31/03/2023
አሏህ ሆይ
ዳግም ወደኃላ ወደማንመለስበት ቀጥተኛ መንገድ ምራን:: ደስታን አግኝተን ዳግም የማናዝንበትን ደስታ ለግሰን::
እዝነትህን አውርድልን
ጌታችን ሆይ
የምንፈራው ነገር ሁሉ ለኛ ከባድ ነው አንተ ያቀለልከው ሲቀር፣ የምንፈራውን ሁሉ አቅልልን ፣ ከፈራነው ነገርን ሁሉ አንተ ጠብቀን
ቸሩ ጌታችን ሆይ
በዚህች በተከበረች ወቅት ካንተ ውጪ ችግሩን እና ጭንቀቱን የሚረዳለት ለሌለው ባሪያህ እዘንለት
በብዙ ጭንቀት እና መከራ ውስጥ ላሉት ባሮችህ ሁሉ ፈረጃውን ቅርብ አድርግላቸው
አዛኙ ጌታችን ሆይ
እየፆምን ያለውን የረመዷን ፆም ተቀበለን::ጉድለታችንንም በእዝነትህ እለፈን:: በየቀኑ ከእሳት ነፃ ከምታወጣቸው ባሮችህ መድበን
* አሏህ ሆይ ሰላምና እዝነትን በነብያችንና በተወዳጁ ሙሀመድ(ሰዓወ) ላይ እንዲሁም በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ በሙሉ ላይ ይወረድ
አሚን
Ustaz abubeler Ahmed