አርሂቡ ጫት ቤት

አርሂቡ ጫት ቤት መቐለ ይገኛል ፈጥነው ይዘዙን

ዒድ ሙባረክ
29/03/2025

ዒድ ሙባረክ

29/03/2025

እንኳን ለዒድ አል-ፈጥር በዓል አደረስዎ እያለ በዓሉ የራሕመት ፣ የበረካ እና የሰላም እንዲሆንልዎ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡ዒድ ሙባረክ!

23/02/2025

ሊቨርፑል ማንቼስተር ሲቲን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)ሊቨርፑል ማንቼስተር ሲቲን 2 ለ 0 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ማጠናከር ችሏል።

03/02/2025

አሜሪካን ያስጨነቀው የቻይናው ሰው ሰራሽ አስተውሎት

አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ዲፕ ሲክ” የተባለውን የቻይና የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበርያ ለአሜሪካውያን የማንቂያ ደውል ነው ብለውታል።

“ዲፕ ሲክ” በቻይና የተሰራ ሲሆን ከቻት ጂፒቲ እና መሰል ተወዳዳሪዎቹ ጋር ሲነጻጸር እጅግ ባነሰ ዋጋ በመሰራቱ የቴክኖሎጂ ገበያውን ተቆጣጥሮታል።

በዓለማችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ቀዳሚውን ስፍራ የያዘችው አሜሪካ ስትሆን የቻይናው ዲፕ ሲክ ግን እነዚህን የአሜሪካ ድርጅቶች የሚገዳደር ሆኗል።

“ዲፕ ሲክ” አገልግሎት ላይ በዋለ በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ በአሜሪካ በከፍተኛ ቁጥር የተጫነ ነፃ መተግበርያ ሆኗል። ይህን ተከትሎ በአሜሪካ አሉ የሚባሉት የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የቴክኖሎጂ ድርጅቶች የአክሲዮን ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ አሽቆልቁሏል።

ለአብነትም “ኤንቪዳ” የተሰኘው ታዋቂ ድርጅት አጠቃላይ የድርጅት አክሲዮን ዋጋው በ600 ቢሊየን ዶላር መቀነሱን ቢቢሲ ዘግቧል።

የዲፕ ሲክ ቀዳሚዎች እና ተገዳዳሪዎች የሆኑት እነ የቻት ጂፒቲው “ኦፕን ኤ አይ” እና “ኤንቪዳ” የተሰኙ ድርጅቶች መሰል ቴክኖሎጂዎችን ለማበልጸግ በቢሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ወጥቶባቸዋል።

ነገር ግን የቻይናውን ዲፕ ሲክ ለማበልጸግ ስድስት ሚሊየን ዶላር ብቻ መፍጀቱን ድርጅቱ ገልጿል። ይህም ለቴክኖሎጂ ገበያው መናጋት ዋናው ምክንያት ሆኗል።

በተጨማሪም ይህን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል ለማሰልጠን ቀዳሚዎቹ የአሜሪካ ሞዴሎች 16 ሺሕ አካባቢ ልዩ ቺፖችን የተጠቀሙ ሲሆን የቻይናው ዲፕ ሲክ ግን 2ሺህ ብቻ እንደተጠቀመ አስታውቋል።

በዚህም የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂዎችን ለማበልጸግ በጣም ውድ የሆኑ እቃዎች እና ከፍተኛ ኃይል ያስፈልጋል የሚለውን እሳቤ የሞገተ ሆኗል።

ትራምፕ ይህ ለአሜሪካ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች የማንቂያ ደውል ነው ያሉ ሲሆን ባነሰ ዋጋ መሰል መተግበርያዎችን መስራት መቻሉ ደግሞ በጥሩ ጎኑ የሚነሳ ነው ብለዋል። ነገር ግን አሜሪካ በዘርፉ ያላትን ቀዳሚነት ያሳጣታል ብለው በፍጹም እንደማይሰጉ ተናግረዋል።

የቻት ጂፒቲ አበልጻጊ ድርጅት የሆነው “ኦፕን ኤ አይ” ባለቤት ሳም አልትማን ዲፕ ሲክን ቢያደንቁም የዓለማችን ቱጃር ኤሎን መስክ ግን ድርጅቱ ምን አልባትም ልክ ላይሆን ይችላል ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከካናዳ፣ ሜክሲኮና ቻይና በሚገቡ እቃዎች ላይ ታሪፍ እንዲጣል ትዕዛዝ መስጠታቸው የአሜሪካ ሰሜናዊ ጎረቤት ካናዳ ፈጣን የአጸፋ እርምጃ እንድትወስድና የመ...
03/02/2025

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከካናዳ፣ ሜክሲኮና ቻይና በሚገቡ እቃዎች ላይ ታሪፍ እንዲጣል ትዕዛዝ መስጠታቸው የአሜሪካ ሰሜናዊ ጎረቤት ካናዳ ፈጣን የአጸፋ እርምጃ እንድትወስድና የመከዳት ስሜት እንዲሰማት አድርጓል ተብሏል።

ትራምፕ በካናዳ ላይ ታሪፍ መጣል ከአሜሪካ የረጅም ጊዜ አጋር ጋር የንግድ ጦርነት ጀምረዋል።

የረፐብሊካኑ ፕሬዝደንት ታሪፍ የተጣለው "አሜሪካውያንን ለመከላከል" እና በሶስቱ ሀገራት ህገወጥ የፌንታንይል ምርትና ንግድ እንዲቀንሱ ጫና ለማድረግ እንዲሁም ከካናዳና ሜክሲኮ የሚመጡ ህገወጥ ስደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ ያለመ ነው ሲሉ የውሳኔያቸውን ተገቢነት አስረድተዋል።

ታሪፎቹ የሚዘልቁ ከሆነ የኑሮ ውድነቱን በማባባስ መራጮች ትራምፕ ቃል መገቡት መሰረት በፍጆታ እቃዎች ላይ የዋጋ ቅናሽ ያደረጋሉ የሚለውን እምነት ሊሸረሽር እንደሚችል ተገልጿል።

ታሪፎቹ የኑሮ ውድነቱን በማባባስ መራጮች ትራምፕ ቃል መገቡት መሰረት በፍጆታ እቃዎች ላይ የዋጋ ቅናሽ ያደረጋሉ የሚለውን እምነት ሊሸረሽር እንደሚችል ተገልጿል

28/01/2025

አደገኛ መተግበሪያ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ መሆኑን ንግድ ባንክ አስታወቀ ጥር 20/2017

ከጫናችሁ ያለፈቃድ ገንዘብ ይቆረጥባችኃል!

ደምበኞች በዋትስ አፕ እና በቴልግራም የሚሠራጭ Pharma+/CBE Vacancy መተግበሪያን እንዳይጭኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሳስቧል።

ባንኩ ባስተላለፈው የማስጠንቀቂያ መልዕክት፤ ባደረገው ምርመራ መሠረት አደገኛ መተግበሪያ ማግኘቱን ገልጿል።

ይህ Pharma+/CBE Vacancy የተሰኘ አሳሳች መተግበሪያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሰፊው እየተሰራጨ እንደሆነ በመጥቀስ፤ ይህ መተግበሪያ በቴሌግራም እና ዋትስአፕ ወደ ደንበኞቹ እየደረሰ መሆኑን ጠቁሟል።

መተግበሪያው በስልክ ላይ ከተጫነ ያለ ፈቃድ ገንዘብ ማስተላለፍ እንደሚችልም አሳውቋል።

ባንኩ ከዚህ አይነት አደጋ ለመጠበቅ ከቴሌግራም ወይም ዋትስአፕ መተግበሪያዎችን አታውርዱ ብሏል።

ደንበኞች መሰል ተግባራት ሲገጥሟቸው በ951 ነጻ የስልክ መስመር ደውለው እንዲያሳውቁ አሳስቧል።

በተመጣጣኝ ዋጋ
16/01/2025

በተመጣጣኝ ዋጋ

16/01/2025
29/10/2024

ለአዲሶቹ ተከታዮቼ ምስጋና! በመቀላቀልዎ ደስ ብሎኛል! Acmad Qafar, Bëšřé Bøÿ, Ababa Barihune, Jamaa Mohammed

Address

ኢትዮዺያ
Mekelle
1234567789

Telephone

+251914422732

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አርሂቡ ጫት ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share