Who is me my friends?

Who is me  my friends? Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Who is me my friends?, Dilla.

13/04/2025

እየሱስ ጌታ ነዉ።

😄ንጉሡ በከተማው የሚገኝ ከሁሉ የሚበልጠውን ሊቅ እንዲያመጡለት ባለሟሎቹን አዘዘ። ባለሟሎቹን በጥበቡ፣በበማስተዋሉም እጅግ የላቀ የሚሉትን ጠቢብ አመጡለት።ንጉሡም ወደ ጠቢቡ እየተመለከተ "ሶስ...
30/09/2023

😄ንጉሡ በከተማው የሚገኝ ከሁሉ የሚበልጠውን ሊቅ እንዲያመጡለት ባለሟሎቹን አዘዘ። ባለሟሎቹን በጥበቡ፣በበማስተዋሉም እጅግ የላቀ የሚሉትን ጠቢብ አመጡለት።ንጉሡም ወደ ጠቢቡ እየተመለከተ "ሶስት ጥያቄዎች እጠይቅሃለሁ የመጀመሪያው ጥያቄዬ እግዚአብሔር የት ነው የሚኖረው?"

⭐ጠቢቡም እጅ ነስቶ ይህን ጥያቄ ለመመለስ ትኩስ ወተት እና ስኳር ያስፈልገኛል አለ።ንጉሡም እንዲመጣለት አደረገ። ጠቢቡም ስኳሩን ወተት ውስጥ ጨምሮ አማስሎ ለንጉስ ሰጠው እንዲቀምሰው
"ግርማዊነቶ ወተቱ እንዴት ያለ ጣዕም አለው?" አለው
ንጉሱም"ይጣፍጣል"አለው
ጠቢቡም መልሶ"ከወተቱ ውስጥስኳሩን ማየትይቻላል? "ብሎ ጠየቀው
ንጉሱም"አይቻልም ስኳሩ ሟምቷል።"አለው
ጠቢቡም "ልክ እንደሟሟው ስኳር እግዚአብሔር ሁሉም የአለም ስፍራ ላይ አለ አናየውም እንጂ"አለው

⭐ንጉሡ በመልሱ ረክቶ ሁለተኛው ጥያቄ ጠየቀው"ፈጣሪን እንዴት ልናገኘው እንችላለን?"

🟡**ጠቢብም ግርማዊነቶ ይህንን ለመመለስ የወተት ክሬም ያስፈልገኛል አለ። ንጉሡም እንዲያመጡለት አዘዘ።
ጠቢቡም እጅ ነስቶ"ግርማዊነቶ በክሬሙ ላይ በቅቤ ይታያል?"ብሎ ጠየቀው**
ንጉሡም"ክሬሙን ብንናነሳው ቅቤ ከስር እናገኛለን ከላይ ግን አይታይም "አለው
ጠቢቡም"የሁለተኛ ጥያቄዎም መልስ እንዲህ ነው ፈጣሪም በእውነተኛ ማንነታችንን ወደ ልባችንን ስንመለስ እናገኘዋለን"አለው።

🟡ንጉሡም በጠቢቡ ተደንቆ ወደ መጨረሻው ጥያቄ አለፈ"እግዚአብሔር ምን ማድረግ ይቻለዋል? "አለው

ጠቢቡም ከንጉሡ ሎሌዎች አንዱ እንዲቀርብለት ጠየቀ። ንጉሡም አስጠራለት። ጠቢቡም"ይህ ጠባቂዎ ንጉሠ ነገሥት ነው እንበል እናም ግርማዊነቶ ለንጉሥ ዙፋን ይገባዋል እና እርሶ ከእኔ ለጎን ይቆማሉ ጠባቂዎ ደሞ በዙፋኖ ይቀመጣል "አለ
ንጉሱም በመስማማት ዙፋኑን ለሎሌው ለቀቀ።
ጠቢቡ ወደ ንጉሡ እያየ" ፈጣሪ ሎሌን ጌታ፤ጌታን ሎሌ ማረግ ይችላል"አለው።
***

04/08/2023

ቆሻሻ አውጡ እያሉ ሲጨው
ማዘር ወደኔ ትዞርና

#እራስህን ችለ ውጣ☹️😂

03/08/2023

አስተማሪ፡ አንበሳ ቢያባርርህ ምን ታደርጋለህ?

ተማሪ፡ ዛፍ ላይ ወጥቼ አመልጠዋለሁ።

አስተማሪ፡ ተክትሎ ቢወጣስ?

ተማሪ፡ ከዛፍ ላይ ዘልዬ ወደወንዝ ውስጥ በመግባት ዋኝቼ አመልጠዋለሁ።

አስተማሪ፡ አንበሳው ወንዙ ውስጥ ቢገባና እሱም እየዋኘ ቢከተልህስ?

ተማሪ፡ እን የምሎት ቲቸር... ይሄ አንበሳ እንዲበላኝ የፈለጉት ለምንድነው? 💀

አስተማሪዎች ጥያቄዎችን ጠይቀው የማይጨርሱት ነገርስ... 😂😭

06/08/2022
17/11/2021

በሲዳማ ክልል በተሽከርካሪዎች ላይ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ
******************

የሲዳማ ክልል ኮማንድ ፖስት ከነገ ጀምሮ ገደብ የተጣለባቸውን የሰአት እላፊ፣ የእንቅስቃሴዎች ገደብ እና ክልከላዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም ህጋዊ ሞተር ሳይክሎች ከጥዋቱ 12 ሰአት ጀምሮ አስከ አመሻሹ 1 ሰዓት፣ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ከጥዋቱ 12 ጀምሮ እስከ 2 ሰአት እንዲሁም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በተመሳሳይ እስከ ምሽት 2 ሰዓት ክፍት መሆናቸው ተገልጿል።

ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል (ታርጋ ያለው ብቻ) አንድ ሰው ጭኖ ከጠዋት 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት፣ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ ከጎንና ጎን ያለበሱትን ሸራ በማንሳትና ሶስት ሰው ብቻ በመጫን እስከ ምሽት ሁለት ሰዓት፣ የህዝብ ትራንስፖርትና ታክሲዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 2 ሰዓት ብቻ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ ተገልጿል።

በክልሉ የኮማንድ ፖስቱ ምክትል ሰብሳቢና የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ መመሪያውን የሚተላለፉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በጭነት አገልግሎት በሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ላይ ገደብ አለመጣሉንና ነግር ግን ጥብቅ ፍተሻ በፀጥታ አካላት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

ከአጎራባች ክልሎችና ዞኖች ወደ ሲዳማ ክልል ከአመሻሽ ከ12 ጀምሮ ምንም አይነት ሞተር ሳይክል እንዲገባ አይፈቀድም ያሉት አቶ አለማየሁ በመተላለፊያ አካባቢዎች በፀጥታ አካላት ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ብለዋል።

በተጨማሪም የጦር መሳሪያ በእጃቸው የሚገኝ የክልሉ ነዋሪዎች እንዲያስመዘግቡም ተጠይቋል።

አቶ አለማየሁ አያያዘውም በሲዳማ ክልል በሚገኙ በሁሉም ቀበሌዎች የነዋሪነት መታወቂያ እንዳይሰጥ መመሪያ የወረደ መሆኑን አስታውሰው ይሄን ደንብ ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም አካል ቅጣት ይጠብቀዋል ብለዋል።

እስካሁን ባለው 83 የሚሆኑ የጁንታው ተላላኪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያነሱት አቶ አለማየሁ በምርመራ ነፃ የሆኑ ተጠርጣሪዎች እንደሚለቀቁ አረጋግጠዋል።

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
የመዝናኛ ቻናላችን የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት የዩቲዩብ የመዝናኛ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCp9pS23Vw1n8WpcpZBDJNmA
በምስል የሚገኙ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የኢንስታግራም ገፃችንን ይከተሉ
https://www.instagram.com/ebcnews1/
አጫጭርና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
https://twitter.com/ebczena
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW

06/10/2021

ነገ ለላ ቀን ነዉ ።

Address

Dilla

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Who is me my friends? posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share