17/07/2026
"ሿሿ" የተሠራው የኢትዮጵያውን ሙስሊሞች ብዛት
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
የትክክለኛ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ማኅበረሰብ ዝም ብሎ በወረቀት ላይ የሚሰፈር የቁጥር ጉዳይ አይደለም፤ የህልውና፣ የፍትህ እና እኩል የመታየት ጥያቄ ነው። ማኅበረሰቡ የ1999 ዓ.ል. (እ.ኤ.አ የ2007ቱን) ቆጠራ በሙሉ ልቡ ያልተቀበለበት በርካታ ምክንያቶች አሉት።
"ሙስሊሞች ብዙ የሚመስሉት ሂጃብ ስለሚያደርጉ ነው"
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢
የ1999 የሕዝብ ቆጠራ ዉጤት የሕዝበ ሙስሊሙ ቁጥርን ሆነ ተብሎ የማሳነስ ሸፍጥ ሥራ የተሠራበት ነው።አንዳንዶቹ ያፈጠጡና ያገጡ ነበሩ። ለምሳሌ በወቅቱ በሕዝበ ሙስሊሙ ልሂቃን፣ሚዲያዊችና ጥቂት ሙስሊም ባለ ስልጣናት ዘንድ ተቃውሞና ትችት አስተናግደው ነበር።
የቆጠራው ሪፖርት በሁሉም ስፍራ የሙስሊሙን ቁጥር ዝቅ አድርጎ ቢያቀርብም በተለይ ደግሞ የሙስሊሞች ቁጠር በኦሮሚያ ክልል 47. 5%(አርባ ሰባት ነጥብ አምስት በመቶ)፣ ቤኒሻንጉል ክልል 45.4%(አርባ አምስት ነጥብ አራት በመቶ)፣አዲስ አበባ ከተማ 16. 2%(አስራ ስድስት ነጥብ ሁለት በመቶ) ፣አማራ ክልል 17.2%(አስራ ሰባት ነጥብ ሁለት በመቶ) ፣ ደቡብ ክልል(ሳይከፋፈል) 14. 1%(አስራ አራት ነጥብ አንድ በመቶ) ፣ትግራይ ክልል 4%( አራት በመቶ) እንደሆነ ተደርጎ መቅረቡ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሮ ነበር።
ለተናሳው የሕዝበ ሙስሊም ተቃውሞ የያኔዋ የስታስቲክስ ባለስልጣን አመራር ሙስሊሞች ከቆጠራው ሪፖርት ይልቅ መሬት ላይ ብዙ መስለው የሚታዩት ሂጃብ ስለሚያደርጉ ነው የሚል አስቂኝ ምላሽ ሰጥተውም ነበር።
1999ኙ የሕዝብና ቤት ቆጠራ በክልል ደረጃ ብቻ ሳይሆን ሙስሊም የሚበዛባቸውን ዞኖች፣ከተሞችና ወረዳዎችን ጭምር የሙስሊሞችን ቁጥር አሳንሶ በማቅረብ በመጨረሻም በኢትዮጵያ የሙስሊሞች ከሀገሪቱ ሕዝቦች መካከል 33. 8%(ሰላሳ ሦስት ነጥብ ስምንት በመቶ) አድርጎ አቅርቧል።
የቆጠራ ውጤቱ መዘዝ
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
ቆጠራው የማኅበረሰቡን ትክክለኛ ገጽታና ስፋት ከማሳየት ይልቅ፣ በፖለቲካ ፍላጎት ተጠምዝዞ የሙስሊሙን ቁጥር ሆን ተብሎ ከእውነታው አሳንሶ ለማሳየት የተሰራ ስህተት እንደነበር በጽኑ ያምናል። ይህ ደግሞ በሀገር፣ በክልልና በወረዳ አስተዳደሮች ውስጥ ልናገኝ የሚገባንን ተሳትፎ እና ፍትሃዊ ውክልና ነፍጎናል።
የዚህ የተዛባ ቆጠራ አደጋ አንዴ ተከስቶ የሚያበቃ አልነበረም። የቆጠራ ውጤት ቢያንስ ለአስር ዓመታት የሀገርን ሀብትና በጀት ለመከፋፈል የሚያገለግል በመሆኑ፣ በሙስሊሙ አብላጫ አካባቢዎች ሊሰሩ የሚገባቸው መንገዶች፣ ልጆቻችን የሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች፣ እና እናቶቻችን የሚታከሙባቸው የጤና ተቋማት ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ እንዲታለፉ አድርጓል።
ከምንም በላይ ደግሞ፣ አምልኳችንን የምንፈፅምበት መስጊድ እና የምናርፍበት የመቃብር ቦታ ለማግኘት ስንጠይቅ "በአካባቢው ያላችሁ ቁጥር አነስተኛ ነው" በሚል ሰበብ ማኅበረሰቡ በገዛ ሀገሩ መብቱን እንዲገፋና የባህልና የቋንቋ ተጽዕኖ እንዲደርስበት ትልቅ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል።
ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው የቆጠራው ሂደት ግልጽነት ስለጎደለው ነው። የማኅበረሰቡን ቋንቋና ባህል የማያውቁ ቆጣሪዎችን በማሰማራት፣ መረጃዎችን በመደበቅ፣ እንዲሁም ሰፊ መልክዓ ምድር ላይ የሚኖረውን አርብቶ አደር ሙስሊም በበቂ ሁኔታ በጀትና የሰው ሀይል ሳይመደብለት ከቆጠራ ውጭ እንዲሆን ተደርጓል።
ዛሬ ላይ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄ ግልጽና ቀጥተኛ ነው፤ አሁን የምንፈልገው ሌላውን የሚጎዳ ሳይሆን ሁላችንም በሀገራችን እኩል የምንታይበት፣ የሃይማኖት አባቶችና የማኅበረሰብ መሪዎች በታዛቢነት የሚሳተፉበት፣ ከማንኛውም የፖለቲካ ጫና ነፃ የሆነ፣ እና እውነተኛ ገጽታችንን የሚያሳይ ፍትሃዊ ቆጠራ እንዲካሄድልን ነው። እኛ እኩል መቆጠር የምንፈልገው ሀገራችንን በእኩልነት ለመገንባት ነው።
ትክክለኛ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ማካሄድ እጅግ አስፈላጊና ወሳኝ ጉዳይ ነው። የሚከተሉትን ነጥቦችን በማየት የአጀንዳውን አስፈላጊነትን መረዳት ይቻላል።እነርሱም፦
1) የሕዝብ ብዛትን ይወስናል፦ በትክክል ያልተቆጠረ የሕብረተሰብ ክፍል ከእውነታቸው ጋር በሚቃረን መልኩ የሕዝቡ ብዛት አንሶ ወይንም በዝቶ ሊገለጽ ይችላል፤ ይህም የትኛው ህዝብ ብዙሃን የትኛው ህዝብ አናሳ ተብሎ እንደሚበየን ይወስናል።
2) ተገቢ ያልሆነ ዉክልና፦ የሕዝብ ቁጥር መዛባት አንድ የሕብረተሰብ ክፍል በመንግስት ተቋማት፥በየደረጃው ባሉ የክልል፥የዞን፥የወረዳና የከተማ ምክርቤቶች በተመራጭ ዉክልናው መጠን ላይ ከተገቢው በታች የመወከል አልያም ከተገቢው በላይ የመወከል ሁኔታን ሊፈጠር ይችላል።
3) የሕዝብና ቤት ቆጠራ ዉጤት በመሆኑ መንግስት ምን ዓይነት ፖሊሲ መከተል እንዳለበት በመወሰን አንድን የሕብረተሰብ ክፍል በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ ሌላውን ተጎጂ ያደርጋል።
4) ቆጠራው ለ10 እና ከዚያ በላይ ዓመታት የሚደረግ በመሆኑ አንድ ጊዜ የሚደረግ ቆጠራ የሕብረተሰቡን የሕዝብ እድገት መጠን ለመተንበይ አገልግሎት ላይ የሚዉል በመሆኑ በቆጠራውና በቀጣይ በሚኖረው ትንበያ መሠረት የበጀት ክፍፍል፥ የጤና፥የትምህርትና ሌሎች ወሳኝ ተቋማት ግንባታ አስፈላጊነት፥አዲስ ወረዳ ወይም ቀበሌ ይዋቀር የሚለውን ጉዳይ ለመወሰን የሕዝብ ቁጥር ከግምት የሚገባ በመሆኑ የቆጠራው መዛባት ጉዳቱ አንድ ጊዜ ብቻ የሚከሰት ሳይሆን ዓመታትን የሚሻገር ነው።
5) የቆጠራ ዉጤት ክህዝብ ብዛት ባሻገር ስለ የገቢ ምንጭና ድህነት፥ እድሜ፥የትምህርት ደረጃ፥ የሥራ ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን የሚያካትት በመሆኑ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ልዩ ተጠቃሚ አልያም ተጎጂ የማድረግ እድሉ ከፍተኛ ነው።
6) የህዝብና ቤት ቆጠራ ዉጤት ላይ ተንተርሰው ከሚታቀዱት ነገሮች መካከል የመንገድ ግንባታ፥ የትራንስፖርት ስምሪት፥የቤቶች ግንባታ፥የከተማ ፈጠራ፥የከተማ ደረጃ ምደባ፥የኤልክትሪክና የስልክ መስመር ዝርጋታ ወዘተ ይጠቀሳሉ። የተሳሳተ ቆጠራ ዉጤት ላይ በመንተራስ ለአንድ አከባቢ ሕዝብ ዝቅተኛ መሠረተ ልማቶች ለሌላው ደግሞ ከፍያለ መሠረተ ልማት እንዲታቀድና እንዲሰራ ያደርጋል።
7) ለሃይማኖት ተቋማት የቦታ አሰጣጥ ላይ የወጡ መመሪያዎች የሃይማኖቱ ተከታዮች የቦታ ጥያቄ በቀረበበት አከባቢ ምን ያክል ብዛት ያላቸው የሃይማኖት ተከታዮች አሉ? የሚለውን በዋነ መስፈርት የሚጠቀም በመሆኑ የአንድ ሃይማኖት ተከታይ ወደኖች ለእምነት ተቋማት የሚሰጣቸውን የመሬት አቅርቦት መጠን ይወስናል።
8) የሕዝብ ቆጠራ ዉጤት መዛባት የአንድን ዞን፥ወረዳ ወይም ከተማ አብዛኛው ሕዝብ የየትኛው ቋንቋ ተናጋሪ እንደሆነ ለማወቅና የትኛው ቀንቋ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ለመሰን የሕዝብና ቤት ቆጠራ ዉጤት አገልግሎት ላይ የሚዉል በመሆኑ በቆጠራው አንሶ የተቆጠረው የሕብረተሰብ ክፍል ሲጎዳ ቁጥሩ ከፍ ብሎ በቆጠራው የታየውን የሕብረተሰብ ክፍል በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ ያደርጋል።
የተሳሳተ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ምክንያቶች
🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒
1) ያልተሟና ትክክለኛ ያልሆነ የመረጃ አሰባሰብ፦ ቆጠራው በአቆጣጠር ስልት ችግር፥ ብቃት የሌላቸው ቆጣሪዎች፥እና ሌሎች ምክንያቶች ትክክለኛና ሙሉ መረጃ ባለመሰባሰብ የቆጠራ ዉጤት ሊዛባ ይችላል።
2) ከእውነታው በታች የመቆጠር፦ አንዳንድ የሕብረተሰብ ክፍሎች ከአኗኗር ዘይቤያቸው፥ ከአሰፋፈራቸውና ከሚኖሩበት መልከዓምድር የተነሳ አልያም ሆነ ተብለው ሳይቆጠሩ ተዘለው፥ ቆጣሪዎች በሚሰሩት ሸፍጥ ወይንም ስለቆጠራው ዓላማና ጥቅም ካለመረዳት ቆጠራውን በስጋት በማየት ራሳቸው ያነሰ መረጃ በመስጠታቸው የተነሳ ከእውነታው በታች ሊቆጠሩ ይችላሉ።
3) ከእውነታው የበለጠ መቆጠር፦ በተቃራኒው አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች ስለሕዝብና ቤት ቆጠራ ጥቅም በመረዳታቸው ከፍ ያለ ቤተሰብ ሲያስመዘግቡ አልያም ቆጣሪዎቹ የሚፈልጉትን የሕብረተሰብ ክፍል መረጃ ከፍ አድርገው በመሙላታቸው የተነሳ ከእውነታቸው ከፍ ባለደረጃ ሊቆጠሩ ይችላሉ።
4) የቆጠራ ዉጤት መረጃን በአግባቡ ካለመጠበቅ የሚመጣ የዉጤት መዛባት፦ ቆጠራው ተጠናቆ ካበቃ በኋላ ማንኛውም የቆጠራውን ዉጤት ማግኘት የቻለ አካል ሆነ ብሎ ዉጤቶቹን በማዛባት በቆጠራው ከተገኘው የተለየ ዉጤት እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።
5)ከእምነትና ግንዛቤ ማጣት የሚፈጠር የዉጤት መዛባት፦ ሕዝቡ የቆጣሪውን አካል ማንነትና አሰራር ላይ እምነት ከማጣት አልያም ስለቆጠራው በቂ ግንዛቤ ካለመያዝ የተነሳ ተገቢው መልኩ ባለመቆጠር የዉጤት መዛባት ሊፈጠር ይችላል።
6) ቴክኖኖጂያዊ ጉዳዮች፦ ለቆጠራው በተግባር ላይ የሚውለው ቴክኖሎጂ ለጥቃትና ለማጭበርበር የተጋለጠ በመሆኑ የተነሳ በቆጠራው ላይ ልዩ ፍላጎት ያላቸው አካላት በቴክኖሎጂው ላይ ያለውን ከፍተት በመጠቀም የቆጠራውን ዉጤትን ሊያዛቡ ይችላሉ።
7) የቋንቋ እና የባህል ክፍተት የሚፈጥረው የዉጤት መዛባት፦ ለቆጠራ የሚሰማሩ አካላት የሚቆጥሩትን ሕብዝ ቋንቋ እና ባህል አለማወቃው በቆጠራቸው ትክክለኛ መረጃ መሰብሰብ እንዳይችሉ በማድረግ አጠቃላይ ቆጠራው ትክክለኛ ዉጤት እንዳይኖረው ሊያደርግ ይችላል።
8) የሪሶርስ ወይም የበጀት እጥረት የሚፈጥረው የዉጤት መዛባት፦ ለየሕዝብና ቤት ቆጠራ ባለስልጣን ወይም ለተወሰኑ አከባቢዎች ቆጠራ ከአከባቢው የቆዳ ስፋት፥የሕዝብ አሰፋፈር፥ የአየር ሁኔታ፥ መልከዓ ምድርና የቆጠራ ጊዜ ጋር የማይመጣጠን ወይም በቂ በጀት፥ሀብትና የሰው ኋይል አለመመደብ በቆጠራው ዉጤት ላይ ተጽዕኖ ያሳርፋል።
9) የቆጠራው ወቅትና መርሃግብር ችግር፦- የሕዝብና ቤት ቆጠራ ጊዜ ህብረተሰቡ ጠቃሚ ወይም ወሳኝ አድርጎ ከሚያያቸው ሌሎች ሁነቶች፥በዓላት፥የጾም ጊዜ፥ የምርት አጨዳ፥ ወይም ሌላ መሰል ጊዜ ጋር በተመሳሳይ ወቅት በሚሆንበት ሁኔታ ሁሉም የህብተሰብ ክፍል ለቆጠራው ቅድሚያ ባለመስጠት በሚፈጠር ክፍተት የተነሳ ትክክለኛ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ሊደረግ ይችላል።
10) የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት፦ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች የሕዝብና ቤት ቆጠራ ዉጤትን ለእነርሱ ፍላጎት አላማ ማሳኪያ እንዲሆን በመሻት የቆጠራው ዉጤት እንዲዛባ ሊያደርጉ ይችላሉ።
ይህም በቆጠራው ዉጤት ከፍ ብሎ ወይም አንሶ እንዲታይ የሚፈልጉትን የህብረተሰብ ክፍል ዉጤትን ሊያሳድጉ ወይም ሊያሳንሱ የሚችሉ የቆጠራ ስልቶችን በመጠቀም፥ከበቂ በላይ ወይም በታች ቆጣሪዎችን በመመደብና መሰል ተግባራትን በመፈጸም አልያም ከቆጠራው መጠናቀቅ በኋላ ዉጤቱን በሚፈልጉት መልኩ በመቀየር ዉጤቱን ሊያዛቡ ይችላሉ።
እና ምን ይደረግ?
✅✅✅✅✅
1) ትክክለኛ የሕዝብና ቤት ቆጠራ እንዲደረግ መንግስት ለሃይማኖት ተቋማት፥ ለጎሳ መሪዎች፥ተሰሚነት ላለቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ልዩ ትኩረት በመስጠት በጀት በመመደብ የሕብረሰቡ ንቃተ ሕሊና እንዲያድግ መሥራት ይገባዋል።
2) ለአርብቶ አደር አከባቢዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት፥በቂ የሰው ኋይልና በጀት በመመደብ ትክክለኛ ቆጠራ ሊደረግ ይገባል።
3) ሰፊ የቆዳ ስፋት ላላቸው ክልሎች፥ዞኖችና ወረዳዎች ከስፋታቸው ጋር የሚመጣጠን የሰው ኋይልና በጀት ሊመደብ ይገባል።
4) በሕዝብና ቤት ቆጠራ ላይ ሁሉም ከሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ቆጣሪዎች እንዲሳፉ የማድረግ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ ለየአከባቢዎቹ የአከባቢውን ቋንቋ፥ባህልና ስነ-ልቦና የሚያውቁ ቆጣሪዎች ሊመደቡ ይገባል።
5) ቆጠራው የሚቆጠረው አከባቢ ሕዝብ ትክክለኛ መረጃ ስለመመዝገቡ ማጣራት እንዲችል የቆጠራው መረጃ መመዝገብ ያለበት ተቆጣሪው ሕዝብ በሚናገረው ቋንቋ ሊሆን ይገባል።
6) ከቆጠራው እቅድ፥ዝግጅትና ሂደት ጭምር በፌደራል፥በክልል፥ዞንና ወረዳ፥ከተማ በሕዝብና ቤት ቆጠራ መሥሪያ ቤት ከተለያየ ኋይማኖት ተከታዮች ወኪሎች እንዲሳተፉ ማድረግ።
7) የህዝብና ቤት ቆጠራ ዉጤት ከቆጠራ በፊት የህብረተሰቡን ንቃተ ሕሊናን ማሳደግ በሚችል መልኩ ስለቆጠራው አስፈላጊነት በሁሉም መልኩ ተገቢ ትምህርት መስጠት ይገባል።
8) ከቆጠራው ጊዜ ቆጣሪዎች ትክክለኛ መረጃ መቀበል ስለመቻላቸው ማረጋገጥ የሚቻልበት፥ ቅሬታም የሚቀርቡበት ስርዓት ማዘጋጀትና መረጃዎቹ ዳግም በቅሬታና ለአጥኚዎች ክፍት ሊሆን የሚችልበትን ስርዓት መዘርጋት።
🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒
እስከዛሬ ለማሰናከል በመንገዳችን ላይ የተለያዩ አጀንዳዎችን እየወረወሩ ከመስመር ለማውጣት ብዙ ደክመዋል።ዛሬም አጀንዳዎችችንና ምድባችን አንለቅም።ጉዞው ይቀጥላል።
ለማንኛውም የኔን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያላደረጋችሁ ፈጥናችሁ አድርጉ። ሊንኩ ከታች በአስተያየት መስጫው ላይ ተቀምጧል።👇
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢