ጋሞ ልማት ማህበር ጨንቻ ቅርንጫፍ Gamo Devlopment Asso. Chencha Branch

  • Home
  • Ethiopia
  • Arba Minch'
  • ጋሞ ልማት ማህበር ጨንቻ ቅርንጫፍ Gamo Devlopment Asso. Chencha Branch

ጋሞ ልማት ማህበር ጨንቻ ቅርንጫፍ Gamo Devlopment Asso. Chencha Branch ከህዝብ ለህዝብ ተቋም

25/03/2025
25/03/2025
የአርባምንጭ አዞዎች ከቱሪዝም ባሻገር ለቢዝነስ ስራ ሊውሉ ይችላሉ ተባለ~~~~~~~~~👉ጋሞ ልማት ማህበር ከሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ የአርባምንጭ አዞ ራንቺ በማስተዳደር ላይ የሚገኝ ሲሆን ...
25/03/2025

የአርባምንጭ አዞዎች ከቱሪዝም ባሻገር ለቢዝነስ ስራ ሊውሉ ይችላሉ ተባለ
~~~~~~~~~
👉ጋሞ ልማት ማህበር ከሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ የአርባምንጭ አዞ ራንቺ በማስተዳደር ላይ የሚገኝ ሲሆን የጋሞ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዋኖ ዋሎሌ አዞዎችን ከቱሪዝም ባሻገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካህደዋል። ዶ/ር ካሳሁን ደለኔ ለምን በአዞ ላይ ኢንቨስት እናደርጋለን? በሚል ርዕስ የውይይት ሰነድ አቅርበዋል።

👉አዞዎች ከቱሪዝም መስክ ባሻገር ትርፋማ የንግድ እድሎችን እንደሚሰጡ በተለያዩ ጥናቶች ተደርሰውበታል። በታሪክ አዞዎች ከኢኮ ቱሪዝም፣ ከዱር እንስሳት ጥበቃ እና ልዩ ልዩ ሳፋሪስ ጋር የተቆራኙ ሲሆኑ የቅርብ ጊዜ ክስተቶች እንደሚያሳዩት የእነዚህ ጥንታዊ ተሳቢ እንስሳት የንግድ አቅም እንደ ግብርና፣ ፋሽን እና ፋርማሲዩቲካል ፋብሪካዎችም ጭምር ተፈላጊ እየሆነ መቷል።

👉የአዞ ቆዳ አንዱ የገቢ ምንጭ ነው። በዓለም ዙሪያ ያሉ ኩባንያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የአዞ ቆዳ ምርቶች ከቦርሳ እና ከጫማ እስከ የቅንጦት አልባሳት ድረስ በማምረት ለዓለም ገበያ አቅርበው ገቢ እያገኙ ይገኛሉ።

👉በብዙ አገሮች እንደ ጣፋጭ ምግብ ተደርጎ የሚወሰደው የአዞ ሥጋ ሌላይኛው የገቢ ምንጭ ሲሆን ሥጋው በከፍተኛ ፕሮቲን የበለፀገ በመሆኑ የአዞ ሥጋ በአፍሪካ፣ በእስያ እና በአውስትራሊያ ባሉ ክልሎች ለምግብ ኢንዱስትሪው አስተዋጾ በማድረግ አዲስ ንግድ ሆኗል።

👉የአዞ ደም እና ሌሎች ተረፈ ምርቶችም ከፋርማሲዩቲካል ኢንደስትሪው ትኩረት ስቧል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት የአዞ ደም ኃይለኛ ፀረ-ተህዋሲያን ባህሪያት ያለው ሲሆን ለኢንፌክሽን፣ ቁስሎች እና አልፎ ተርፎም ካንሰርን ለማከም ጥቅም ላይ ይውላል። ይህ በአዞ-የተመነጩ ምርቶች ላይ ያለው ፍላጎት እየጨመረ በባዮኢንጂነሪንግ እና በፋርማሲዩቲካል ምርምር ላይ ያተኮሩ ንግዶችን አዲስ ገበያ በመክፈት በጤና አጠባበቅ ውስጥ አዳዲስ እድገቶችን ያስገኛል።

👉በቅንጦት ጌጣጌጥ ኢንዱስትሪ ውስጥ የአዞ ጥርሶች ጥሩ ገበያ አግኝተዋል። የእነሱ ልዩ ሸካራነት፣ መጠን እና ገጽታ ለበለጠ እና ለከፍተኛ ደረጃ መለዋወጫዎች በጣም ተፈላጊ ያደርጋቸዋል። ዲዛይነሮች የአዞ ጥርሶችን በመጠቀም የአንገት ሀብል፣ የጆሮ ጌጥ እና የእጅ አምባሮች ይፈጥራሉ። የአዞ ጥርሶች ለየት ያለ ማራኪነት ከጥንካሬያቸው ጋር ተዳምሮ ለፋሽን ወዳጆች ልዩ የሆነ ተፈጥሮን የተላበሱ የቅንጦት ዕቃዎችን ለሚፈልጉ ማራኪ አማራጭ አድርጎላቸዋል።

👉የጋሞ ልማት ማህበር ም/ሥራ አስፈፃሚ የቢዝነስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማሩ ሞታ የአዞ ውጤታማነት ለማረጋገጥ ከአለም አቀፍ የአዞ ተመራማሪዎች ማህበር ጋር አብሮ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረው በአሁኑ ሰዓት በራንቹ ውስጥ በርካታ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል::

👉ዶ/ር ዋኖ በራንቹ የሚገኙ አዞዎችን ከቱሪዝም ባለፈ ወደ ቢዝነስ በፍጥነት መቀየር እንደሚያስፈልግ ገልፀው የገበያ ትስስር መፍጠር፣ ፕሮጅክቶችን በመቅረፅ ገቢ ማግኘት፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር አብሮ በመሥራት ትርፋማ መሆን፣ ከምርምር ተቋማት ጋር አብሮ መስራት እንዲሁም በስትራተጅክ ዕቅድ ውስጥ በማካተት በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ቅድሚያ ለጋራ ልማት!
መጋቢት 17/2017 ዓ/ም

16/03/2025
16/03/2025

አቶ ምንትስኖት ማትቃ የጨንቻ ከተማ ነዋ ብር 1200 /አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በጋሞ ልማት ማህበር የጨንቻ ቅርንጫፍ የፕላቲኒዬም ደረጃ አባልነትን ተቀላቅሏል።
🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒

አቶ ምንትስኖት ማትቃ የጋልማ ተግባራትን ለመደገፍ በዛሬው ቀን 26/06/2017 ዓ/ም የማህበሩ የፕላቲኒዬም ደረጃ አባልነትን ተቀላቅሏል። ሌሎችም አባል ለመሆን የምትፈልጉ በአካል ወደ ጋልማ ጨንቻ ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ በመምጣት አሊያም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጋልማ ጨንቻ ቅ/ጽ/ቤት አካውንት ቁጥር 1000077546808 ገቢ በማድረግ አባል መሆን እንደምትችሉ እንገልጻለን፡፡

🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒
🌾🌾 ቅድሚያ ለጋራ ልማት! 🌾🌾
🌾የካቲት 26/2017 ዓ.ም! 🌾

16/03/2025

በጨንቻ ዙሪያ አስተዳደር የዳሎና ዛራ ቀበሌ አ/አደሮች 10 ሺህ ብር በመክፈል የጋሞ ልማት ማህበር የ2017 ዓ/ም የአ/አደር አባልነት ዕድሳት አድሷል።

በጨንቻ ዙሪያ አስተዳደር የዳሎና ዛራ ቀበሌ አ/አደሮች በቁጥር 200/ሁለት መቶ/ አ/አደሮች አባልነት መዋጮ 10,000 ብር (አሥር ሺህ ብር) በመክፈል የጋሞ ልማት ማህበር የ2017 የአባልነት ግዴታቸውን በመወጣት ግንባር ቀደም ሆኗል። ለሥራ ትጋታቸው የቀበሌውንና የወረዳውን አመራር ከልብ በጋልማ ጨንቻ ቅርንጫፍ ስም እናመሠግናለን።

ቅድሚያ ለጋራ ልማት!!
የካቲት 26/2017 ዓ.ም
ጋሞ ዞን ጨንቻ

16/03/2025

በጨንቻ ዙሪያ አስተዳደር የዶኮ ሻሌ ቀበሌ አ/አደሮች 12 ሺህ ብር በላይ በመክፈል የጋሞ ልማት ማህበር የ2017 ዓ/ም የአ/አደር አባልነት ዕድሳት አድሷል።

በጨንቻ ዙሪያ አስተዳደር የዶኮ ሻሌ ቀበሌ አ/አደሮች በቁጥር 250/ሁለት መቶ ሃምሳ/ አ/አደሮች አባልነት መዋጮ 12,500 ብር (አሥር ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጋሞ ልማት ማህበር የ2017 የአባልነት ግዴታቸውን በመወጣት ግንባር ቀደም ሆኗል። ለሥራ ትጋታቸው የቀበሌውንና የወረዳውን አመራር ከልብ በጋልማ ጨንቻ ቅርንጫፍ ስም እናመሠግናለን።

ቅድሚያ ለጋራ ልማት!!
የካቲት 27/2017 ዓ.ም
ጋሞ ዞን ጨንቻ

16/03/2025

በጨንቻ ዙሪያ አስተዳደር ቤሌ ቀበሌ አ/አደሮች 10 ሺህ ብር በመክፈል የጋሞ ልማት ማህበር የ2017 ዓ/ም የአ/አደር አባልነት ዕድሳት አድሷል።

በጨንቻ ዙሪያ አስተዳደር የቤሌ ቀበሌ አ/አደሮች በቁጥር 200/ሁለት መቶ/ አ/አደሮች አባልነት መዋጮ 10,000 ብር (አሥር ሺህ መቶ ብር) በመክፈል የጋሞ ልማት ማህበር የ2017 የአባልነት ግዴታቸውን በመወጣት ግንባር ቀደም ሆኗል። ለሥራ ትጋታቸው የቀበሌውንና የወረዳውን አመራር ከልብ በጋልማ ጨንቻ ቅርንጫፍ ስም እናመሠግናለን።

ቅድሚያ ለጋራ ልማት!!
የካቲት 28/2017 ዓ.ም
ጋሞ ዞን ጨንቻ

Address

Gamo Zone
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጋሞ ልማት ማህበር ጨንቻ ቅርንጫፍ Gamo Devlopment Asso. Chencha Branch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share