Amen home health care Services

Amen home health care Services Amen Home Care Service in Addis Abeba

25/08/2026

በእርግዝና ወቅት የሚደረግ የስኳር ቅድመ ምርመራ ለሁሉም እናት (universal screening for Gestational diabetes)

በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም (Gestational diabetes, GDM) ሲባል በእርግዝና ጊዜ በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ከፍ ብሎ ሲገኝ የሚከሰት የጤና ችግር ሲሆን ነፍሰ ጡር እናቶችን ከሚያጠቁ የጤና ችግሮች በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው።

ይህ የስኳር አይነት ብዙውን ጊዜ ከወሊድ በኋላ የሚጠፋ ቢሆንም በትክክል ካልታከመ በጽንስና እናት ላይ ጊዜያዊና የረጅም ጊዜ የጤና ችግሮች ሊያስከትል ይችላል።

ይህንን የእርግዝና ጊዜ የጤና ችግር በአስተማማኝ ሁኔታ ለማከምና ለመከላከል የስኳር ቅድመ ምርመራ ለሁሉም እናት (universal screening for GDM) አስፈላጊ ነው። ሁሉም ነፍሰ ጡር እናቶች የስኳር ምርመራ ማድረግ አለባቸው።

የስኳር ቅድመ ምርመራ ለሁሉም እናት ለምን አስፈለገ?

እያንዳንዷ ነፍሰ ጡር እናት የስኳር ምርመራ ማድረግ ይገባታል። የስኳር ህመም ተጋላጭነት ምክንያቶች ቢኖሩም ባይኖሩም የስኳር ምርመራ ማድረግ ለሁሉም እርጉዝ ሴት የሚመከር ነው። ይህ አካሄድ በብዙ አስረጅዎች የሚደገፍ ነው።

የእርግዝና ጊዜ የስኳር ቅድመ ምርመራ መቼ ይሰራል?

የስኳር ቅድመ ምርመራ ለሁሉም ነፍሰ ጡር እናት የሚሰራው በ24 እና 28 ሳምንታት መካከል ባለው አማካኝ የእርግዝና ወራት ነው።
ነገር ግን ከፍተኛ የስኳር ተጋላጭነት ያላቸው ሴቶች (ለምሳሌ ከዚህ በፊት በነበረው እርግዝና ስኳር የታየባቸው፣ ከፍተኛ ውፍረት፣ ወይም ሌላ የሆርሞች መዛባት ችግር) ከ24 ሳምንትም ቀደም ብለው እርግዝና እንደታወቀ ወዲያውኑ ሊመረመሩ ይችላሉ።

የስኳር ቅድመ ምርመራ ለሁሉም እናት እንዴት ይሰራል?

ለእርግዝና ጊዜ የስኳር ቅድመ ምርመራ ለመስራት በጣም የተለመደው የምርመራ ዘዴ የሚበጠበጥ 75 ግራም ግሉኮስ ያለው ጣፋጭ ሽሮፕ በመጠጣት (Oral Glucose Tolerance Test, OGTT) የሚሰራው ነው።

እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን ጉዳይ ቢኖር ለዚህ የስኳር ምርመራ (OGTT) የደም ናሙናው መወሰድ ያለበት ከደም ሥር በሚቀዳ ደም እንጂ ከጣት ላይ ከሚወሰድ ናሙና አይደለም። ክንድ ላይ ካለው የደም ስር የሚወሰደው የደም ናሙና በትክክለኛነቱና አስተማማኝነቱ ተመራጭ ነው። በሁሉም የጂዲኤም ህክምና መመሪያዎች እንደተገለፀው የእርግዝና ጊዜ ስኳር ህመም ለማወቅ (diagnostic purpose) የምንጠቀምበት መስፈርት በደም ፕላዝማ ውስጥ ባለው የግሉኮስ መጠን ላይ የተመሰረተ ነው።

የጂዲኤም ምርመራን ለሁሉም እናቶች ለማዳረስ የሚረዱ ምክሮች

የጂዲኤም ምርመራን ለሁሉም እናቶች ማሰራት የተረጋገጡ የጤና ጥቅሞች ቢኖረውም በኢትዮጵያ በስፋት እየተተገበረ አይደለም። ስለሆነም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነፍሰ ጡር ሴት ለጂዲኤም ምርመራ ማድረግ እንድትችል ከቤተሰብ፣ ከጤና ባለሙያዎች እና ከጤና መሪዎች የተቀናጀ ጥረት አስፈላጊ ነው።

21/08/2026

የአስም ታማሚ ነዎት ወይስ ቤተሰብዎ ውስጥ አስም ያለበት ሰው አለ? እንግዲያውስ በአለም አቀፍ ደረጃ (GINA 2025) እና በአለም ጤና ድርጅት (WHO) መመሪያ መሠረት የአስም ህክምና ላይ ትልቅ ለውጥ ተደርጓል።
​❌ ሳልቡታሞል (ሰማያዊው ኢንሄለር) ብቻውን መውሰድ ለምን ይብቃ ተባለ?
​እስካሁን ድረስ አስም ሲነሳብን የምንወስደው ሰማያዊው ሳልቡታሞል (Salbutamol/Ventolin) ሳምባን በቅፅበት ቢያሰፋም፣ ዋነኛውን የአስም መንስኤ—ማለትም የሳምባ መቆጣትና ማበጥን—አያክምም። እንዲያውም ሳልቡታሞልን ብቻውን በተደጋጋሚ መጠቀም አስም በብዛት እንዲቀሰቀስና ለከፋ አደጋ እንደሚያጋልጥ በጥናት ተረጋግጧል።
​💥 አዲሱ ፍቱን መፍትሔ፡ ቡደሶናይድ/ፎርሞቴሮል (Budesonide/Formoterol)
​አሁን በአዲሱ መመሪያ መሠረት፣ አስሙ ቀላልም ይሁን የጠና፣ ዋነኛው ህክምና Budesonide/Formoterol የተባለው ጥምር መድኃኒት ነው። ይህ መድኃኒት ሁለት ስራዎችን በአንድ ላይ ይሰራል፡
​ፎርሞቴሮል (Formoterol): ልክ እንደ ሳልቡታሞል በ1 ደቂቃ ውስጥ ሳምባን በፍጥነት ይከፍታል።
​ቡደሶናይድ (Budesonide): የሳምባን መቆጣትና ማበጥ ያክማል።
​💡 መድኃኒቱ እንዴት ጥቅም ላይ ይውላል?
1. ​ለቀላል አስም (ደረጃ 1-2)፦ አስም ሲነሳብዎት ብቻ ይህንን መድኃኒት 1 ፑፍ (Puff) ይወስዳሉ። ሌላ ማስታገሻ መያዝ አያስፈልግዎትም።
2. ​ለጠና አስም (ደረጃ 3-5)፦ በየቀኑ ጠዋትና ማታ ለመከላከያነት ይወስዱታል፤ በተጨማሪም አስም ሲነሳብዎት በዚያው መድኃኒት ያስታግሳሉ። (አንድ ኢንሄለር ለሁለቱም ስራ!)
​🔓 / 🔑 ይህ ህክምና ለምን ተመረጠ?
1. ​ከፍተኛ ደህንነት፡ ድንገተኛ የፅኑ ህክምና ፍላጎትን እና ለህልፈት መዳረግን እስከ 64% ይቀንሳል።
​2. ተስማሚ ነው፡ ታካሚው ከአንድ በላይ ኢንሄለር መግዛትና መያዝ ስለማይጠበቅበት ወጪንና መደባለቅን ይከላከላል።
3. ​ለእርጉዝ ሴቶችና ህፃናት፡ ከፍተኛ የደህንነት መረጃ ያለውና በእርግዝና ወቅትም አስምን ለመቆጣጠር በዋናነት የሚመረጥ መድኃኒት ነው።
​⚠️ ማሳሰቢያ፦ የአስም ህክምናዎን ከመቀየርዎ ወይም ማንኛውንም መድኃኒት ከመውሰድዎ በፊት ሁልጊዜ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ሐኪምዎን ያማክሩ!

21/08/2026

።። ?? የቀጣሪው ግዴታዎች ምንድናቸው??? ጠቃሚ መረጃን ይዟል። ይህን ፔጅ ለብዙሀኑ እንዲደርስ share በማድረግ ያጋሩ መልካምነት ለራስ ነው አንድ ቀን መልሶ ይከፍሎታል🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
የግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ መብትና አፈጻጸም መመሪያ
መግቢያ
በኢትዮጵያ የግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ቁጥር 1268/2014 መሠረት፣ ማንኛውም የግል ድርጅት ሠራተኛ የወደፊት ሕይወቱን ዋስትና እንዲያገኝ ተደንግጓል። በእርጅና፣ በጤና ጉድለት ወይም በሞት ምክንያት የሚገጥማቸውን የገቢ መቋረጥ ስጋት ለመከላከል አስተዋጽኦ አለው። ይህ መመሪያ የጡረታ መብትዎን እንዴት ማስከበር እንደሚችሉ እና ግዴታዎችዎን በቀላል ቋንቋ ያስረዳል።
ምዕራፍ ፪፦ የጡረታ መዋጮ እና ምዝገባ
፪.፩ የምዝገባ ግዴታ ማንኛውም የግል ድርጅት ሠራተኛ ስራ በጀመረ በ60 ቀናት ውስጥ በጡረታ ፈንድ መመዝገብ እንዲሁም ለውጥ ካለም ማሳወቅ አለበት።
፪.፪ የመዋጮ መጠን
ከሠራተኛው ደመወዝ፦ 7% (ሰባት በመቶ)
ከአሠሪው (ድርጅቱ)፦ 11% (አስራ አንድ በመቶ)
ድምር፦ 18% በየወሩ ለጡረታ ፈንድ ገቢ መደረግ አለበት።
ምዕራፍ ፫፦ የጡረታ አበል መብት መስፈርቶች
አንድ ሠራተኛ የዕድሜ ጡረታ አበል ለማግኘት የሚከተሉትን ማሟላት አለበት፦
ዕድሜ፦ 60 ዓመት የሞላው።
የአገልግሎት ዘመን፦ ቢያንስ 10 ዓመት ያገለገለ እና መዋጮ የከፈለ። ማሳሰቢያ፦ ከአስር ዓመት በታች ያገለገለ ሠራተኛ አበል ሳይሆን የአንድ ጊዜ ስንብት ክፍያ (Gratuity) ብቻ ነው የሚያገኘው።
ምዕራፍ ፬፦ የጡረታ አበል አሰላሰል (Formula)
የጡረታ አበል የሚሰላው ሠራተኛው ጡረታ ከመውጣቱ በፊት በነበሩት የመጨረሻዎቹ ሦስት ዓመታት አማካይ ደመወዝ ላይ ተመስርቶ ነው።
ለመጀመሪያዎቹ 10 ዓመታት፦ የአማካይ ደመወዙ 30%።
ከ10 ዓመት በላይ ላለው ለእያንዳንዱ ዓመት፦ ተጨማሪ 1.25% ይታሰባል።
ለማንኛውም 10 ዓመታት ላገለገለ የግል ድርጅት ሠራተኛ የሚከፈለው የአገልግሎት ጡረታ አበል መጨረሻ ባገለገለባቸው ሦስት ዓመታት ውስጥ ይከፈለው የነበረው አማካይ ደመወዝ 30 በመቶ ኾኖ ከ10 ዓመታት በላይ ለፈጸመው ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ዓመት አገልግሎት በ1 ነጥብ 25 በመቶ ተጨምሮ ይታሰባል፡፡
ምሳሌ፦ አንድ ሠራተኛ ለ20 ዓመታት አገልግሎ አማካይ ደመወዙ 10,000 ብር ቢሆን፦
ለ10 ዓመቱ = 3,000 ብር (30%)
ለተጨማሪው 10 ዓመት (10 x 1.25%) = 12.5% (1,250 ብር)
ጠቅላላ ወርሃዊ ጡረታ፦ 4,250 ብር ይሆናል።
ምዕራፍ ፭፦ የጉዳት እና የተተኪዎች የጡረታ መብት
የጉዳት ጡረታ፦ በሥራ ላይ በሚደርስ አደጋ ምክንያት መሥራት ለማይችል ሠራተኛ የሚሰጥ።
የተተኪዎች መብት፦ ሠራተኛው ቢሞት ለትዳር ጓደኛ (50%)፣ ለልጆች (20% ለእያንዳንዱ) የጡረታ ክፍያ ይተላለፋል።
ማንኛውም የግል ድርጅት ሠራተኛ የተወሰነለትን የጡረታ አበል በወቅቱ መውሰድ አለበት። የውዝፍ ጡረታ አበል ክፍያ ጥያቄ ከአምስት ዓመታት በኋላ በይርጋ ይታገዳል፡፡
በማንኛውም ፌደራል ፍርድ ቤቶች
ጠበቃ እና የህግ አማካሪ
0943192020

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
ቴሌግራም የቀላቀሉ
👇👇
https://t.me/courtsss/556

21/08/2026

Want to lower your blood pressure
• DASH Diet {(Dietary Approaches to Stop Hypertension) .. low Na high K)} 🥗
• Cut sodium 🧂
• More potassium 🍌
• Lose weight 🏃‍♀️
• Exercise daily 💪
• Less alcohol 🍷

Address

Addis Abeba
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amen home health care Services posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amen home health care Services:

Shortcuts

Share