19/02/2023
" ትመሰገኑ ዘንድ ይገባችኃል "
የካቲት 11/2015 ዓ.ም በሳፉየር አዲስ ሆቴል ባዘጋጀነው "የሪል እስቴት እና የባለድርሻ አካላት የግንኙነት መድረክ " ኩነት በነገር ሁሉ የረዳን አምላክ ይመስገን እያልኩኝ ከሀሳቡ ፅንሰት ጀመሮ ፕሮግራማችን በተሳካ ሁኔታ እስኬጠናቀቅ ድረስ በሀሳባቹ እና በዕውቀታቹ ፣ በጉልበታቹ እንዲሁም በገንዘባቹ ከፍተኛ ጥረት ያደረጋችሁት ውድ የስራ ባልደረቦቼ የውቅር ትሬዲንግ ቤተሰቦች እናንተ በእርግጥም ምስጋናና እና ክብር ይገባችኋል🙏
በውቅር ትሬዲንግ አዘጋጅነት በነበረው ኩነት ላይ ዕውቀታችሁን እና ልምዳችሁን በዕለቱ ያጋራችሁን ፣ የፕሮግራማችን የሚዲያ አጋር የሆናችሁን ፣ በዕለቱ ጥሪያችንን እና ግብዣችንን አክብራቹ በፕሮግራማችን ላይ የታደማቹ እንግዶቻችን ሁላችሁንም በውቅር ትሬዲንግ የንግድ ተቋም ስም እናመሰግናለን🙏🙏🙏
እናንተ ትመሰገኑ ዘንድ ይገባችኋል 👇👇👇
1. አቶ ጌታቸው በሻውረድ የ BRUH Fiance founder & CEO ከለንደን በ Zoom Meeting እውቀቶትን እና ልምዶትን ስላከፈሉን 🙏🙏
2. ኢንጂነር ጌቱ ከበደ የጠለቀውን ዕወቅት እንሸምት ዘንድ በዕለቱ የዕውቀት ማዕድን ስላቋደሱን
3. ለእኛ መሰባሰብ ፣ ለመዋቀር እና ውቅር ትሬዲንግ የንግድ ተቋማችንን እንመሰርት ዘንድ ሰበበ ድርጊት ለሆነን ለአቡቀለምሲስ የማሰልጠኛ ተቋም መስራች እና ባለቤት ኢንጅነር ደሳለኝ ከበደ
4. ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ በኢትዮጵያ የ DSTV Manager
የዕለቱ የመድረክ አጋፉሪ በመሆን ፕሮግራማችንን ውበት እና ግርማ ሞገስ ስላላበስክልን
5. በእርሱ ፍቃድ ሪል እስቴት አቶ በእርሱ ፍቃድ
5. የሚዲያ ሽፉንን የሰጣችሁን እና አጋር የሆናችሁን
፨ ድሬ ቲዩብ
፨ አሃዱ ሬዲዮ እና Tv
፨ ኢትዮጵያን ቢዝነስ ሪቪው
፨ አዲስ ማለዳ
፨ FM 97.1 ሬዲዮ
6. የሽያጭ እና የግዢ አማካሪ ድርጅቶች እና ባለ ሞያዎች
7. የባንክ እና የኢንሹራንስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፨