14/03/2024
ይጠቀሙበታል ያሉትን ገፆች እስተዋውቀዋል
| በአዳዲስ የቢዝነስና የሥራ ፈጠራ ሃሳቦች አፍላቂ ናቸው ይሏቸዋል፡፡እውቅ ኢኮኖሚስት እና ኢንተርፕርነር፡፡ባህር ማዶ በግዙፍ የፋይናንስ ማእከል ኢንቨስትመንት ባንክ ውስጥ እውቅ ባለሙያ ሆነው አገልግለዋል፡፡ ወደአገራቸው ከተመለሱ በኋላ ስኬትና ውድቀት፣ፈተናና እና ውዝግብ ሳይለያቸው ከ2 አስርት አመታት በላይ አሳልፈዋል፡፡
‹‹የማይሰበረው›› በሚል ርእስ በታተመ የሕይወት ታሪካቸው ብዙዎችን ማደስደነቅ የቻለ የሕይወት ተሞክሮን ማካፈል ችለዋል፡፡
በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ‹‹ለተሻለ ነገ እናንብብ›› የንባብ ዘመቻን የተቀላቀሉት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ እንዲህ የሚል መልእክት ልከዋል፡፡
‹‹እናንተ የኢትየጵያ ወጣቶች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን፡፡ ዕውቀትን መነሳሳትን እና መነቃቃትን የምታገኙባቸውን የመስመር ላይ የመረጃ ምንጮች ለእናንተ ላካፍል በመቻሌ ደስተኛ ነኝ፡፡ ባለንበት ዓለም ትምህርትን የማግኛ መንገዶች በዓይነት እየበዙ መጥተዋል፡፡››
በሕይወቱ ውስጥ ብዙ ቁም ነገሮች እያገኘባቸው ያሉ የመረጃ ምንጮች ድረ ገጾች ናቸው፡፡ እነዚህ ድረ ገጾች ሰፊ የሥልጠና እና የትምህርት ምንጭ ከመሆናቸውም ባሻገር በምትፈልጉት ዘርፍ ልኅቀትን ትጎናጸፉ ዘንድ ራሳችሁን ለማረቅ ይጠቅሟችኋል፡፡ በዕውቀት ጎዳና ሩቅ እና ጥልቅ ለመጓዝ የሚያስችሉ አዳዲስ ክኂሎችን ለማግጎልበት እያንዳንዱ የመረጃ ምንጭ ቀጣይ ሕይወታችሁን እንድትሠሩና የውስጣችሁን አቅም እንድታወጡ መንገድ ከፋች ይሆንላችኋል›› በማለት በርከት
ያሉ የኢትዮጵያ ወጣቶች ቢጎበኟቸው እና ቢጠቀሙባቸው በብዙ ይጠቀሙበታል ያሉትን ገፆች እስተዋውቀዋል፡፡
ከእነዚህም መካከል
1. TED-Ed (https://ed.ted.com/) - Offers a wide range of educational videos and lessons on various topics, including psychology, motivation, and life skills.
2. Psychology Today (https://www.psychologytoday.com/intl) - Provides insightful articles, blogs, and resources on psychology, mental health, and personal development.
3. MindTools (https://www.mindtools.com/) - Offers practical resources and tools for personal development, leadership skills, and career advancement.
4. Positive Psychology Program (https://positivepsychology.com/) - Features articles, exercises, and resources focused on positive psychology, happiness, and well-being.
5. Brain Pickings (https://www.brainpickings.org/) - Curates insightful articles, book recommendations, and quotes on various topics, including literature, psychology, and philosophy.
6. The School of Life (https://www.theschooloflife.com/) - Provides educational content, courses, and resources aimed at developing emotional intelligence, resilience, and life skills.
TED-Ed celebrates the ideas of teachers and students around the world. Discover hundreds of animated lessons, create customized lessons, and share your big ideas.