08/12/2022
በሚሊኒየም አዳራሽ መርሐ ግብር ላይ እንዳትገኙ!!!
በማኅበረ ቅዱሳና በደጃችሽ አይዘጉ "ኅብረታችን ለቤተ ክርስቲያናችን" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጁት መርሐ ግብር ላይ ማንም የቤተ ክርስቲያን ልጆች እንዳትገኙ እንላለን።
ምክንያቱም እነዚህ ማኅበራት የእኛ ጠላቶች ስለሆኑ። የእነዚህም ይሁኑ ሌሎች ማኅበራት ምንም እይጠቅሙም።
እኛ ሌት ከቀን በቤተ ክርስቲያን ስም የሚሰበሰቡና የተለያዩ አገልግሎት ለመፈጸም የሚጥሩ በሙሉ እንዲጠፉ አበክረን እንሰራለን።
ታኅሣሥ 2 ቀን 2015 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በጅማና አካባቢው ላይ እየተተገበሩ ላሉ የቤተ ክርስቲያን ስራ አገልግሎቱ እንዲስፋፋ ለማድረግ ማኅበራቱ ለህዝበ ክርስቲያኑ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
እኛ በአገልግሎት እንዳንቃጠል ከፈለጋችሁ በመርሐ ግብሩ ላይ እንዳትገኙ እኛም መልእክት እናስተላልፋለን።
የሰይጣን ማኅበራት ስብስብ!!!
ምንተ ንግበር ግን ሰይጣን የሚቃጠልበት እግዚአብሔር አምላክ የሚመልክበትን የአገልግሎት ዘርፍ ከማኅበራቱ ጎን በመሆን የበኩላችንን እናደርጋለን።
ትኬቱን በ100 ብር ብቻ እየገዛን የበኩላችንን እንወጣ!!
ሁላችንም ታኅሣሥ 2 ቀን 2015 በሚሊኒየም አዳራሽ እንገናኝ።!!!