Iconia Christian Counseling and Training Service

Iconia Christian Counseling and Training Service Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Iconia Christian Counseling and Training Service, Consulting Agency, Sebeta.

31/10/2022

ሕይወታችሁን የሰው ጥገኛ አታድር።
ሰው ሁልጊዜ እሱን የሕይወት ተከታይ ሆነ ብቻ ላይ የጥገኛነት (ሐዋርያው) እንድትሆንለት ይፈልጋል።
ይበልጥ የሕይወትህ ልጓሙን ተጎታች አድርጎት መኖር ይፈልጋል እና ሕይወትህን ለማንኛውም እጅ አትሰጥ።

31/10/2022

ኤፌ. 2፥4-10
------------
ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥

በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።..
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።

28/10/2022
25/10/2022

በሕይወትህ ጉዞ ላይ ማንኛውም ባዶነት አይታይ
ዘጸ 4:1-4
------------
ሙሴም መለሰ፦ እነሆ አያምኑኝም ቃሌንም አይሰሙም፦ እግዚአብሔር ከቶ አልተገለጠልህም ይሉኛል አለ።

እግዚአብሔርም፦ ይህች በእጅህ ያለችው ምንድር ናት? አለው። እርሱም፦ በትር ናት አለ።

ወደ መሬት ጣላት አለው፤ እርሱም በመሬት ጣላት፥ እባብም ሆነች፤ ሙሴም ከእርሷ ሸሸ።

እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የአባቶቻቸው አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ፥ እግዚአብሔር እንደ ተገለጠልህ እንዲያምኑ እጅህን ዘርግተህ ጅራትዋን ያዝ አለው። እጁንም ዘርግቶ ያዛት በእጁም ውስጥ በትር ሆነች።

❤  አማኝ❤===============✍️ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በስሙ ያመኑትን አማኞች በዚህ ምድረበዳ አለም ብቻቸውን አልተዋቸውም ከአባቱ ዘንድ አጽናኝ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል።ከዚ...
25/10/2022

❤ አማኝ❤
===============
✍️ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በስሙ ያመኑትን አማኞች በዚህ ምድረበዳ አለም ብቻቸውን አልተዋቸውም ከአባቱ ዘንድ አጽናኝ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል።ከዚህም የተነሳ ቅዱሳን ይህንን ምድረበዳ አለም አቋርጠው የተባረከውን ተስፋቸውን ኢየሱስ ክርስቶስን እስኪገናኙ ድረስ መንፈስ ቅዱስ በተለያየ አይነት መንገድ ይረዳቸዋል።

✍️ በአዲስ ኪዳን ስለመንፈስ ቅዱስ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ስናጠና በኢየሱስ ክርስቶስ የቤዛነት ስራ አምነው የጸደቁትን ቅዱሳን በተለያየ አይነት አገልግሎት እንደሚያገለግላቸው ተጽፏል።

✍️ አማኞች ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለን ህብረት ለመንፈሳዊ ህይወታችንና ለእድገታች አማራች የሌለው እውነት ስለሆን ከእርሱ ጋር ያለንን ህብረት ልናሳድግ ይገባናል።

📌 መንፈስ ቅዱስ ከአማኞች
ጋር በተያያዘ የሚሰራው ስራ፦
===================
1) ዳግም ልደትን ይሰጣል
------------------
ቲቶ 3
5፤ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤

2) ይመራናል።
-------------
“ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።”ዮሐንስ 16፥13
3) ያስተምረናል።
-------------
“አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።”ዮሐ 14፥26
4) ያጽናናልና (ይመሰክርናል።
---------------------
“ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤”ዮሐንስ 15፥26
5) የጸሎት አቅም ይሰጠናል።
--------------------
ሮሜ 8
26፤ እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤
6). የጸጋ ስጦታን ይሰጣል።
-------------------
1ኛ ቆሮ 12
⁷ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ሰው የሚሰጠው ለጋራ ጥቅም ነው።

¹¹ እነዚህ ሁሉ የዚያው የአንዱ መንፈስ ስጦታዎች ሲሆኑ፣ ለእያንዳንዱ ሰው እርሱ ራሱ እንደ ፈቀደ ይሰጠዋል።
7) የእግዚአብሔርን ነገር እንድንረዳ ያደርገናል።
-----------------------------------
1 ቆሮ 2
12፤ እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም።
8) የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆንን ይመሰክርልናል።
---------------------------------
ሮሜ 8
16፤ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።
9) የእድሜ ዘመን የሀጥያት ስርየት እንዳገኘን ይመሰክርልናል።
---------------------------------
ዕብ 10
17፤ ብሎ ከተናገረ በኋላ፥ ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል።
10) ክርስቶስን እንድንናፍቅ ያደርገናል
----------------------------
ራእይ 22 (Revelati

Address

Sebeta

Telephone

+251913027490

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Iconia Christian Counseling and Training Service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share