Aschalew Mobile አስቻለው ሞባይል

Aschalew Mobile አስቻለው ሞባይል Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Aschalew Mobile አስቻለው ሞባይል, Business service, assela, Asella.

05/03/2016
በሞባይል ቪዲዮዎችን, mp3ችን..... እንዴት ዳውንሎድ ማድረግ እንችላለን?ስልኮት አንድሮይድ ሲስተም የሚሰራ ከሆነ (Aplication Markate) ወይም (Play Store) ውስጥገብተው ...
01/03/2016

በሞባይል ቪዲዮዎችን, mp3ችን..... እንዴት ዳውንሎድ ማድረግ እንችላለን?
ስልኮት አንድሮይድ ሲስተም የሚሰራ ከሆነ (Aplication Markate) ወይም (Play Store) ውስጥ
ገብተው (Tube Mate) ብለው ፅፈው ሰርች ያድርጉ ካገኙት በዋላ (Download) ያድርጉ፡፡ ከዛ (Install) ያድርጉ የጫኑትን (Aplication) ይክፈቱ ለምሳሌ ቪዲዮ ከሆነ (YouTube) የሚለውን በመክፈት የሚፈልጉትን (search) የሚለው ውስጥ በመፃፍ የሚፈልጉትን ቪዲዮ (Download) ማድረግ ይችላሉ፡፡ከተመቻቹ share ያርጉ
አስቻለው ሞባይል

እንዴት ሰነበታችሁአይፎን ስልክ በቀላሉ ፎርማት ማድረግ1.መጀመሪያ ኮምፒውተሮ ላይ አብዴት የሆነ iTunes መጫን2.ሞባይሉን በUSB cable ያገናኙና iTunes ስልኩን እስከሚያገኘው ይጠብ...
26/02/2016

እንዴት ሰነበታችሁ
አይፎን ስልክ በቀላሉ ፎርማት ማድረግ
1.መጀመሪያ ኮምፒውተሮ ላይ አብዴት የሆነ iTunes መጫን
2.ሞባይሉን በUSB cable ያገናኙና iTunes ስልኩን እስከሚያገኘው ይጠብቁ
3.ከዛ ካሉት device ዉስጥ የርሶን ስልክ ይምረጡ
3.summary tab የሚለውን በመክፈት 'restore iPhone' የሚለውን ክሊክ ማድረግ Restart አርጎ እስኪጨርስ መጠበቅ
4.ሲጨርስ 'slide to set up' የሚለው ክሊክ በማድረግ ሴቲንጎቹን መሙላት!!
ከአስቻለው ሞባይል ሴንተር
ሼር ያርጉ

ሞባይሎ ብር እየበላ ካስቸሮት ያንብቡት1. እንተርኔት በማይጠቀሙበት ጊዜ የሞባይል ዳታ ያጥፉ2. ኢመል አካዉንትዎ በራሱ ጊዜ አዳዲስ መልእክቶች መኖራቸዉንና አለመኖራቸዉን ቼክ እንዳያደርግ መ...
17/11/2015

ሞባይሎ ብር እየበላ ካስቸሮት ያንብቡት
1. እንተርኔት በማይጠቀሙበት ጊዜ የሞባይል ዳታ ያጥፉ
2. ኢመል አካዉንትዎ በራሱ ጊዜ አዳዲስ መልእክቶች መኖራቸዉንና አለመኖራቸዉን ቼክ
እንዳያደርግ መከልከል (Adjust account sync settings)
3. አንዳንድ አፕልኬሽኖች እርስዎ ሳያቁ ዳታ ሊያወርዱ ስለሚችሉ አፕዴት እንዳያደርጉ
መከልከል (restrict background data)
*3.1, setting
*3.2, data usage
*3.3, ከዛ ወደ ታች ሲወርዱ የሚያገኙትን አፕሊኬሽን አንዴ በመጫን በሚያገኙት ሳጥን ውስጥ የራይት ምልክት /✔/ ማድረግ
4.የተጠቀሙትን የዳታ መጠን ሊያሳይ የሚችል አፕልኬሽን ይጫኑ
6. ትልቅ መጠን ያላቸዉን አፕልኬሽኖች ለመጫን wifi ይጠቀሙ፡፡ ከተመቾት ሼር ያርጉ
አስቻለው ሞባይል ሴናተር
አሰላ

የተዘጋ ስልክ ማለት ምን ማለት ነው ?                        unlock phoneኔትወርክ ሰጪ ድርጅቶች የምንላቸው የሞባይል ኔትወርክ የመስመር ስልክ እናየኢንተርኔት አገልግሎት...
01/11/2015

የተዘጋ ስልክ ማለት ምን ማለት ነው ?
unlock phone
ኔትወርክ ሰጪ ድርጅቶች የምንላቸው የሞባይል ኔትወርክ የመስመር ስልክ እና
የኢንተርኔት አገልግሎት የመሳሰሉትን ለህዝብ የሚያቀርቡ ድርጅቶች ናቸው ። ለምሳሌ
ኢትዮጰያ ውስጥ ያለው የኔትወርክ አገልግሎት የሚሰጠው የኢትዮጰያ ቴሌኮሙኒኬሽን
ኮርፖሬሽን ነው ።
ወደ ሌላ ሀገራት ስንሄድ ከአንድ በላይ የኔትወርክ ሰጪ ድርጅቶች እናገኛለን አንድአንድ
አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች መነሻ ካደረጉበት ሀገር በተጨማሪ አለም አቀፍ እውቅና
ያላቸው ናቸው ። ለምሳሌ T-mobile. Verizone.etisalat.safaricom.me
tropcs.orange.chinamobile.Vodafone.Airtel.Qte.At&t እነዚህ አገልግሎት
ሰጪ ድርጅቶች ሲም ካርድ በመስጠት ደምበኞቻቸውን ለመሳብ ከሚጠቀሙባቸው
መንገዶች አንዱ የሞባይል ቀፎ አምራቾች ከሚሸጡበት ዋጋ ቅናሽ ማድረግ ዋነኛው
ነው ቀፎ አምራቾች የምንላቸው ሳምሰንግ አፕል ኖኪያ ሞተሮላና የመሳሰሉት ናቸው
ኔትወርክ ሰጪ ድርጅቶች ከቀፎ አምራቾችየሚወስዷቸውን ቀፎወች በተወሰነ ቅናሽ
ለደንበኞቻቸው ከሲምካርድ ጋር ይሰጧቸዋል በመጀመርያ ላይ የሚያደርጉትቅናሽ
ለድርጅቱ ትክክለኛ ኪሳራ ነው ሆኖም ደንበኞቻቸው የአየር ሰአት በገዟቸው ቁጥር
ተጠቃሚ ይሆናሉ ነገር ግን በዚህ መንገድ የተገዙ ስልኮች የሌላ ኔትወርክ ሰጪ
ድርጅት የሆነን ሲምካርድ መቀበል አይችሉም ይህ የሆነበት ምክንያት ቀድሞ ያደረጉት
ቅናሽ ስላለ ሴኩሪቲ (ይለፍ) ያደርጉበታል ከላይ በተቀሰው መልኩ የተገዛ ስልክ ወደ
ኢትዮጰያ መቶ የኢትዮጰያ ሲም ካርድ ስናስገባበት ሊሰራ አይችልም ይህም የሆነው
ውጪ ሀገር ያለው ኔትወርክ ሰጪ ድርጅት ያስቀመጠው /ያኖረው/ሴኩሪቲ ይለፍ ስላለ
ነው ። በዚህ መንገድ ሲም አልቀበል ያለ ስልክ የተዘጋ ስልክ እንለዋለን ። ኮምፒዩተር
ሶፍትዌር በመጠቀም የተዘጉ ስልኮችን መክፈት እንችላለን
የተዘጉ ስልኮች የሚከተሉትን ፅሁፎች ያሳያሉ
* sim not valid
* wrong sim
* contact service provider
* unknown sim
* phone restricted
ከውጪ ሀገር የገቡ ስልኮች የምንከፍተው ሀገር ስለቀየሩ አይደለም ። መከፈት
የሚፈልጉ ስልኮች በሙሉ ከአምራች ሳይሆን ከኔትወርክ ሰጪ ድርጅቶች በመጠነኛ
ቅናሽ የተገዙ ስልኮች ናቸው ።
ከአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በቅናሽ የተገዛ ስልክ እዚያው ሀገር ሆነን የሌላን
አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ሲም ካርድ ብንከትበት አይሰራም።
ከአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የገዛነው ስልክ ከሌላ ሲም ጋር ለማዋሀድ /ለመክፈት/
ሁለት አይነት መንገድ አለ አንደኛው መንገድ ኮምፒዮተር ፍላሸር ቦክስ እና ፍላሽ ፋይል
በመጠቀም በራሳችን መክፈት ሲሆን ሁለተኛው መንገድ ደሞ ድርጅቱን በማግኘት
መጠነኛ ክፍያ በመፈፀም ማስከፈት ናቸው ። ክፍያው በኢንተርኔት ግብይት ስርአት (e-
commerce) በመጠቀም መክፈል ይቻላል ። ሁለተኛው መንገድ ለመጠቀም ክሬዲት
ካርድ /cridit card/ያስፈልገናል ። ከተመቾት ሼር ያርጉት
አስቻለው ሞባይል ሴንተር
አሰላ

30/10/2015

Apple ID መክፈት ይፈልጋሉ
1. App Store የሚለውን አፕሊኬሽን እንከፍተዋለን
2. App store ውስጥ የምንፈልገውን አፕሊኬሽን
እንመርጣለን
3. የመርጥነው አፕሊኬሽን ውስጥ በቀኝ በኩል GET የሚል
ይመጣል እሱን ስንነካው እዛው ቦታ ላይ Install የሚል
ይመጣል እሱን እንነካዋለን ከዛ እዛው ቦታ ላይ ክብ
የሚሽከረክር(Processing) ይመጣል
4. ከዛ Sign In የሚል ይመጣል በሱ ስር ደሞ 3
ምርጫዎች ይመጣሉ እነሱም፦
፨Use Existing Apple ID
፨Create New Apple ID
፨Cancel
5. Create New Apple ID የሚለውን እንመርጣለን
6. ከዛ የሃገር ምርጫ(Choose Country) የሚል ይመጣል
ኢትዮጵያ የሚል ስለሌለው UK በሚለው እንጠቀማለን UK
የሚለውን ስንነካው በቀኝ በኩል የራይት(✔) ምልክት
ይሰጠናል ከዛ መጨረሻ በቀኝ በኩል Next የሚል አለ እሱን
እንነካዋለን
7. ከዛ Next የሚለውን የነካንበት ቦታ ላይ Agree የሚል
ይመጣል እሱን ስንነካው በድጋሚ መሃል ላይ Agree የሚል
ይመጣል እሱን እንነካዋለን
8. ከዛ የሚከተሉትን ባዶ ቦታዎች እንሞላለን
፨Email
፨Password
፨Verify
፨Question
፨Answer
፨Question
፨Answer
፨Question
፨Answer
፨Email ይሄ ቦታ ላይ የምንሞላው Email በድንገት
የApple ID Password ቢጠፋብን Reset ማድረጊያ ነው
ደሞ ሁለቱም ላይ የምንሞላው Email የተለያየ መሆን
አለበት።
፨Day
፨Month
፨Year
እነዚህ Day,Month & Year የሚለው የትውልድ ቀናችንን
ነው የምንሞላበት።
9. ከዛ 8ንተኛውን መንገድ ሞልተን ቀጨረስን በዋላ በቀኝ
በኩል እታች ላይ Next የሚለውን እንነካለን።
10. ከታች የተጠቀሱትን እንሞላለን
1.Billing Information
፨Visa
፨MasterCard
፨Amex
፨Maestro
፨None ✔
None የሚለውን ስንነካው ራይት (✔) ምልክት ይሰጠናል።
2.Billing Address
ጥያቄዎች?
1፨Title
2፨First Name
3፨Last Name
4፨Address
5፨Address
6፨Address
7፨Town
8፨Country
9፨Postcode
10፨Phone
መልሶቻቸው።
1፨Mr
2፨የራሳህን ስም
3፨የአባትክን ስም
4፨Highbury
7፨London
8፨England
9፨N5 1FE
10፨የመጀመሪያው ሳጥን ውስጥ 0844 አስገቡ እዛው
አጠገቡ ጋር ያለው ሳጥን ውስጥ 4129958 ይሄን አስገቡ።
"5-6" ጥያቄዎች ባትሞሉትም ችግር የለውም።
11. ከዛ 10ኛውን መንገድ ሞልተን ቀጨረስን በዋላ በቀኝ
በኩል እታች ላይ Next የሚለውን እንነካለን።
12. Verify Email የሚል ይመጣል ከዛ ከላይ በቀኝ በኩል
Done የሚለውን እንነካለን።
13. Email አችንን ስንከፍተው Verify Your Apple ID
የሚል እናገኛለን ከዛ ስንከፍተው Verify now የሚለው ስር
ሊንክ አለ እሱ ውስጥ ስንገባ Apple ID እና Password
አችንን አስገብተን Verify Address የሚለውን ስንጫን
Email Address Verified የሚል ይመጣል።
14. ከዛ Setting->iTunes & App store ውስጥ ገብተን
Apple ID እና Password አችንን እናስገባለን ከዛ
የምንፈልገውን Application Download ማረግ እንችላለን፡፡
አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ
አስቻለው ሞባይል ሴንተር
አሰላ

የሞባይል ጀነሬሽን ምንድነው                               1G /first Generation/የመጀመሪያው የሞባይል(wirless) ዘመን ማለት ሲሆን የአናሎግ ግንኙነትየተደመረ...
29/10/2015

የሞባይል ጀነሬሽን ምንድነው
1G /
first Generation/
የመጀመሪያው የሞባይል(wirless) ዘመን ማለት ሲሆን የአናሎግ ግንኙነት
የተደመረው በ1980ዎቹ አካባቢ ነበር፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ አውቶሜትድ የሆነ
ስልክ በጃፓን NTT(NIPPON Telegraph and Telephone) ድርጅት
ለገበያ ቀረበ፡፡አምስት አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መላውን የቶኪዮ ከተማ
በማገናኘት ጃፓን የአለማችን የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ 1G ኔትውርክ ባለቤት
ሆነች፡፡
2G
/second Generation/
ሁለተኛው የሞባይል ዘመን ማለት ሲሆን ይህ ዘመን ከ 1G(first
Generation) የሚለየው ዲጅታል ራዲዮ ሲግናል መጠቀም መጀመሩ ነበር፡፡
GSM( Global System for Mobile ) አሁን ኢትዮጲያ ውስጥ
የምንጠቀምበት የሞባይል ሲም ካረዶች ናቸው( የሲም ካረዱን ጀርባ ይመልከቱ
GSM የሚል ጽሁፍ አለው )፡፡
ወደ 3G ከመሄዳችን በፊት
2.5g ስለሚባለው ጊዜ እንይ
ይህ ጊዜ የ2G ኔትዎርክ ላይ ተጨማሪ ቴክኖሎጂ ከ3G በመውሰድ የተፈጠረ
ነው፡፡ፓኬት ዳታ ቴክኖሎጂን ከ GPRS( General Packet Radio
Services) ጋር ያስተዋወቀ ነው፡፡ ኢንተርኔትን ወደ ሞባይል ያመጣም ነበር፡፡
GPRS የ28 Kbps ዳታ ፍጥነት አለው፡፡
3G
/3rd Generation/
ትልቅ ፈጥነት ያለው ኔትዎርክ ሲሆን ፈጥነት ለሚፈልጉ እንደ ቪዲዮ ስልክ
ግንኙነት አይነት የተሰራ ነው፡፡ 200 kbit/s ዳታ የማስተላለፍ ፍጥነትም
አለው፡፡ እንደ iphone , android , Samsung እና ሌሎች እስማርት ስልክ
ለሆኑ የተዝጋጀ ነው፡፡ ሞባይል ቴሌቪዥንም የተዋወቀው በዚሁ ነው፡፡
4G
/4th Generation/
Ultra broadband internet አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ለምሳሌ ለላፕቶፕ
ዋየርለስ ሞደም በዩኤስቢ ፣ አፒ ስልክ (IP telephony ) ፣ HD ሞባይል
ቴሌቪዥን ፣ ቪዲዮ ኮንፍርነስ ፣3ዲ ቴሌቪዥን አገልግሎቶች አሉት፡፡ ipv6
ኔትዎርክ የሚጠቀም ነው፡፡
5G
/5th Generation/
በ2020 ይጠብቁ
አንብቡው ሲጨርሱ share ያርጉ
አስቻለው ሞባይል ሴንተር
አሰላ

የሞባይል ባትሪዎን እድሜ ማሰረዘም ይፈልጋሉ1.በኦርጅናል ቻርጀር /ቢቻል በተመሳሳይ ሞዴል / መጠቀም2. ቻርጅ ሰክተን አለመጠቀም ስልኩ ስለሚግል ባትሪውን ያሳብጣል3. ሰልክን ሌሊቱን ሙሉ ቻ...
27/10/2015

የሞባይል ባትሪዎን እድሜ ማሰረዘም ይፈልጋሉ
1.በኦርጅናል ቻርጀር /ቢቻል በተመሳሳይ ሞዴል /
መጠቀም
2. ቻርጅ ሰክተን አለመጠቀም ስልኩ ስለሚግል ባትሪውን ያሳብጣል
3. ሰልክን ሌሊቱን ሙሉ ቻርጂ እና (100% battery full )ካለ ቶሎ መንቀል
4፡ የ ሰልካችን የችርጂ መጠን 0% እስኪሆን መጠቀም የለብንም
5: ቢቻለ በ3ቀን አንዴ ለተወሰነ ሰዓት ስልኩን ማጥፋት

27/10/2015

የ3ጂ/ 4ጂ ሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎትዎን ለመቆጣጠር
ጠቃሚ ምክሮች!
1.የኢንተርኔት አጠቃቀምን መመጠን
የተለያዩ መተግበሪያዎች/Applications/ ሙሉ በሙሉ ስራ
ላይ በሚሆኑበትጊዜየተለያየ መጠን ያለው
ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፣
ለምሳሌ:- ቪዲዮ የሚያጫውቱ እንደ ዩቲዩብ/youtube/ እና
ፌስ ቡክ/facebook/ ያሉ መተግበሪያዎች ከሌሎች
መተግበሪያዎች ይልቅ ከፍተኛ መጠን ያለው ኢንተርኔት
ይጠቀማሉ፡፡ በመሆኑምስልክዎ ላይ ጭነው
የሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች የሚጠቀሙትን የኢንተርኔት
መጠን ለመቆጣጠር የሚከተለውን ቅደም ተከተል መተግበር
ይችላሉ፡
ሴቲንግ /Setting/ ውስጥ Data usageን ይመርጣሉ>
mobile data ውስጥ > data usage cycle የሚለው ላይ
> ቀስቶቹን በማንቀሳቀስ ምን ያህል መጠን ያለው ኢንተርኔት
በምን ያህል ጊዜ ውስጥ መጠቀም እንደሚፈልጉ መመጠን
ይችላሉ፡፡
2. በራስ መር ማዘመንን /Update/ ማጥፋት
ስልክዎ ላይ የተጫኑ ሶፍትዌሮች ወይም መተግበሪያዎች
እንዲዘምኑ /Update/ ካልፈቀዱ በስተቀር በራሳቸው ጊዜ
ያለርስዎ ፈቃድ እንዳይዘምኑበማድረግ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡
3. ቪዲዮ ሙዚቃእና ጌም በቀጥታ ከኢንተርኔት ላይ
መመልከት/መጫወት ከፍተኛ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ
ቪዲዮዎች እና ሙዚቃዎችንበቀጥታ ሲመለከቱ ወይም
ሲያወርዱ በተለይ ደግሞ ጥራታቸው ከፍ ያሉ ቪዲዮዎችእና
ሙዚቃዎችከሆኑከፍተኛ የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፡፡
በአንዳንድ አጋጣሚዎችከፍተኛ ጥራት ያለው ቪዲዮ እና
ሙዚቃንመምረጥ በጥራት ዝቅተኛ ከሆነ ተመሳሳይ ይዘት
ካለው ቪዲዮ እና ሙዚቃበሁለት እጥፍ የሚልቅ የኢንተርኔት
ፍጆታ ይጠቀማሉ፡፡
ለምሳሌ:- በሞባይልዎ ከዩቲዩብ (youtube)ቪዲዮ እና
ሙዚቃንእየተመለከቱ ከሆነ ጥራቱንዝቅ በማድረግ
የኢንተርኔት አጠቃቀምዎንመመጠን ይችላሉ፡፡ይህንን
ለማድረግ:-
3.1. ስልክዎ ላይየዩቲዩብ/youtube/ መተግበሪያን ይክፈቱ
3.2. ሜኑ የሚለው ውስጥ ጄነራል/General/ን ይምረጡ
3.3. High Quality on Mobile የሚለውን ያልተመረጠ /
Un-tick/ በማድረግ የቪዲዮውን ጥራት ዝቅ
ማድረግ ይችላሉ፤
ያስተውሉ:
ከፍተኛ ጥራት ያለው ሙዚቃ(ምስል የሌለው) በ(256kbps)
የጥራት መጠን ሲጠቀሙ በሰዓት እስከ 100 ሜጋባይት
የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፣
በተመሳሳይ ሁኔታቪዲዮ በHD ጥራት ሲመለከቱ በሰዓት እስከ
1ጂቢ የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፡፡
ጌሞችን ከኢንተርኔት በቀጥታ እየተጠቀሙ ከሆነበሰዓት ከ10
እስከ 80 ሜ.ባ ድረስ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፡፡
4. መተግበሪያዎች ማሳወቂያ/Notification/ እንዳይልኩ
ማድረግ እና ከጀርባ በኩል/Background/ ኢንተርኔት
እንዳይጠቀሙ ማገድ:-
አንዳንድ መተግበሪያዎች እየተጠቀሙባቸው ባይሆንም
በውስጥ በኩል እርስዎ ሳያውቁ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፤
ለምሳሌ:- የተሻለ የመተግበሪያው/Application/ ስሪት
ሲኖር ራሳቸውን ያዘምናሉ።
ስለዚህ መተግበሪያዎችን ስልክዎ ላይ ሲጭኑ
ስለመተግበሪያው የተለያዩ ማሳወቂያዎች/notifications/
እንዲደርስዎ ይፈልጉ እንደሆነሲጠየቁ መከልከል እንዲሁም
አካባቢዎን ፈልጎ እንዲያገኝ ፈቃድ ሲጠየቁ
ባለመፍቀድ የኢንተርኔት አጠቃቀምዎንመመጠን ይችላሉ፡፡
የጫኗቸውን መተግበሪያዎች ማዘመን /አፕዴት ማድረግም
ሆነመጠቀም ሲፈልጉ ብቻራስዎ ገብተው እንዲፈቅዱ
አድርገው መጫን ይችላሉ፤በዚህ መንገድ እርስዎ ሳይፈቅዱ
ስልክዎ በውስጥ በኩል ኢንተርኔት እንዳይጠቀም ማድረግ
ይችላሉ፡፡
5.የማይጠቀሙባቸውን መተግበሪያዎች ከስልክዎ ማጥፋት
አንዳንድ መተግበሪያዎች ባይጠቀሙባቸውም ስልክዎ ላይ
በመጫናቸው ብቻ ኢንተርኔት ሊጠቀሙ ስለሚችሉ
የማይፈልጓቸውን መተግበሪያዎች በማጥፋት ወይም /
Uninstall/ በማድረግ የኢንተርኔት አጠቃቀምዎን
መቆጣጠር ይችላሉ፡፡
6.ያልተላኩ መልዕክቶችን ማጥፋት
በስልክዎ ኢሜይል የሚልኩ ከሆነእና ያልተላከ መልዕክት
ማስቀመጫ ሳጥን /outbox/ ውስጥ መልዕክት ካለዎት፣
የሞባይልዎን ኢንተርኔት በሚያበሩበት ጊዜመላክ ይፈልጉ
እንደሆነለመጠየቅ ዝግጁ ስለሚሆኑኢንተርኔት ይጠቀማሉ፡፡
በተለይ ደግሞ ትላልቅ አባሪዎችን መልዕክቱ ላይ አይይዘው
ከሆነ ከፍተኛ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፤ ስለዚህ ያልተላኩ
መልዕክቶች ውስጥ ያሉ መልዕክቶችን በማጥፋት የኢንተርኔት
አጠቃቀምዎንመመጠን ይችላሉ፡፡
7.የኢሜይል ሴቲንግ
በሞባይልዎ የኢሜይል አገልግሎት የሚጠቀሙ ከሆነ በምን
ያህል የጊዜገደብ አዳዲስ ኢሜይሎች ሲገቡ
እንደሚያሳውቅዎመወሰን ይችላሉ፡፡
ለምሳሌ:- ሁልጊዜም አዲስ ኢሜይል ሲገባ ሊሆንይችላል፣
በየ10 ደቂቃው ወይም እርስዎ በወሰኑት ጊዜሊያደርጉት
ይችላሉ፡፡የኢንተርኔት አጠቃቀምዎንለመመጠን ይህን ሴቲንግ
መቀየር ከፈለጉ፤
7.1 የስልክዎ 'email' ላይ የሚጠቀሙትን የኢሜይል አይነት
ይምረጡ ለምሳሌ (POP3, IMAP,
Exchange)
7.2 በመቀጠልም ቅደም ተከተሉን በመከተል፣ በምን ያህል
ጊዜአዲስ ኢሜይል መግባቱን ማሳወቅ እንዳለበት
መወሰን ይችላሉ፡፡
ስለዚህ እነዚህ አገልግሎቶች ኢንተርኔትዎን በከፈቱበት ወቅት
ሁሉበውስጥ ከጀርባ/በኩል ኢንተርኔት ስለሚጠቀሙ
ካልፈለጉት በሚከተለው ዘዴ ማጥፋት ይችላሉ፡፡
እንደ ስልክዎ አይነት በጥቂቱ ቢለያይም በአብዛኛዎቹስልኮች
ላይ ሴቲንግ ውስጥ location ወይም location settingን
በመምረጥ እና የመገኛ አካባቢዎ በዋይ ፋይ ብቻእንዲገኝ
በመፍቀድ፤ የኢንተርኔት
አጠቃቀም መጠንዎን መቆጣጠር ይችላሉ፡፡
9.ከአገር ውጪሲሆኑየኢንተርኔት ሮሚንግን ማጥፋት
ሲም ካርድዎን ከአገር ውጪበሚሄዱበት ጊዜመጠቀም
እንዲችሉ የሮሚንግ አገልግሎት ለማግኘት ከኢትዮ ቴሌኮም
ጋርውል ፈጽመውከሆነ የሞባይልኢንተርኔትን በማጥፋት
ቁጥጥር ማድረግ ይችላሉ።
ይህን ለማድረግ የሚከተለውን ቅደም ተከተል ይተግብሩ።
ስልክዎ አንድሮይድ የሚጠቀም ከሆነ Settings ውስጥ >
Wireless & Networks የሚለውን ይመርጣሉ> Mobile
Networks ውስጥ በመግባት > Data Roaming
የሚለውን በማጥፋት የኢንተርኔት አጠቃቀምዎንመገደብ
ይችላሉ፡፡
ስልክዎ አይፎን/ iPhone ከሆነ: Settings ውስጥ >
General የሚለውን ይመርጣሉ ከዚያም> Network ውስጥ
> Data Roaming የሚለውን በማጥፋት የኢንተርኔት
አጠቃቀምዎንመገደብ ይችላሉ፡፡
10.ዋይ ፋይ ሲጠቀሙየሞባይል ኢንተርኔትዎን ማጥፋት
የዋይ ፋይአገልግሎት በሚያገኙበትአጋጣሚሞባይል
ኢተርኔትዎን በማጥፋት የኢንተርኔት አጠቃቀምዎን መቆጣጠር
ይችላሉ፡፡
11.ሆትሰፖት እና ቴዘሪንግ/ Hotspots and tethering/
የስልክዎን ኔትዎርክበሌላ መሳሪያ መጠቀም ከፈለጉ እና
ስልክዎን እንደ ዋይ ፋይሆት ሰፖት አድርገውት ከሆነ
ወይም በዩ.ኤስ.ቢ ሚጠቀሙበት ከሆነ ያገናኟቸው
መሳሪያዎች ለምሳሌ ኮምፒውተር ቢሆን ከፍተኛ ኢንተርኔት
ስለሚጠቀሙ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብዎታል፡፡ሌሎች
ሰዎችም የእርስዎን ስልክ ኔትዎርክ እንደዋይፋይ
ሊጠቀሙበት
ስለሚችሉ የምስጢር ቁጥር በማስገባት መቆጣጠር ይችላሉ፡፡
12.የሞባይል ኢንርኔትን ማጥፋት
ከላይከተገለጹት የጥንቃቄ ነጥቦች በተጨማሪ ኢንተርኔት
መጠቀም በማይፈልጉበት ጊዜየሞባይልዎን የኢንተርኔት
በማጥፋት በአግባቡ ይጠቀሙ፡፡
አስቻለው ሞባይል ሴንተረ
አሰላ

12/09/2015

Address

Assela
Asella
ASCH2323

Telephone

0911759158

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Aschalew Mobile አስቻለው ሞባይል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share