24/08/2026
“እስከዚህ ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል!” —
1ሳሙኤል 7፥12
የአንድ ዓመት ጉዞአችንን በማሰብና፣ አጠቃላይ አመቱን ድል እና ስኬት እንዲሁም የ“ልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት” በረከትን፤የረዳንን እግዚአብሔርን በአንድነት አመስግነናል። 🙏
በዚህ አመት ያለፍንባቸው ፈተናዎች፣ ያገኘናቸው ድሎች፣ እና የአገልግሎታችን ፍሬዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ጸጋና እገዛ ምስክሮች ናቸው።
ስለዚህ ለአመቱ፣ ለእያንዳንዱ መምህር፣ ለልጆቻችን እና ለ“የልጆች የወንጌል ፌስቲቫል ሳምንት” እግዚአብሔር ስለሰጠን ስኬት እና መከናወን እግዚአብሔር ይመስገን! 🙌
ወደፊትም በአንድነት፣ በፍቅርና በታማኝነት ልጆችን ወደ ክርስቶስ መንግስት ለማምጣት እንትጋ። ❤️
#የልጆችወንጌልፌስቲቫል #ልጆችለክርስቶስ #እግዚአብሔርይመስገን