24/06/2026
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በፍርድ ቤት አሸነፈ
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ ውስብስብ መረጃዎችን በፍጥነትና በፍትሃዊነት በመመርመር የሕግ አገልግሎትን በከፍተኛ ደረጃ እያቀለጠፈው ይገኛል። ይህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እድገት የህግ ባለሙያዎችን ድካም፣ ጊዜና ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ ከመቀነሱም በላይ፣ ህብረተሰቡ እንግልት ሳይገጥመው ፈጣንና ፍትሃዊ ውሳኔ እንዲያገኝ ትልቅ በር ከፍቷል።
ለዚህም ማረጋገጫ የሚሆነው በእንግሊዝ አገር የሚገኘው "ጋርፊልድ" የተሰኘው የኤአይ የሕግ ቢሮ በፍርድ ቤት ክርክር ውስጥ ታሪካዊ ድል ማስመዝገቡ ነው። ፋይናንሻል ታይምስ እንደዘገበው፣ ይህ ክስተት በሕግ ታሪክ ውስጥ አንድ የኤአይ የሕግ አገልግሎት ፍርድ ቤት ቀርቦ ጉዳይ በመርታት ድል ያገኘበት የመጀመሪያው ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኖ ተመዝግቧል። የቴክኖሎጂው መስራቾች እንደሚሉት ይህ ስኬት ወደፊት የሕግ አሰራርን ይበልጥ ለማዘመንና ለማፋጠን ያለውን የጎላ ፋይዳ በግልጽ ያሳየ ነው።