Fasil Genet

Fasil Genet Business group

05/04/2020

#2 death registered 😒

Take ov ur self dears❤
01/04/2020

Take ov ur self dears❤

*ቀሽም ዜና* በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 25 ደርሷል።አዲስ በቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች የ30ና የ37 አመት ግለሰቦች ሲሆኑ ሁለቱም በተመሳሳይ በረራ ከዱባይ የገቡ መሆናቸውን...
31/03/2020

*ቀሽም ዜና*
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 25 ደርሷል።

አዲስ በቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች የ30ና የ37 አመት ግለሰቦች ሲሆኑ ሁለቱም በተመሳሳይ በረራ ከዱባይ የገቡ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አሳውቋል ።

ሶስተኛው የ60 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ መጋቢት 6 ነው ከፈረንሳይ የገቡት።

30/03/2020



በድጋሚ ጦርነት ላይ እንደሆንን ለማስገንዘብ እንወዳለን!

አሁንም ጊዜው ሳይረፍድ፣ ከፍተኛ ዋጋ ሳንከፍል በፊት እንዚህ ጉዳዮች እንዲታሰባቸው፣ መፍትሄም እንዲያደኙ አጥበቀን እንጠይቃለን፦

- በሀገሪቱ ያሉ ብዙ ሰዎች የሚገበያዩባቸው ስፍራዎች፣ በከተሞችም በገጠሩም ክፍል ያሉት እንቅስቃሴዎች መፍትሄ ይፈለግላቸው።

- ያልተዘጉ ጫት ቤቶች፣ ሺሻ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ የምሽት መዝናኛ ቤቶች በተለይም ክልል ከተሞች ላይ በአስቸኳይ መፍትሄ ይፈለግላቸው።

- የወጣቶች መሰባሰቢያዎች የእግር ኳስ መጨወቻ ሜዳዎች፣ ፑል ቤቶች፣ ከረንቡላ ቤቶች፣ የቪድዮ ጌም ማጫወቻዎች፣ ...ወዘተ መፍትሄ ይፈለግላቸው።

- በአዲስ አበባ እንዲሁም በክልል ከተሞች ላይ አሁንም ያንተስተካከለው የትራንስፖርት ሁኔታ ነገ ዋጋ ሳያስከፍለን ቢስተካከል መልካም ነው።

- ገጠር ውስጥ ያለው የሞተር ትራንስፖርት መፍትሄ ይፈልጋል። በአንድ ሞተር ስንት ሰው ተጭኖ እንደሚጓጓዝ የምናውቀው ነው።

- ህዝቡ ጤናው እንዲጠብቅ የውሃ አቅርቦት በሚቻለው መልኩ እንዲስፋፋ ቢደረግ ጥሩ ነው።

- የኢንዱስትሪ ፓርክ ሰራተኞች እጅግ በጣም ለአደጋ ተጋላጭ ናቸው ፤ መፍትሄ ይፈልጋል።

- የአየር መንገድ ሰራተኞች ይበልጥ ለዚህ ቫይረስ ተጋላጭ ናቸው፤ የጥንቃቄ እርምጃው ከፍ ካላለ በሚጪዎቹ ቀናት የሚከፈለው ዋጋ ከባድ ነው።

- በግል ድርጅቶች የሚሰሩ ሰራተኞችም ደህነነታቸው ቢጠበቅ ጥሩ ነው። ስራም፣ ትርፍም ጤና ሲኮን ነው።

- መንግስት ትዕዛዞች የማይከበሩ ከሆነ ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ ሊያደርግ ይችላል። ይህ ከፍተኛ ተፅእኖ እንዳለው ቢታወቅም ሁሉም ያጣውን፣ ጎረቤቱን ለመደገፍ እርስ በእርስ ለመተዛዘን እራሱን ማዘጋጀት አለበት።

- በኢኮኖሚው ሻልያለ ሁሉ ወገኑን የሚያይበት ትክክለኛ ወቅትም ስለሆነ ሁሉም ያለው ለመካፈል፣ ይህን ጦርነት ለማሸነፍ መዘጋጀት አለበት።

- ሁለት ያለው አንዱን ለሌላው ማካፈል የሚጠበቅበት ወቅት ስለሆነ እያንዳንዳችን በመልካምነታችን፣ በመተጋገዝ ይህን ወቅት ልናልፍ ይገባል።

- በጎዳና ላይ ለሚገኙ ዜጎች፣ በኢኮኖሚ የተዳከሙ ወገኖችን ለማገዝ በፍጥነት መንቀሳቀስ ይገባል።

- ከምንም ነገር በላይ ጦርነቱን ከፊት ሆነው ለሚመሩት የጤና ባለሞያዎቻችን በቂ የህክምና ቁሳቁስ ካልተሟላ የሚከፈለው ዋጋ ከባድ ነው። በተለይ ከከተማ ውጭ ያሉ የጤና ባለሞያዎች ሁኔታ በእጅጉን ያሳስባል።

በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 34 ሺህ ደርሷል!➡️በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 723,700➡️ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 151,991➡️በቫይረሱ ምክን...
30/03/2020

በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 34 ሺህ ደርሷል!

➡️በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 723,700

➡️ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 151,991

➡️በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች 34,005

➡️በቻይና 31 አዲስ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ተገኝተዋል

➡️በኒውዮርክ 1 ሺህ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አልፏል።

ምንጭ: አልጃዚራ

29/03/2020

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለት ተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎች ለይቶ ማቆያ ማዕካለት መከፈታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።

ሁለቱ የለይቶ ማቆያ ማዕከላት በመተከል ዞን መንደር 49 ቀበሌ እና ካማሺ ዞን ካማሺ ከተማ አቅራቢያ ባለፈው ሳምንት ውስጥ ነው የተከፈቱት።

“ማዕከላቱ የንፅህና መጠበቂያ፣ የህክምና ቁሳቁስ፣ አልጋና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ለማሟላት ጥረት እየተደረገ ነው “ብለዋል። አገልግሎት የሚሰጡ የህክምና ባለሙያዎችም ተገቢውን ስልጠና አግኝተው ተመድበዋል።

29/03/2020

ተጨማሪ መረጃ በetv ከአዳማ፦

በአዳማ ከተማ ሦስት (3) በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን ተከትሎ የከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጥ መደረጉን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

በከተማዋ ውስጥ የሚደረግ የሰዎች እንቅስቃሴም በከፊል እንዲቋረጥ መደረጉን የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ግዛቸው ገቢሳ ገልፀዋል።

በአዳማ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባጃጅ እና ታክሲዎች ስራ እንዲያቆሙ ቢደረግም ከተማውን አቋርጦ የሚያልፍ የትራንስፖርት አገልግሎት ግን እንደቀጠለ መሆኑም ተገልጿል።

Address

Mekelle

Telephone

+251960033967

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fasil Genet posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Fasil Genet:

Share