28/08/2025
Google ብዙ የማናውቃቸውና ሚስጢራዊ የመረጃ መፈለጊያ ዘዴዎች ያሉት ሲሆን ከነዚህ መካከል የተወሰኑትን ላካፍላችሁ።
👾👾👾👾👾
✔️ Exact Phrase Search: የምንፈልገውን ቃል ወይም ሃረግ ራሱን በቀጥታ ሰርች ለማድረግ የምንፈልገውን ቃል በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ አስገብተን መፈለግ እንችላለን። ለምሳሌ "Ethiopian flag"
✔️ Excluding Words: በፍለጋ ጊዜ መረጃችን ላይ እንዳይካተት ወይም እንዳይመጣ የምንፈልገውን ቃል ከቃሉ በፊት የመቀነስ (minus) ምልክት ካደረግን ቃሉ አይኖርም። ለምሳሌ food-egg ብለን ሰርች ብናደርግ እንቁላል ያልገባባቸውን የምግብ ዝርዝሮች ያመጣልናል።
✔️ Site-Specific Search: አንድን ቃል ከምንፈልገው ድረገፅ ላይ ብቻ ፈልጎ እንዲያመጣልን ከፈለግን "site" ብለን የድረገፁን ሊንክ እናስገባና ቃሉን እንፅፋለን። ለምሳሌ ከwikipedea ላይ artificial intelligence የሚል ቃል ከፈለግን Google መፈለግያው ላይ "site:wikipedia.org artificial intelligence" የሚል ሃረግ እናስገባለን።
✔️ Wildcard Search: ሰርች ማድረግ የፈለግነውን ሙሉ ቃል ከረሳነው ከምናስታውሰው ቃል በፊት ወይም በኋላ asterisk (*) ምልክት እናስገባለን። ለምሳሌ premier league የሚል ቃል ሰርች ማድረግ ፈልገን premier የሚለውን ቃል ግን ብንረሳው *league ብለን ከፃፍን የሰርች ውጤታችን premier league, champions league, rocket league, Little league የሚሉ አማራጮችን ያመጣልናል።
✔️ Defining Words: የአንድን ቃል ትርጉም በፍጥነት ማዎቅ ከፈለግን define ብለን ቃሉን መፃፍ እንችላለን። ለምሳሌ define: serendipity
በፈለግነው ቋንቋ እንዲተረጉምልን ከፈለግን ደግሞ ከቃሉ በኋላ የቋንቋውን ስም እንፅፋለን። ለምሳሌ define: serendipity Amharic ወይም define: serendipity spanish
define በሚለው ቦታ translate የሚለውን መጠቀምም እንችላለን።
✔️ Unit Conversions: Google ላይ ማንኛውንም መለኪያ አሃድ ወደ ሌላው መለወጥ እንችላለን። ለምሳሌ "10 miles to kilometers" ወይም "25 pounds to kilograms."
✔️ Time Zone Conversion: Time zones ከአንዱ ክልል ወደሌላው ለመቀየር ጎግልን መጠቀም እንችላለን።ለምሳሌ "current time in [city]" or "time in [city] compared to [city]."
✔️ Weather Forecast: የፈለጋችሁትን አካባቢ የአየር ንብረት ትንበያ ማዎቅ ከፈለጋችሁ "weather [city]" ብላችሁ መፃፍ ትችላላችሁ። ለምሳሌ weather Addis ababa
✔️ Calculator: ቀለል ያሉ የሂሳብ ጥያቄዎችን መስራት ከፈለጋችሁ ጉግልን መጠየቅ ትችላላችሁ። ለምሳሌ "8 * (5 + 2)" ይህን መፈለጊያው ላይ ብታስገቡ መልሱን ቀጥታ ታገኛላችሁ።
✔️ Related Sites: ከአንድ ድረገፅ ተመሳሳይ ስራ የሚሰራ ሌላ ድረገፅ ከፈለግን ከምናውቀው ድረገፅ በፊት related የሚል ቃል መጨመር እንችላለን። ለምሳሌ "related:wikihow.com" ከwikihow ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ድረገፆች ይዘረዝርልናል።
✔️ Advanced search: Google home page ላይ settings የሚለውን ነክተን advanced search የሚለውን ከመረጥን ዝርዝር ሰርች ማድረጊያ ገፅ ይከፍትልናል።
Wikipedia is a free online encyclopedia, created and edited by volunteers around the world and hosted by the Wikimedia Foundation.