25/03/2026
በአለም አቀፍ ደረጃ በኢራን ጦርነት ምክንያት፣ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚደረገው የመርከብ ጉዞ በመስተጓጎሉ ምክንያት የነዳጅ ጉዳይ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረ ቢሆንም ለኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ብሎም ኢኮኒሚሚዋ በግብርና ላይ ለተመሰረተው ኢትዮጵያ በዚሁ የኢራን ጦርነትና የአገር ውስጥ ግጭት ምክንያት የማዳባሪያ አቅርቦት መቀነስ ብሎም የዋጋ ንረት ምናልባትም ከነዳጅ በበለጠ ፈተና ሊሆን ይችላል፡፡
ግብርና ለኢትዮጵያ ከጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት 35 በመቶ ድርሻ የሚይዝና እና ከ70 በመቶ በላይ ለሚሆነው የሰው ኃይል የሥራ ዕድል የፈጠረ ዘርፍ በመሆኑ፣ በዚህ ዘርፍ ላይ የሚመጣ ማንኛውም መስተጓጎል የሀገሪቱን የምግብ ዋስትና በከፍተኛ ደረጃ ይፈታተናል፡፡
የኢራኑ ጦርነት ብቻ ሳይሆን በአገር ውስጥ ግጭት የማዳበሪያ ስርጭቱን ሊጎዳው ስለሚችል መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት በእግጁ ሊያስቡበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
(የዚህን ሀሳብ ዝርዝር ከታች በመጀመሪያው ኮሜንት ባለው ሊንክ ያገኙታል)