kaa’eera moo hin keenye?” kan jedhuus gaaffii isa biraa miseensonni kunniin leenjii kanarratti gaafatan yoo ta’u, gaaffilee ka’aniif gama Kutaa Leenjii fi Humna Ijaarsaa waldichaatiin deebiin fi ibsi kennameera.

Leenjii kanas kan kennan Ittigaafatamaa Kutaa Leenjii fi Human Ijaarsaa kan ta’an Obbo Tashoomaa Baqqalaa yoo ta’an, Obbo Tashoomaan gosoota tajaajilaa, mirgaa fi dirgama miseensotaa fi qabxiilee kanneeniin walqabatan bifa adda ta’een ibsuun leenjicha kennaa turan.

Waldaan Afoosha irraa ka’ee, gara waldaa hojii gamtaatti guddatuun rakkoo faayinaansii namoota hedduu furuu danda’e kun, adda durummaan tajaajiloota qusannoo, liqii fi gorsa diinagdee garaa garaa kennaa kan jiru yoo ta’u, Obbo Tashoomaan kana ibsuu cinaatti, akkaataa qoodiinsa bu’aa waldichaa haalaan ifa taasisaniiru.

Ibsa isaanii kanaaniis, hangi bu’aa fi baasii waldichaa ogeessa oodiitii Federaalaatiin hojjetamuun miseensota hundaaf akkaataa aksiyoona isaaniirratti hundaa’uun akka qooddamuuf ibsaniiru.

​Obbo Tashoomeen gaaffii “Waldaan kun daangaa aksiyoonaa kaa’eeraa?”jedhuuf yeroo deebii kennan, akka labsii waldaalee hojii gamtaatti, namni tokko %10 baay’ina aksiyoona gurguruuf waldichaaf heyyamamee bitachuu akka danda’u ifa taasisaniiru.

​Dhumarrattis, miseensonni leenjii fudhatan kana gara qabatamaatti jijjiiranii akka itti fayyadaman dhaamuu fi leenjichi torban torbaniin cimee akka itti fufu akeekuun leenjiin guyyaa sanaa xumurameera.

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio-Terit Credit Societies posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share