Jólléë Háràr

Jólléë Háràr Jechota fi barrefamota kiyyarra akka barnota gudda irra baracha jirtan abb

26/04/2023
26/04/2023
26/04/2023
26/04/2023
28/11/2022

በሀረሪ ክልል የሙስና ወንጀልን ለመከላከልና ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ የሚያስችል ኮሚቴ ተቋቋመ።

በሀረሪ ክልል የሙስና ወንጀልን ለመከላከል እና የወንጀሉን ተዋንያን ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል ክልላዊ ኮሚቴ ተቋቁሟል።

ይህም በተለያዩ መዋቅሮች በተደራጀ መልኩ የሚፈፀም የመሬት ነክ ሙስና፣ ከግብር፣ ከግዥ፣ ለፕሮጀክቶች፣ ከግንባታ ፍቃድ፣ ከመንጃ ፍቃድ ህገ ወጥ ንግድ፣ ከኢንቨስትመንት፣ለመንግስታዊ አገልግሎቶች ከዜጎች የሚጠየቅ ጉቦ፣ በፍትህ ዘርፍ እና በሌሎችም ዘርፎች የሚፈፀም ሙስናን በመከላከል ወንጀለኞች ለህግ ቀርበው ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚያግዝ ነው።

የተቋቋመውና አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴው በሙስና ወንጀል ላይ የሚያደርገውን የህግ ማስከበር ዘመቻ የሚያስተባብር፣ የወንጀሉን ተዋንያን የሚለይና ለሕግ እንዲቀርቡ የሚያደርግ ነው።

የኮሚቴው አባላትም፦

1ኛ.አቶ አዩብ አህመድ__የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ ኃላፊ
2ኛ.አቶ ካሊድ ኑሬ__ የሀረሪ ክልል የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር
3ኛ.አቶ ጥላሁን ዋደራ____ የሀረሪ ክልል ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
4ኛ.አቶ ከተማ ለማ___ የመልካም አስተዳድር እና ሪፎርም አማካሪ
5ኛ.አቶ ሐምዲ ሰልሃዲን_ የዲሞክራሲ ተቋማት ግንባታ አማካሪ ናቸው።

ይህ የፀረ ሙስና ክልላዊ ኮሚቴ የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣትና ትርጉም ያለው ውጤት ማምጣት እንዲችል የህብረተሰቡ ሙሉ ትብብር እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ የሙስና ተዋንያንን በተመለከተ ያለውን መረጃ፣ ከቂምና ከበቀል ነጻ በሆነ መንገድ በቀጣይ ቀናት በክልላዊ ኮሚቴ ለህዝብ ይፋ በሚያደርጋቸው አድራሻዎች በመላክ ሙስናን ለማጥፋት በሚደረገው ትግል ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ክልላዊ ኮሚቴው የሚወስዳቸው እርምጃዎች እና የእንቅስቃሴው ውጤት በየጊዜው ለህዝብ ይፋ የሚደረግ ይሆናል።

15/11/2022

Address

Jenna
Hirna
ISLAMICZON

Telephone

+251915024918

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jólléë Háràr posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Jólléë Háràr:

Share