ጽንዓ Media

ጽንዓ Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ጽንዓ Media, Business service, Bole, Addis Ababa.

ጽንዓ ትዩብ | Tsinia Tube ኦርቶዶክሳዊ የቪድዮ ትምህርቶች፣ መዝሙራት፣ ምክረ አበው፣ ብሒለ አበው፣ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች፣ ሃይማኖታዊ ጥቅሶችና አባባሎች እንዲሁም ትምህርታዊ የቀጥታ ሥርጭቶች የሚቀርቡበት መድረክ ነው። ማንኛውንም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን የተመለከተ ቁም ነገር ሲፈልጉ የመጀመሪያ መድረሻዎን ጽንዓ ቲዩብ | ጽንዓ Tube ቢያደርጉ ይጠቀማሉ።

ነሐሴ/19/2018/ ዓመተ ምህረት  👉በስመ   አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን   ለምናመሰግንበት ለመልአኩ   ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን           እኔ...
25/08/2026

ነሐሴ/19/2018/ ዓመተ ምህረት


👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን ለምናመሰግንበት ለመልአኩ ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን

እኔ #በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው #ገብርኤል ነኝ
ሉቃ.1፥19

👉ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን አባቶቻችን እንዳስተማሩን ዘመኑ ጣኦት የሚመለክበት ንጉስ ናቡከደነፆር በባቢሎን ምርኮ የወሰዳቸው #የእግዚአብሔር ሰዎች አናንያ፤ አዛርያ፤ ሚሣኤል እጅግ ይወዳቸው ነበር

👉ከባቢሎናውይን ይልቅ በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ሦስት ሰፍሮ በምናገኘው ታሪካቸው እንደሚግረን ንጉሱ የጣኦት ምስል አሰራ በገሊላ አውራጃ ያለውን ሕዝብ ጠርቶ ለጣኦቴ ያልሰገደ ወደ እሳት ውስጥ ይጣላል ብሎ አወጀ የንጉስ ትዕዛዝ ነውና ሕዝቡ ሁሉ ለጣዖቱ ሲንበረከክ እነርሱ ግን ቆመው ያዩ ነበር

👉ናቡከደነፆር እርሱ ላስቆመው ጣኦት አለመስገዳቸውን ሲሰማ ተናደደ፤ ተበሳጨም እሳቱን 7 እጥፍ እንዲነድ አስደረገ ሦስቱንም አስሮ እሣቱን እያሳየ "ከመቃጠል ወይስ ለእኔ ጣኦት መስገድ የቱ ይሻላል ቢላቸውም #የእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምንም ነገር አያስፈራውምና የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶን ሊያድነን ይችላል ባያድነንም ግን አንተ ላቆምከው ጣኦት አንሰግድም አሉት

👉በዚህ ጊዜ ጉልበት ያላቸው ሠዎች ተፈልገው ሦስቱን ወጣቶች አስረው ወደ እሳት ቶን ውስጥ ጣሏቸው አስረው የጣሉቸው ወታደሮች የእሳቱ ወላፈን አቃጠላቸው ግን መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ እሳቱን አበረደላቸው አጠፋላቸው

👉በዚህም ጊዜ ንጉስ ናቡከደነፆር እንዲህ በማለት መሰከረ "እኛ አስረን የጣልናቸው ሦስት ነበሩ አሁን ግን አራተኛው ሰው በእሳቱ ሲመላለስ ይታየኛል የአራተኛው መልክ ደግሞ #የአማልክትን መልክ ይመስላል አለ

👉 #የእግዚአብሔር የማዳኑ ስራ ሲገለጥ ቅዱስ ገብርኤል ሲታይ አዋጁ ሁሉ ተሻረ ጉልበት ሁሉ ለጣኦት ይስገድ ተብሎ የነበረው አዋጅ ተሽሮ ጉልበት ሁሉ ለሠለስቱ ደቂቅ አምላክ የሚል አዋጅ ታወጀ

👉የስሙ ትርጓሜ ታማኝ አገልጋይ የሆነው በዘመናችንም ለበርካቶች ታላቅ ተአምራት ሰርቷል ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ጥበቃው ረድኤት በረከቱ አይለየን

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን"

24/08/2026

እግዚአብሔር ይመስገን!!
ለሆነዉም ላልሆነዉም!

እግዚአብሔር አምላክ ጽዮንን መርጧታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዷታልና፥ እንዲህ ብሎ። "ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።"መዝሙር ፦ 131(132) : 13...
21/08/2026

እግዚአብሔር አምላክ ጽዮንን መርጧታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዷታልና፥ እንዲህ ብሎ። "ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።"
መዝሙር ፦ 131(132) : 13―14

እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የዕርገት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ነሐሴ 16 ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋዋ በክብር ወደ ሰማይ ያረገበት ታላቅና ድንቅ የ...
21/08/2026

እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የዕርገት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ነሐሴ 16 ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋዋ በክብር ወደ ሰማይ ያረገበት ታላቅና ድንቅ የመታሰቢያ በዓሏ ነው።
የእመቤታችን የ64 ዓመታት የምድር ሕይወት
3 ዓመት፦ በወላጆቿ በኢያቄም እና በሐና ቤት
12 ዓመት፦ በቤተ መቅደስ በቅድስና
33 ዓመት ከ3 ወር፦ ከወዳጅ ልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር
15 ዓመት፦ በቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ (በአደራ)
ከዕረፍት እስከ ትንሣኤና ዕርገት የተደረጉ ታምራት
ጥር 21 ቀን (በ50 ዓ.ም)፦ እመቤታችን ከዚህ ዓለም በሞት አረፈች። ሐዋርያት ሊቀብሯት ወደ ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ “እንደ ልጇ ተነሣች እንዳይሉ” ሥጋዋን ለማቃጠል ተማከሩ።
የታውፋንያ እጅ መቆረጥና መፈወስ፦ ታውፋንያ የተባለው አይሁዳዊ የአልጋዋን ሸንኮር በድፍረት ሲይዝ በመልአክ እጁ ተቆረጠች፤ በኋላ ግን ተጸጽቶ በመለመኑ እመቤታችን እጁን መልሳለታለች።
ወደ ገነት መወሰድ፦ መልአኩ የእመቤታችንን ሥጋ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወደ ገነት ወስዶ በዕፀ ሕይወት ሥር አኖረው።
የሐዋርያት ሱባኤ እና መቃብር፦ ሐዋርያት ሥጋዋን ለማግኘት ከነሐሴ 1 ጀምሮ ሱባኤ ገቡ። በ14ኛው ቀን ጌታችን ሥጋዋን ሰጥቷቸው በጌቴሴማኔ ቀበሯት።
የቅዱስ ቶማስ ምስክርነት እና ሰበን፦ በወቅቱ በሕንድ የነበረው ቅዱስ ቶማስ ሲመለስ እመቤታችን ስታርግ አግኝቷት ሰበኗን (መግነዟን) ተቀበላት። ለሐዋርያትም ነግሯቸው ሰበኑን አካፈላቸው።
የነሐሴ 16ቱ ሰማያዊ ቅዳሴ፦ ሐዋርያት “ዕርገቷን እኛም ማየት አለብን” ብለው በዓመቱ ነሐሴ 1 ቀን እንደገና ሱባኤ ገቡ። ነሐሴ 16 ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ረዳት ቄስ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስን ዋና ዲያቆን አድርጎ በመቀደስ ሐዋርያትን አቆረባቸው፤ የእርገቷንም ምስጢር አሳያቸው።
እንኳን ለእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገት በዓል በሰላም አደረሰን❤❤❤❤❤❤❤❤!!!!

ነሐሴ 15/2018                          #በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ           በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ                  ለ...
20/08/2026

ነሐሴ 15/2018






#በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ

በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ

ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሣስባሉ መዝ.44፥16

👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን ዋዜማ እንኳን አደረሰን እንዲሁም ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን

👉የጠፋ በግ አዳምን የፈለገው ባገኘውም ጊዜ የተሸከመው እውነተኛ ቸር ጠባቂያችን #ክርስቶስ ካንቺ የተወለደ እመቤታችን #ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ

👉 #እግዚአብሔር በብሩህ ደመና ተጭኖ መጥቶ በማኅፀንሽ ያደረ ሆይ ደስ ይበልሽ

👉በቅዱሳን ነቢያት በቅዱሳን መላእክት አድሮ የሚኖር ካንች ተወልዶ የተገለጸልን ሆይ ደስ ይበልሽ

👉ከወለድሽው በኋላ ማኅተመ ድንግልናሽ እንዳይለወጥ አድርጎ የጠበቀሽን #አማኑኤልን የወለድሽው ሆይ ደስ ይበልሽ

👉ማኅተመ ድንግልናሽ ሳይለወጥ የወለድሽ ሆይ ሰላምታ ይገባሻል

👉እኛ ከምንወደው እሱም ከሚወደን ልጅሽ ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ #ለምኝልን

👉እናታችን ማርያም የቅዱሣን ሁሉ መሠብሠቢያ የምትሆን ቅድስት ሀገርሽን ኢትዮጵያን በምልጃ ፀሎትሽ አስቢያት እኛንም ልጆችሽን ልጅሽ #ክርስቶስ ይቅር ይለን ዘንድ ለምኝልን በዚህ እለት የሚታሰቡ #ቅዱሣን ምልጃ ፀሎታቻዉ የከበረ ቃል ኪዳናቸዉ ከኛ ጋራ ይሁን

👉የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን"

     👉በስመ   አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችንን መድኃኒታችንን   በፆምና በፀሎት ለምንለምንበት    በምልጃ ፀሎቷ እንድታስበን ለምንማፀንበት ሐዋርያት የእናታችን  #ማርያምን የከበረ ሥጋ...
20/08/2026






👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችንን መድኃኒታችንን በፆምና በፀሎት ለምንለምንበት በምልጃ ፀሎቷ እንድታስበን ለምንማፀንበት ሐዋርያት የእናታችን #ማርያምን የከበረ ሥጋዋን ላገኙበት የሱባኤ ማጠናቀቅያ እንኳን አደረሰን

👉አምላክን የወለደሽ እጅግ ርህሩህና አዛኝ የሆንሽ እመቤት ነሽና ባንቺ ጥበቃ ከተማፀኑ እርዳታሽንም አማላጅነትሽንም የፈለጉ ሁሉ አንድ ስንኳ አልቀረባቸዉምና የኛንም የልጆችሽን ልመና ሰምተሽ ተቀብለሽ ከልጅሽ ዘንድ አማልጅን

👉የተመሰገንሽ የከበርሽ እናታችን ማርያም ሆይ በልጅሽ በአምላካችን በመድኃኒታችን #ክርስቶስ ዘንድ ስለ ኃጢአታችን ስርየት ለምኝልን በዚህ ምድር አኗኗራችንም የበረከት እንዲሆንልን የጉስቁልና ኑሮን ያርቅልን ዘንድ ከልጅሽ ዘንድ አማልጅን

👉ስለአስራት ሀገርሽ ኢትዮጵያ ከልጅሽ #ክርስቶስ ዘንድ ለምኝልን ማልጅልን ከሚታይም ከተሰወረም መከራ ልጅሽ ይጠብቀን በፀሎትሽ ረዳትነት በልጅሽ አዳኝነት እንታመናለን አባቶቻችን ሐዋርያትን እንደባረክሽ እኛንም ባርኪን "አሜን"

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸው ቅዱሣን አባቶቻችን ፃድቁ እና በፀሎት በምልጃቸዉ ይጠብቁን

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን"

ከደጃፋቸው በራፍ .. ነጫጭ እርግቦች ተኮልኩለዋል፡፡ አንዱ ለአንዷ ጥሬ ያጎርሳል ... አነስ አነስ ያሉትን ደግሞ ትልልቆቹ እርግቦች እያኮለኮሉ ያጫውቷቸዋል፡፡ በእርግቦች ዓለም ... እርግ...
14/08/2026

ከደጃፋቸው በራፍ .. ነጫጭ እርግቦች ተኮልኩለዋል፡፡ አንዱ ለአንዷ ጥሬ ያጎርሳል ... አነስ አነስ ያሉትን ደግሞ ትልልቆቹ እርግቦች እያኮለኮሉ ያጫውቷቸዋል፡፡ በእርግቦች ዓለም ... እርግቦቹ የተለመደ ሕይወታቸውን እየኖሩ ነው፡፡ ያልተለመደው ነገር ግን ከሰርክ ጸሎት ወደቤቷ እየተመለሰች ላለችዋ ሐና ... ተራ የእርግቦች ጨዋታ ብቻ አልነበረም፡፡ ቡዝዝ ባሉት የሐና ዓይኖች ... አጥንት ድረስ የሚገባው የዕብራውያን መበለቶች ሽሙጥ ድቅን አለ ... በጆሮዋ በመቅደሱ ገረገራ የቀለበቻቸው ... " በቅሎዋ ሐና መጣች ፣ እግዜር ምን ብትበድለው በልጅ ቀጣት " የሚሉ ቃላት በታንቡሯ ፈሠሡ፡፡ ምርር ብላ አለቀሰች ... አባትም ፣ ወንድምም ባልም በሆናት ኢያቄም ክንዶች ላይ ጽኑዕ ልቅሶን አነባች፡፡ የኢያቄም መፍትሄ ሱባኤ ሆነ .. ሐና በደጃፏ ፣ ባልዋ በእግዚአብሔር ደጃፍ ተማጸኑ፡፡.......
ወንድ እና ሴት ርግቦች ከሰማየ ሰማያት መጥተዋል፡፡ ወንዱ ርግብ በኢያቄም ራስ ሲቀመጥ ፥ ሴቷ ርግብ በሐና ጆሮ ገብታ በማኅጸንዋ ተቀመጠች፡፡ ይህ ሕልም ...የ40 ቀን ሱባዔ መልስ ነው ... ይህ ራእይ ... ለሁለቱ አእሩግ የጌታን አያትነት ያበሰረ ደስታ ነው፡፡ ከከበረው ራእይ ሰባት ቀን በኃላ ... ማርያም የተባለች .. የምድርም የሰማይም ማር ያስገኘ .. የሐና መጽነሷ ሆነ፡፡ ፍጡራን ሁሉ ክብራቸው ቢደመር ... ከቀሚሷ ስር የማይደርሰው .. የፈጣሪ እናቱ ... የመለኮት ማደሪያዋ ማርያም መገኘት ... ከጋብቻ ሆነ፡፡ ጥንቱን በጋብቻ የመጣው መርገም .. በጋብቻ ታከመ፡፡...
የለቅሶ ቤቱ ድንኳን ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልቷል፡፡ ... ሁሉም የሟችን ስም እየጠራ ይላቀሳል፡፡ ... በአይሁድ ባህል ... ሁሉም ቤተ ዘመድ ሳይገኝ ግብአተ መሬት አይሆንም እንጂ .. የቀብሩስ ሰአት ደርሷል፡፡ አንዲት ሆዷ ነፍሰ ጡር መሆኗን የሚያሳብቅባት ጠና ያለች ሴት .. ወደለቅሶ ቤቱ ስትገባ ግን ታሪኩ ተቀየረ፡፡ የሴቷ ጥላ በአስከሬኑ ሲያርፍ ... ሟቹ ተነሳ ... ሳሚናስ ይባላል፡፡ " ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አምላክ አያቱ የተባልሽ ሐና ሰላም ላንቺ ይሁን አላት " ... ለዚህ አንክሮ ይገባል፡፡
______
የኢያቄም ስዕለትን ፥ የሐና እምነትን የተቀበለ አምላክ .. የእኛንም ስዕለት ፣ ጸሎት ፣ መስዋዕት ይቀበልልን!
የእመቤታችን አማላጅነት ይጠብቀን ... የቅዱሳኑ ኢያቄም ወሐና ረድኤት በረከት ይደርብን!

ድንግል ሆይ! ምን ብዬ...ድንግል ሆይ! በቤተ መቅደስ ሳለሽ መላእክት አረጋጉሽ!ድንግል ሆይ! የሰማይ መና ሊመግብሽ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከልሽ!ድንግል ሆይ ! የጌታ...
10/08/2026

ድንግል ሆይ! ምን ብዬ...

ድንግል ሆይ! በቤተ መቅደስ ሳለሽ መላእክት አረጋጉሽ!
ድንግል ሆይ! የሰማይ መና ሊመግብሽ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከልሽ!
ድንግል ሆይ ! የጌታችንን መጸነስ ሊያበሥርሽ ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ተፈሥሒ ተፈሥሒ እያለ ሰገደልሽ!
ድንግል ሆይ! በግብጽ በረኃ በተሰደድሽ ጊዜ አረጋዊ ዮሴፍ ተከተለሽ!
ድንግል ሆይ! በቀራንዮ አደባባይ ስታለቅሽ ወንጌላዊ ዮሐንስ ተከተለሽ።
ድንግል ሆይ! የልጅሽን ትንሣኤ ራሱ ክርስቶስ ገለጠልሽ!
ድንግል ሆይ! ለግንዘተ ሥጋሽ አበው ሐዋርያት በብሩህ ደመና ተሰበሰቡልሽ!
ድንግል ሆይ! ወደሰማይ ስታሪጊ ቅዱስ ቶማስ ከደመናው ውስጥ ሰገደልሽ!!
ድንግል ሆይ! ቅዱስ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ
አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታቱ
ቅዱስ ያሬድ በማኅሌቱ ስምሽን ያወድሱሻል!!
ድንግል ሆይ! እኔ ባሪያሽ እረ ምን ብዬ ላወድስሽ!?

ድንግል ሆይ! ምንም ኀጢአተኛ ብሆን "እንደ አባቶቼ "ሰዓሊ ለነ ቅድስት" እልሻለሁ!! በሱባኤ እማጸንሻለሁ!!

መልካም ሱባኤ

«ፍልሰታ» ማለት «ማለፍ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መፍለስ» ማለት ነው። ይህም የእመቤታችን ዐፅም ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት፣ በኋላም ትንሣኤዋና ዕርገቷ ከተፈጸመ በኋላ ከገነት ወደ ሰማይ ማረ...
07/08/2026

«ፍልሰታ» ማለት «ማለፍ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መፍለስ» ማለት ነው። ይህም የእመቤታችን ዐፅም ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት፣ በኋላም ትንሣኤዋና ዕርገቷ ከተፈጸመ በኋላ ከገነት ወደ ሰማይ ማረጓን ያመለክታል። የምንጾምበት ዋና ምክንያቶች፦

​1. የሐዋርያት ፈለግ ለመከተል (ሐዋርያት ስለጾሙት)፦

​እመቤታችን ጥር 21 ቀን በ64 ዓመቷ ባረፈች ጊዜ ሐዋርያት ሊቀብሯት ሲወስዷት አይሁድ «ሥጋዋን አቃጥለን ጥፋቷን እናጥፋ» ብለው ስላደሙ፣ እግዚአብሔር ሥጋዋን በደመና ነጥቆ በገነት በሕይወት ዛፍ ሥር አኖረው። ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ ተለይቷቸው መኖር ስላልቻሉ «ሥጋሽን ግለጥልን» ብለው ከነሐሴ 1 ጀምረው እስከ ነሐሴ 14 ቀን ድረስ 14 አምስት ቀን ሱባኤ ያዙ። በ14ኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ ሰጥቷቸው በጌቴሴማኒ ቀበሯት።

​2. የእመቤታችንን ትንሣኤና ዐርገት ለማየት፦

​ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በዕርገቷ ዕለት በደመና ተጭኖ ሲመጣ እመቤታችን ከሞት ተነሥታ ወደ ሰማይ ስታርግ ያገኛታል። ሰበኗን (መገነዟን) ሰጥታው እርስዋ አረገች። ቶማስ ወደ ሐዋርያት መጥቶ የእመቤታችንን መነሣት ሲነግራቸው ባዩት ነገር ቀንተው «ቶማስ ትንሣኤዋን አይቶ እኛ ሳናይ?» ብለው እንደገና ከነሐሴ 1 ጀምረው ሱባኤ ገቡ። በነሐሴ 16 ቀን ጌታችን እመቤታችንን እግረ አበሳ (ቀዳሚት) አድርጎ አምጥቶ፣ እመቤታችንን ቄስ፣ ጴጥሮስን ንፍቅ ቄስ፣ እስጢፋኖስን ዲያቆን አድርጎ ቅዳሴ ቀድሶ ቁርባን አቀበላቸው። ሐዋርያት ትንሣኤዋንና ዐርገቷን በአይናቸው አይተው ተደሰቱ።

​3. የበረከትና የጸሎት ጊዜ ስለሆነ፦

​እኛም ዛሬ የሐዋርያትን አርአያ ተከተልን፤ የእመቤታችንን በረከት፣ አማላጅነትና ፍቅር ለመቀበል፣ ከኃጢአታችን ለመንጻትና በሱባኤ ከአምላካችን ጋር ለመገናኘት ይህንን ጾም እንጾማለን።

​መልእክት፦

በዚህ በታላቁ የሱባኤ ወቅት አቅማችን በፈቀደ መጠን በጾም፣ በጸሎት፣ በምጽዋትና በቅዱስ ቁርባን በመወሰን የእመቤታችንን ረድኤት እንቀበል።

​«የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ ጸሎትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን!»

‹‹ሐምሌ 26›› በዚህች ቀን የእመቤታችን ጠባቂ የስደት የመከራዋ ተካፋይ የነበረው አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ አረፈ፡፡አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ ከንጉሥ ዳዊት ሲሆን አባቱ ያዕቆብ...
02/08/2026

‹‹ሐምሌ 26›› በዚህች ቀን የእመቤታችን ጠባቂ የስደት የመከራዋ ተካፋይ የነበረው አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ አረፈ፡፡

አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ ከንጉሥ ዳዊት ሲሆን አባቱ ያዕቆብ ሲሆን እናቱ ዮሐዳ ትባላለች።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የጠበቀ ክርስቶስን ከተረገዘበት ፣ እስኪወለድ ደግሞም እስከ ግብጽ ስደት ድረስ አብሯት የተንከራተተ፣ ጌታችንንም የተንከባከብ ጻድቅ ሰው ነው።

በልዑል እግዚአብሔር ተመርጦ ክርስቶስ ኢየሱስንና እመቤታችንን ያገለገለ መልካም ፣ ጻድቅ አረጋዊ ሰው
ቅዱስ ዮሴፍ ነው።

ደጉ ሽማግሌ ቅዱስ ዮሴፍ ምን ቢያረጅ እመቤታችንን ለማገልገል አልደከመውም። አብሯት ተሰደደ ፡ረሃብ ጥማቷን ፡ጭንቅና መከራዋን ፡ሐዘንና ችግሯን ተካፍሏል። ከእመ ብርሃንና አምላክ ልጇ ጋር ለ16 ዓመታት ኑሯል።

ከእነዚህ ዘመናት በኃላም በ16 ዓ/ም : በተወለደ በ91 ዓመቱ ሲያርፍ ጌታችን "ሥጋሕ አይፈርስም" ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶለታል።

የቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ በረከትና ምልጃ ይደርብን🙏

Address

Bole
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጽንዓ Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share