Afar tiv

Afar tiv # like # comment

በቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅ ላይ የግብዓት ማሰባሰብ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበ...
18/05/2024

በቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅ ላይ የግብዓት ማሰባሰብ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የግብዓት ማሰባሰብ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ የሕግና የሳይበር ሙያተኞች ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት እየተሳተፉ ነው።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር የኢንፎርሜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተወካይ ሃኒማል ለማ በዚሁ ጊዜ÷ በቁልፍ የመንግሥት መሰረተ ልማቶችን የሳይበር ደኅንነት በማስጠበቅ ለዜጎች አገልግሎት ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል ምኅዳር እየተፈጠረ ነው ብለዋል።

የረቂቅ አዋጁ ዝግጅት ተጠናቆ በሥራ ላይ ሲውል የመንግሥትን መሰረተ ልማትን ለመጠበቅ ግልጽ የሆኑ የአሠራር ሥርዓት ለመዘርጋት ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው መመላከቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር የሳይበር ሕግ ምርምርና ዝግጅት ዲቪዥን ኃላፊ ፍቅረሥላሴ ጌታቸው÷ረቂቅ አዋጁን በማጽደቅ ሥራ ላይ በማዋል ቁልፍ የመንግሥት መሰረተ ልማቶችን የሳይበር ደኅንነት የተጠበቀ በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ የሚገኘውን የዘርፉን ጥቃት መመከት እንደሚያስችል ገልጸዋል።

የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅ ይዘት፣ ዓላማና ምንነት ለውይይት መነሻነት ቀርቦ ባለድርሻ አካላት ምክክር እያደረጉበት ይገኛል።

በ10 አመታት ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንጀምራለን-ኤለን መስክ  *************************በቀጣይ 10 አመታት ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንደሚጀመርና በ30 አ...
18/05/2024

በ10 አመታት ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንጀምራለን-ኤለን መስክ
*************************

በቀጣይ 10 አመታት ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንደሚጀመርና በ30 አመት ውስጥ ማርስ ላይ ዘመናዊ ከተማ እንደሚገነባ የስፔስ ኤክስ መስራች ኤለን መስክ ገልጿል።

የማርስ ከተማ ግንባታን እውን ለማድረግ ስፔስ ኤክስ በርካታ የቅኝት ሳተላይቶችን በቅርቡ እንደሚልክ ማስታወቁን የዴይሊ ስታር ዘገባ ያመላክታል።

"በጥቂት አመታት ውስጥ ሰዎችን በማርስ ላይ የማስፈር ዕቅዳችንን ዕውን እናደርጋለን" ብሏል የ52 ዓመቱ ቢሊየነር ኤለን መስክ።

"ከ10 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንጀምራለን፤ ከበረታን እስከ 20 ዓመት፣ በእርግጠኝነት ግን በ30 ዓመት ውስጥ ዘመናዊ ከተማ በማርስ ላይ እንገነባለን" ብሏል ኤለን መስክ።

እ.አ.አ 2002 የተመሰረተው ስፔስኤክስ ወደ አለማቀፉ የህዋ ጣቢያ ለመጀመሪያ ጊዜ መንኮራኩር እና ጠፈርተኞችን የላከ የግል ኩባንያ ነው።

"የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃ የሚወጣው በልማት እንጂ በነፃ እውጪ ነን ባዮች አይደለም" - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ *********************(ኢ ፕ ድ) የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃ የሚወጣው ...
17/05/2024

"የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃ የሚወጣው በልማት እንጂ በነፃ እውጪ ነን ባዮች አይደለም" - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
*********************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃ የሚወጣው በልማት እንጂ በነፃ እውጪ ነን ባዮች አይደለም ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።

የብላቴ ኮማንዶና አየር ወለድ ማስልጠኛ ማዕከል ሠልጣኞች ተመርቀዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ማንም እየተነሳ ነፃ አውጪ ነኝ ይላል፤ ሕዝቡ ነፃ የሚወጣው ከድህነት ሲላቀቅ ነው ብለዋል።

ለዘመናት እርስ በእርስ ስንባላ ያባከነውን ጊዜ የሚያካክስ ሠላም ያስፈልጋል ሲሉም ገልጸዋል።

ፊልድ ማርሻሉ እንዳመላከቱት መከላከያ ሠራዊት ለሠላምና ደህንነት ቅድሚያ ሰጥቶ ኢትዮጵያን የሚጋፉትን ይከላከላል።

በጌትነት ተስፋማርያም

ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓም

ተይዘዋል!...የአፍሮ ስቱድዮ ባለቤት ወ/ሮ ልደት አበባው እና በጋዜጠኝነት ያየናት ወ/ሮ ታደለች ብርሀኔ በትወና ህፃን ናትናኤል መስፍን፣ በትወና ወጣት ካሊድ ድጉማ ከባህልና እሴታችን ባፈነ...
17/05/2024

ተይዘዋል!...
የአፍሮ ስቱድዮ ባለቤት ወ/ሮ ልደት አበባው እና በጋዜጠኝነት ያየናት
ወ/ሮ ታደለች ብርሀኔ በትወና
ህፃን ናትናኤል መስፍን፣ በትወና
ወጣት ካሊድ ድጉማ ከባህልና እሴታችን ባፈነገጠ መልኩ አንድ በእድሜ የገፋች እናት ከ13 ዓመት በማይበልጥ ህፃን ያረገዝኩት ላንተ ሳይሆን ላባትህ ነው ስትል የሚያሳይ አፀያፊ ቪዲዮ የሰሩ ግለሰቦች የይትዩቡ ባለቤቶች ፈታኝ ትግል በኋላ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና በቅን ልቦች ብርቱ ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል ።
ቅን ልቦች ነገም ከባህልና እሴቶቻችን ባፈነገጠ መልኩ የሚሰሩ ዩቱዩበርና ቲክቶከሮችን በህግ የማስጠየቁን ስራ እቀጥላለሁ ብሏል።

03/11/2020

Let’s cross the finish line — together. Vote.

03/11/2020
03/11/2020

በትናንትናው እለት ሁለተኛውን ዙር የአገራዊ ብሄራዊ ምክክርና ተሳትፎ የአመራር መድረክ ጀምረናል፡፡
አገራዊ የሰላም ግንባታ ስትራቴጂያችን ማህበረሰብ ተኮር የምክንያታዊ ሙግት ፤ አገርና ህዝብን ታሳቢ ያደረገ ለመቀራረብ መወያየት ለመግባባት መደራደር ያለበት፤ አገር በቀል የእርቅ የድርድርና ሽምግልና ባህላችንን ከረሳንበት ከፍ በማድረግና አሟጦ በመጠቀም ማዳበርን እንደ ዋነኛ ግብ ይወስዳል፡፡
ይህ ደግሞ በጥልቀት ወደ ህዝቡ ቀርበን እንድንወያይ የሚጋብዘን እውነታ ነው፡፡
ህዝቡ ውስጥ እውነት አለ፡፡ ህዝቡ ውስጥ ሃቅ ከነማስረጃው አለ፡፡ ህዝቡ ጋር ተዝቆ የማያልቅ ለትውልድ የሚጠቅም እምቅ የአብሮነት የጥቅሞችን ማጣጣም እሴት አለ፡፡ ህዝቡ ውስጥ የዘመናት የትብብር ጉዞ አሻራዎች ሰምበርና ምልክቱ አሁንም አለ፡፡ ህዝቡ ውስጥ ብዙ የሰላም ሚስጥሮች አሉ፡፡ ስለዚህ የውይይት አቅጣጫችን ከሰፊው ማእዘን ወደጠባቡ የፖሊሲ ማእቀፍ የሚመጣ (Bottom up approach) የሚባለው አይነት ነው፡፡
ኢትዮጵያ ያለ ኢትዮጵያዊ እሴቶች ልትፀና አትችልም፡፡ የሰላም መንገድ ምንጊዜም ውጣ ውረድ የበዛበት ቢሆንም ቅሉ ፍሬዋ ግን ውድና ጣፋጭ አድማስ የሚሻገር ፤ቁጭት የሌለው ፤ለአካልም ለመንፈስም እርካታን የሚያላብስ የአስተዋዮች መንገድ ነው፡፡
ሰላም ወዳድ ከሆነው ሰፊው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ጋር የጀመርነው ጥረት ከግቡ ይደርሳል፡፡እርስዎም ከኢትዮጵያዊ ሰላም ግንባታ ጉዟችን ጎን ይሰለፉ! በሰላም ውስጥ የሚታጣ ነገር የለም! ስለሰላም የሚታጣ እንኳን ቢኖር ከማግኘት በላይ ነው፡፡ ሰላም ራሱ ስጦታ ነውና!
የሰላም ባለቤት እርስዎ ነዎት!!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Afar tiv posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share