Gata mobile solution ግአታ ሞብይል ጥገና

Gata mobile solution ግአታ ሞብይል ጥገና ሞብይል ጥግና
ግአታ best way

ኮምፒውተርዎን ፈጣን የሚያደርጉ 10 ዘዴዎች1. ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፎቶዎች ዎልፔፐር አይጠቀሙ፡፡2. ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ ለመነካካት አይሞክሩ፡፡3....
07/01/2023

ኮምፒውተርዎን ፈጣን የሚያደርጉ 10 ዘዴዎች

1. ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፎቶዎች ዎልፔፐር አይጠቀሙ፡፡
2. ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ ለመነካካት አይሞክሩ፡፡
3. አፕሊኬሽን ከዘጉ በሁዋላ ዴስክቶፑን ሪፍሬሽ ያድርጉ፤ ይህም ራም ሜሞሪን ነፃ ያደርጋል፡፡
4. የማይጠቀሙበት ሶፍትዌር ካለ ከኮምፒውተሩ ይሰርዙ (አን-ኢንስታል) ያድርጉት)፡፡
5. ዴስክቶፕ ላይ ፋይል አያስቀምጡ፤ ሾርትከትም መብዛት የለበትም፡፡
6. ኮምፒዩተሩ ሲከፈት በራሳቸው የሚከፈቱ ለምሳሌ: ስካይፕ አይነት አፕሊኬሽኖች ካሉ disable ያድርጉ
7. Recycle binን ሁሌም ባዶ ያድርጉ::
8. ሀርድ ዲስኩን ሁለት ፓርቲሽን ይፍጠሩለት፡፡
9. ብዙ ሶፍትዌሮችን ባንዴ አይክፈቱ::
10. ኮምፒውተርዎን update ያድርጉ!

በነገራችን ላይ በነፃ የኦንላይን ትምህርት የሚሰጡ አራት ዌብሳይቶችን እና እንዴት መመዝገብ እንደምትችሉ የሚያሳይ ቪድዮ ዩቲዩብ ቻነሌ ላይ አለ።አሁን ወቅቱ የምዝገባ ወቅት ስለሆነ አያምልጣችሁ።

ፍላሽ ዲስካችን ውስጥ የተደበቀን መረጃ(Hidden File) እንዴት አድርገን ማግኘት እንችላለን?Steps: -1. ፍላሽ ዲስካችሁን ከኮምፒውተራችሁ ላይ ይሰኩ2. የፍላሽ ዲስኩን letter እ...
05/01/2023

ፍላሽ ዲስካችን ውስጥ የተደበቀን መረጃ(Hidden File) እንዴት አድርገን ማግኘት እንችላለን?
Steps: -
1. ፍላሽ ዲስካችሁን ከኮምፒውተራችሁ ላይ ይሰኩ
2. የፍላሽ ዲስኩን letter እዩ ለምሳሌ . E ሊሆን ይችላል
3. ኮማንድ ፕሮምፑትን(CMD) ይክፈቱ
5. CMD/ Command prompt / ከከፈተልን በኋላ
ለምሳሌ የፍላሽ Letter E ከሆነ E: ብላችሁ ጽፋችሁ ኢንተርን ይጫኑ። ከዛም ወደ ፍላሽ ዲስኩ (E) ይገባል ማለት ነው።
6. ከዛም ይህንን ይጻፉ attrib -s -h /s /d *.*
ከዛ Enter ይጫኑ። በእያንዳንዱ ፊደል Space(ክፍተት) አለ ለምሳሌ attrib ክፍተት -s ክፍተት -h ክፍተት /s ክፍተት /s ክፍተት *.* በቃ ፍላሻችሁ ውስጥ የተደበቁ ፋይሎችን ማግኘት ትችላላ

የቴሌግራም ቻነሌንም ይቀላቀሉ 👇

https://t.me/dotcomtvshow

በ   ወይም በ   የተዘጉ ሞባይል ስልኮች ካለ ምንም ኢንተርኔት እና ምንም መረጃ ሳናጠፋ እንዴት መመለስ እንደምንችል እንይ!በቅድሚያ የሚያስፈልጉ ነገሮች👇1ኛ፦ Aroma file manager...
05/01/2023

በ ወይም በ የተዘጉ ሞባይል ስልኮች ካለ ምንም ኢንተርኔት እና ምንም መረጃ ሳናጠፋ እንዴት መመለስ እንደምንችል እንይ!

በቅድሚያ የሚያስፈልጉ ነገሮች👇

1ኛ፦ Aroma file manager የሚባል አፕሊኬሽን በሌላ ስልክ ላይ ዳውንሎድ ማድረግ
በዚህ ሊንክ ዳውንሎድ አድርጉ፦
https://www.allmobitools.com/download-aroma-file-manager-zip/

2ኛ፦ ያወረድነውን app
የምንናስቀምጥበት ሚሞሪ ካርድ ያስፈልገናል

3ኛ፦ የተዘጋው ስልክ ያስፈልጋል

Step1⃣ aroma file manager አፕሊኬሽ ካወረዳችሁ በኃላ ወደ ሚሞሪ ካርዱ ጫኑት። እና ካርዱ ወደ ተዘጋው ስልክ አስገቡት

Step2⃣ ከዛ ስልኩ እናረገው እና የ recovery stock ወይም ስልካችን ካጠፋነው ቡኃላ የ power እና የ ድምፅ መጨመርያ ኣንድ ላይ ተጭነን እንቆያለን( እንደ ስልኩ አይነት ሊለያይ ይችላል)

Step3⃣ ወደ recovery mode ከገባን ቡኃላ የ ድምፅ መጫኞቹ ወደ ላይ እና ታች የ power መጫኛው ደሞ እንደ ok ሆነው እንጠቀማቸው

Step4⃣ recovery mode ላይ install zip from sd card የሚለውን ላይ ok/power button እንጫን እና aroma file manager ያስቀመጥንበት folder ገብተን እንለዋለን

Step5⃣ ከዛ aroma file manager ከከፈታቹ ቡሃላ ወደ የሚለውን ትወርዱ እና automount all devices on start የሚለውን ተጭናችሁ ከዛ ዝጉት

Step6⃣ step4 ላይ እንዳደረጋችሁት step6 ላይም ድገሙት

Step7⃣ aroma file manager እንደገና ሲከፈት ወደ data folder ፤ከዛ system folder ትገቡ አና 'gesture.key' or 'password.key' የሚል ታገኛላችሁ

Step8⃣ ከዛ ያገኛችሁት gesture.key or password.key ኣጥፉትና ስልካችሁን reboot ኣድርጉት

Step❾ በቃ አሁን ስልኩ ይከፈታል ።ስልኩ ሲከፈት የማትረሱትን pattern ወይም password በማስገባት መጠቀም ትችላላችሁ ።



💐የዩቲዩብ ቻነሌን እግረመንገዳችሁን ሰብስክራይብ አድርጉ 👇

https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ

💐የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ 👇

https://t.me/dotcomtvshow

Download AROMA File Manager 2.00 ZIP (2023) | (Pattern Unlock) Managing Files In Recovery Mode. Download Aroma File Manager now.

ይሄን ህመም በአማርኛ ምን እንበለው?========================አቢኒ 13 አመቱ ነው። አዳሪ ትምህርት ቤት ነው የሚማረው። ጥሩ ተማሪ ከመሆኑ ባሻገር ከአስተማሪዎችም ከተማሪዎችም ...
04/01/2023

ይሄን ህመም በአማርኛ ምን እንበለው?
========================
አቢኒ 13 አመቱ ነው። አዳሪ ትምህርት ቤት ነው የሚማረው። ጥሩ ተማሪ ከመሆኑ ባሻገር ከአስተማሪዎችም ከተማሪዎችም ጋር ይግባባል። አንድ ቀን ክፍል ውስጥ ጓደኞቹ ለቀልድ ብለው እስክሪብቶውን ደበቁበት። አቢኒ "አምጡ!!" እያለ መጮህ ጀመረ። ጓደኞቹ እንዳመረረ ገብቷቸው ቢመልሱለትም። እሱ ግን በጣም እየጮሀ ዴስኩን ገለበጠው። ለተወሰነ ደቂቃ ሌላ ሰው ሆነ።

በሌላ ጊዜ ደግሞ የትምህርት ቤቱ አትክልተኛ "በዛ በኩል መሻገር አይቻልም!" ሲለው በጣም ተናዶ ሰደበው። ይባስ ብሎ አበቦችን መነቃቀል ጀመረ። አትክልተኛው ከሰሰውና አቢኒ ዳይሬክተሩ ጋር ቀረበ። ዳይሬክተሩ ጋር ሲቀርብ ከንዴቱ ተረጋግቶ ባደረገውም ነገር ተፀፅቶ ነበር። ዳይሬክተሩ በአጠቃላይ ተግባቢና ጥሩ ፀባይ ያለው እንደሆነ ስለሚያውቅ ከመቅጣቱ በፊት የአእምሮ ሀኪም እንዲያየው ይዞት መጣ። ከምርመራው በኋላ አቢኒ Intermittent Explosive Disorder እንዳለበት ሲነገረው "በአማርኛ ምንድነው የሚባለው?" ብሎ ጠየቀ። መስፈርቱን አስቀምጥና ስያሜውን አብረን እንፈልጋለን።

አንድ ሰው Intermittent Explosive Disorder አለበት የምንለው የሚከተሉትን መስፈርቶች ሲያሟላ ነው።
ሀ. እድሜው ከ6 አመት በላይ ሰው በተደጋጋሚ ንዴቱን ባለመቆጣጠር ሰው ላይ መጮህ፣ እቃ መወርወር፣ እንስሳትን ወይም ሰዎችን መማታት፣ እቃ መስበር ወይም ንብረት ማውደም።
ለ. የሚያሳየው የሀይለኝነት ፀባይ ካናደደው ነገር ጋር አለመመጣጠን።
በትንሽ ነገር በጣም ከፍተኛ ንዴትና ሀይለኝነት ውስጥ መግባት።
ሐ. ሀይለኝነቱ የታቀደበት አይደለም። ወይም ለማስፈራራት፣ ለስልጣን ወይም ጥቅም ለማግኘት ተብሎ የሚደረግ አይደለም።
መ. ሀይለኝነቱ በመደጋገሙ ምክኒያት በግለሰቡ ላይ ጭንቀት ወይም በማህበራዊ ግንኙነቱ ላይ ተፅእኖ አሳድሯል።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

03/01/2023

❤️👏👏👏👏👏

Address

Holeta
Holeta

Telephone

+251934262290

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gata mobile solution ግአታ ሞብይል ጥገና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share