ሶዶ መብራት ኃይል አ/ቃ/ሕ/ቤ/ያን ሁለንተናዊ የልጆች አገልግሎት

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • ሶዶ መብራት ኃይል አ/ቃ/ሕ/ቤ/ያን ሁለንተናዊ የልጆች አገልግሎት

ሶዶ መብራት ኃይል አ/ቃ/ሕ/ቤ/ያን ሁለንተናዊ የልጆች አገልግሎት ምሳሌ 22:6NASV
[6] ልጅን የሚሄድበትን መንገድ አስተምረው፤ በሚሸመግልበት ጊዜ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።

“እስከዚህ ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል!” — 1ሳሙኤል 7፥12የአንድ ዓመት ጉዞአችንን በማሰብና፣ አጠቃላይ አመቱን ድል እና ስኬት እንዲሁም  የ“ልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት” በረከትን፤...
24/08/2026

“እስከዚህ ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል!” —
1ሳሙኤል 7፥12

የአንድ ዓመት ጉዞአችንን በማሰብና፣ አጠቃላይ አመቱን ድል እና ስኬት እንዲሁም የ“ልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት” በረከትን፤የረዳንን እግዚአብሔርን በአንድነት አመስግነናል። 🙏

በዚህ አመት ያለፍንባቸው ፈተናዎች፣ ያገኘናቸው ድሎች፣ እና የአገልግሎታችን ፍሬዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ጸጋና እገዛ ምስክሮች ናቸው።

ስለዚህ ለአመቱ፣ ለእያንዳንዱ መምህር፣ ለልጆቻችን እና ለ“የልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት” እግዚአብሔር ስለሰጠን ስኬት እና መከናወን እግዚአብሔር ይመስገን! 🙌

ወደፊትም በአንድነት፣ በፍቅርና በታማኝነት ልጆችን ወደ ክርስቶስ መንግስት ለማምጣት እንትጋ። ❤️

#የልጆችወንጌልፌስቲቫል #ልጆችለክርስቶስ #እግዚአብሔርይመስገን

📅Day7  እሁድ ከሰዓት 📌የምስጋና እና አድናቆት ቀን✨የመምህራን ልዩ ዝግጅት
19/08/2026

📅Day7 እሁድ ከሰዓት
📌የምስጋና እና አድናቆት ቀን
✨የመምህራን ልዩ ዝግጅት

📅Day7 📌part1 ማለዳ አምልኮ እና የሰንበት ትምህርት ተማሪዎች ሽልማት እና የታዳጊ ልጆች ምርቃት
18/08/2026

📅Day7

📌part1 ማለዳ አምልኮ እና የሰንበት ትምህርት ተማሪዎች ሽልማት እና የታዳጊ ልጆች ምርቃት

ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን! 🙏የልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት በድልና በስኬት አጠናቀናል። ይህ ሁሉ እንዲሆን የረዳንና ያገዘን አምላካችን እግዚአብሔር ከዘላለም እስከ ዘላለም ስሙ የተ...
17/08/2026

ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን! 🙏
የልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት በድልና በስኬት አጠናቀናል። ይህ ሁሉ እንዲሆን የረዳንና ያገዘን አምላካችን እግዚአብሔር ከዘላለም እስከ ዘላለም ስሙ የተመሰገነ ይሁን! 🙌

ውድ መምህራን እና እስተባባሪዋች

ከሀሳብ እስከ ዕቅድ፣ ከዕቅድ እስከ ዝግጅት፣ ከዝግጅት እስከ ተግባር፤አብራችሁን ስትፀልዩ፣ ስትዘጋጁ፣ ስትለፉና ስትደክሙ ነበር። ስናዛችሁ ስለታዘዛችሁን፣ ስንወቅሳችሁም እንደ አገልጋይ በትህትናና በቅንነት ስለተቀበላችሁን እናመሰግናለን። ❤️ይህን አገልግሎት በእጃችሁ ብቻ ሳይሆን በልባችሁ ጭምር ስለተሸከማቹ እግዚአብሔር አምላክ ይባርካችሁ።የልጆችን ሕይወት ለማቅናት፣ ወንጌልን ለማድረስና ልጆችን በእግዚአብሔር መንገድ ለማሳደግ ያደረጋችሁት ድካም በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ አለው።

“ስለዚህ፥ በጌታ ሥራ ሁልጊዜ ብዙ ሁኑ፤ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን እያወቃችሁ።” — 1 ቆሮንቶስ 15፥58

ውድ የቤተክርስቲያናችን አባቶች፣ የአስተዳደር ሽማግሌዎች፣

በዚህ የልጆች የወንጌል አገልግሎት ላይ ለሰጣችሁን ድጋፍ፣ ምክር፣ ጸሎትና አቅጣጫ ከልብ እናመሰግናለን። ለዚህ ሥራ ከጎናችን በመቆም፣ በመደገፍና በማበረታታት ያደረጋችሁት አስተዋጽኦ ለዚህ ስኬት ድርሻ አለው።ለልጆች አገልግሎት ቦታና ዕድል ስለፈጠራችሁ፣ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ልንል እንወዳለን።

ውድ ወላጆች፣
ልጆቻችሁን በእምነት ለእኛ ስለሰጣችሁ፣ ከቤታችሁ ጀምሮ በጸሎት ስለደገፋችሁን፣ በቃላችሁ ስላበረታታቹን፣ እግዚአብሔር ይባርካችሁ። ❤️

እና ውድ ልጆቻችን… 🥰
አብራችሁን ስለቆያችሁ፣ ስለታዘዛችሁ፣ ስለታገሳችሁና ፍቅር ስላሳያችሁን እናመሰግናለን።የተማራችሁትን አትርሱ።
የሰማችሁትን ቃል በልባችሁ ጠብቁ።
ይህ ሳምንት ቢጠናቀቅም፣ በልባችሁ የተዘራው የእግዚአብሔር ቃል ግን ፍሬ እንዲያፈራ እንጸልያለን። 🌱

ለቀጣዩ ዓመት የልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት እስክንደርስ ድረስ፣ ሁላችንንም እግዚአብሔር ጠብቆ በሰላም ያድርሰን! 🙏

📅Day 4 📋የመንፈስ ፍሬ ቀን ገላትያ 5:22-23 [የመንፈስ ፍሬ ግን ፤ 📌ፍቅር፣ 📌ደስታ፣📌 ሰላም፣📌ትዕግሥት፣ 📌ቸርነት፣ 📌በጎነት፣ 📌ታማኝነት፣ 📌ገርነት፣📌 ራስን መግዛት ነው።
14/08/2026

📅Day 4
📋የመንፈስ ፍሬ ቀን
ገላትያ 5:22-23
[የመንፈስ ፍሬ ግን ፤
📌ፍቅር፣
📌ደስታ፣
📌 ሰላም፣
📌ትዕግሥት፣
📌ቸርነት፣
📌በጎነት፣
📌ታማኝነት፣
📌ገርነት፣
📌 ራስን መግዛት ነው።

📅Day 3🛐የወንጌል ቀን እና የታዳጊዎች ስልጠና 📋"የሐሰት ትምህርት"   #ስለ  #ሁሉሞተ
13/08/2026

📅Day 3
🛐የወንጌል ቀን እና የታዳጊዎች ስልጠና 📋"የሐሰት ትምህርት"
#ስለ #ሁሉሞተ

📅Day 2 🛐የፅሎት ቀን "ጌታዬ ይሰማኛል እኔም እፅልያለው"   #ስለ  #ሁሉሞተ
12/08/2026

📅Day 2
🛐የፅሎት ቀን "ጌታዬ ይሰማኛል እኔም እፅልያለው"
#ስለ #ሁሉሞተ

📅Day1 ሰኞ 4/12/18📋የመጽሐፍ ቅዱስ ቀን   ፕሮግራማችን በማረ እና ደስ በሚል ሁኔታ እያሳልፍን እንገኛለን።📌የእግዚአብሔርን ቃል ተምረናል📌በመዝሙር አምልከናል 📌የመድርክ እና የውጭ ጨ...
11/08/2026

📅Day1 ሰኞ 4/12/18
📋የመጽሐፍ ቅዱስ ቀን

ፕሮግራማችን በማረ እና ደስ በሚል ሁኔታ እያሳልፍን እንገኛለን።

📌የእግዚአብሔርን ቃል ተምረናል
📌በመዝሙር አምልከናል
📌የመድርክ እና የውጭ ጨዋታዎችም ነበሩን።

የነበረን ጥሩ ጊዜ ይህን ይመስላል በምስል 🖼️

(ማክሰኞ) በተመሳሳይ ፕሮግራማችን ይቀጥላል።
⏰ሰዓት፡ጥዋት 2:30-6:00
#ስለ #ሁሉሞተ

እንኳን ለ2018ዓ.ም የልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት በሠላም አደረሳችሁ!አደረሰን ይህ የልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት በትላንትናው ዕለት በአጥቢያችን በአባቶች ቡራኬ እና ፀሎት በይፋ ...
10/08/2026

እንኳን ለ2018ዓ.ም የልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት በሠላም አደረሳችሁ!አደረሰን
ይህ የልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት በትላንትናው ዕለት በአጥቢያችን በአባቶች ቡራኬ እና ፀሎት በይፋ የተጀመረ ሲሆን ከዛሬ ሰኞ እስከ እሁድ ድረስ በተለያዩ መርሃግብር የሚካሄድ ይሆናል።
#አንዱስለሁሉሞተ

 # # # 🌈 አንድ ቀን ቀረው! 🌈ከነገ ነሃሴ 3-10በ ቤ/ክናችን የምናከብረው **የልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት** በደስታ እና በትጋት ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ደርሷል። 💙ከጸሎት ጀምሮ ...
08/08/2026

# # # 🌈 አንድ ቀን ቀረው! 🌈

ከነገ ነሃሴ 3-10በ ቤ/ክናችን የምናከብረው **የልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት** በደስታ እና በትጋት ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ደርሷል። 💙

ከጸሎት ጀምሮ ለዚህ ፕሮግራም ስኬት በትጋት በተለያዩ ዘርፎች ስንዘጋጅ ቆይተናል። ዛሬም የመጨረሻውን የግቢ ማስዋብና የማጽዳት ሥራ ከልጆቻችን ጋር በጋራ በአንድነት አከናውነን፣ **የአንድ ቀን ዕድሜ ብቻ ቀርቶናል!** 🎉ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን 🙏

በዚህ ሁሉ ጉዞ ከጎናችን ለነበራችሁ፣ በጸሎት፣ በጊዜ፣ በጉልበት እና በሀሳብ ለደገፋችሁን ሁሉ **ምስጋናችን ከልብ ነው!** 🙏💙
እግዚአብሔር የሰጣችሁትን ፍቅርና ትጋት ይባርክላችሁ።

👧🏽👦🏽 **ውድ ልጆቻችንና ወላጆቻችን፣ እንኳን ለዚህች ድንቅ ቀን አደረሳችሁ!** ❤️
!🎊✨

** #የልጆችየወንጌልፌስቲቫል

Address

Sodo

Telephone

+251938845697

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሶዶ መብራት ኃይል አ/ቃ/ሕ/ቤ/ያን ሁለንተናዊ የልጆች አገልግሎት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share