Shema Store

Shema Store Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Shema Store, Business service, Durame Durame, Durame.

-የጥምቀት ትሸሪቶችን በአሜሪካ USA-ለወንዶችም ለሴቶችም የሚሆኑ ( unisex ) -በፈለጉት ሳይዝ ይዘዙ፤ በፍጥነት ይደርሶታል።http://shemaa.printify.me #ጥምቀት #ትሸርት ...
06/01/2024

-የጥምቀት ትሸሪቶችን በአሜሪካ USA
-ለወንዶችም ለሴቶችም የሚሆኑ ( unisex )
-በፈለጉት ሳይዝ ይዘዙ፤ በፍጥነት ይደርሶታል።

http://shemaa.printify.me

#ጥምቀት
#ትሸርት



05/01/2024

We offer a variety of traditionally designed clothes in USA, Europe and Canada.

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለፈው ማክሰኞ ባወጣው ሪፖርት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (   ) ዙሪያ ድርድርን እንደገና ለማስጀመር ባለፉት ሶስት ቀናት ውስጥ በዲ. ኮንጎ የተካሄደው የ...
06/04/2021

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለፈው ማክሰኞ ባወጣው ሪፖርት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ( ) ዙሪያ ድርድርን እንደገና ለማስጀመር ባለፉት ሶስት ቀናት ውስጥ በዲ. ኮንጎ የተካሄደው የመጨረሻው ዙር ድርድር ምንም ዓይነት እድገት እንዳላመጣና ከስምምነት መድረስ አለመቻሉን አስታውቋል ፡፡
በአፍሪካ ህብረት የተደገፈው የሶስትዮሽ ድርድር በግብፅ ፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል እሁድ እና ሰኞ በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የዴሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት አደራዳሪነት በኪንሻሳ ተካሂዶ የነበረው ውይይት ሰኞ ከተጠናቀቀም በኋላ ለአንድ ቀን ተራዝሞ ድርድር ሲደረግ ቆይቷል ፡፡ ነገር ግን በተከታታይ ልዩነቶች ምክንያት ድርድር ያለተጨማሪ ስምምነት መጠናቀቁን አህራም ዘግቧል ፡፡

  ማነው?ትክክለኛ ስሙ ሙሳ ሳንዲያና ካባ ነው። ብዙዎች ግራንድ ፕ በሚለው የመድረክ ስሙ ያውቁታል። ግራንድ ጊንያዊ ሙዚቀኛ፣ ተዋናይ እና ፖለቲከኛ ነው። ግራንድ ፕ ናባያ፣ ሳንጉያና ውስጥ ...
18/10/2020

ማነው?

ትክክለኛ ስሙ ሙሳ ሳንዲያና ካባ ነው። ብዙዎች ግራንድ ፕ በሚለው የመድረክ ስሙ ያውቁታል። ግራንድ ጊንያዊ ሙዚቀኛ፣ ተዋናይ እና ፖለቲከኛ ነው። ግራንድ ፕ ናባያ፣ ሳንጉያና ውስጥ እ.ኤ.አ 1990 ላይ የተወለደ ሲሆን ከልጅነቱ ጀምሮ ፕሮጄሪያ በተባለ አልፎ አልፎ በሚከሰት ጄኔቲክ በሽታ የተጠቃ በመሆኑ በበሽታው ምክንያት ለየት ያለ አካላዊ ገፅታ አለው። በሽታው የሰዎችን ቁመት ቢበዛ 1 ሜትር ከ10 እንዲሁም ክብደታቸውን 25 ኪሎ ይገድባል። በዚህ በሽታ የተያዙ ሰዎች በአማካይ 13 አመት የሚኖሩ ቢሆንም ግራድ ፕ አሁን 30 አመቱ ነው።

ግራንድ ፕ ፖርቲውን ኤሲዩን በመወከል በሀገሩ በሚካሄደው ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ላይ እጩ ሆኖ የቀረበ ሲሆን "ለ2020 ፕሬዝዳንትነት እወዳደራለሁ እኔን አድምጡኝ፥ በጉልበት እመጣለሁ። እኔን መደገፍ አለባችሁ።" ይላል። ፕ ከፖለቲካ ተሳትፎው ባሻገር የፊልም አክተር ነው። በ2020 ከአሜሪካ የፊልም ፕሮዳክሽን ጋር ሁለት ፊልሞች ላይ ለመተወን ኮንትራት ተፈራርሟል። ነገር ግን ፕ የሀብት መጠኑ በግልፅ አይታወቅም።

ታዲያ ሰሞኑን ግራንድ ፕን የበለጠ ታዋቂ እንዲሆን ያደረገው ከአይቮሪኮስታዊቷ ሞዴል ኢዶክሲ ያኦ ጋር የፍቅር ግንኙነት እንዳላቸው ይፋ በማድረጉ ነው።ፎቶዎቻቸው በማህበራዊ ሚዲያዎች በብዛት ተሰራጭተዋል፥ ብዙዎችም ሞዴሏ ኢዶክሲ ያኦ ግዙፍ ተክለ ሰውነት ያላት መሆኑ ነገሩ ቢገርማቸው መነጋገሪያ አድርገውታል። አንዳንዶች ደግሞ ዝናውንና ሀብቱን አይታ ነው የፍቅር ግንኙነት ውስጥ የገባችው ቢሏትም እሷ ግን ግንኙነታችን በፍቅር ላይ የተመሠረተ ነው በማለት አስተባብላለች።

😳😳😳

 #እናትበቃላት የማይገለፁ፤ ለተናጋሪው ብቻ በአይነ ህሊናው ቁልጭ ብለው የሚታዩ ብዙ ነገሮች  አሉን። አንዱ👇
18/10/2020

#እናት
በቃላት የማይገለፁ፤ ለተናጋሪው ብቻ በአይነ ህሊናው ቁልጭ ብለው የሚታዩ ብዙ ነገሮች አሉን። አንዱ👇

 #ጀግኒትኢትዮጵያዊቷ የ22 ዓመቷ ለተሰንበት ግደይ ዛሬ በስፔን ቫሌንሺያ በነበረው ውድድር ላይ 14 ደቂቃ ከ06 ሰከንድ ከ62 ማይክሮሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ሪከርድ በመስበር ጭምር አ...
08/10/2020

#ጀግኒት

ኢትዮጵያዊቷ የ22 ዓመቷ ለተሰንበት ግደይ ዛሬ በስፔን ቫሌንሺያ በነበረው ውድድር ላይ 14 ደቂቃ ከ06 ሰከንድ ከ62 ማይክሮሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ሪከርድ በመስበር ጭምር አሸንፋለች።
ላለፉት 12 ዓመታት የዚህ ክብረወሰን ባለቤት የነበረችው ጥሩነሽ ዲባባ ነበረች።

እንቁጣጣሽዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ...
10/09/2020

እንቁጣጣሽ

ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡

ሁለተኛው የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡ ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ላይ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ ቤተ መንግሥቱንም፣ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኛት፡፡ ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡

አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ» ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡

መልካም አዲስ ዓመት

ውድ ቤተሰቦቻችን  በሰላም አደረሰን። ብዙ የከበቡንን ችግሮች በፈጣሪ እርዳታ ተቋቁመን እነሆ ወደ አዲሱ ዓመት ልንሸጋገር ጥቂት ሰዓታት ይቀሩናል። በአዲሱ ዓመት ካለንበት ሸሽተን ከቀያችን ሆ...
10/09/2020

ውድ ቤተሰቦቻችን በሰላም አደረሰን። ብዙ የከበቡንን ችግሮች በፈጣሪ እርዳታ ተቋቁመን እነሆ ወደ አዲሱ ዓመት ልንሸጋገር ጥቂት ሰዓታት ይቀሩናል። በአዲሱ ዓመት ካለንበት ሸሽተን ከቀያችን ሆነን እስክያልፍ በስጋትና ጉጉት እንድንጠብቅ ከቤታችን አጮልቀን እንድናይ ያስገደደን ኮሮና ቫይረስ አክትሞ ሀገርና ዜጎቿ ከስጋት ነፃ ሆነው እንዲሰነብቱ ዛሬን በጥንቃቄ እናሳልፍ። ዘረኝነት ከስሞ፤ ፈርሃ እግዚአብሔር ከሰው ልብ ነግሶ ፤ከብሄር ብሄረሰቦች ጎጆዋ ወደ ላይ የሚጨሰው የፍቅር ጥስ ከሀገሬ ሰማይ ከፍ የሚልበት አመት ይሁንልን!

Our dear family new . We have been established by God's help, here are a few hours left to move to the new year. Let's be careful today to see our house and virus that killed us to see our house and virus that killed us from our house and its citizens are free from threat. Racism from the name of racism, fear God from the heart of people, may it be a year that is going to be high from my country!

Address

Durame Durame
Durame

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shema Store posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share