ብርሃን ዘበአማን

ብርሃን ዘበአማን የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው

ከዘጠኙ አበይት በአላት አንዱ ስቅለት ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአለም ቤዛ ሊሆን መከራ የተቀበለበት፣ስለሃጢአታችን በቀራንዮ ኮረብታ በእፀ መስቀል ላይ ስጋውን የቆረጠበት፣ደሙን ያፈሰሰበት ራሱ...
18/04/2025

ከዘጠኙ አበይት በአላት አንዱ ስቅለት ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአለም ቤዛ ሊሆን መከራ የተቀበለበት፣ስለሃጢአታችን በቀራንዮ ኮረብታ በእፀ መስቀል ላይ ስጋውን የቆረጠበት፣ደሙን ያፈሰሰበት ራሱን ስለእኛ አሳልፎ የሰጠበት እለት ነው:: የሚከበረውም በስግደት፣ በፆም፣ በፀሎት፣ በንባብና በትምህርት ነው፡፡ "አምላክ አለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ሰው ሆኖ አለሙን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል" እንዲል የሰው ልጅ በበደለና ባልታዘዘ ጊዜ "እሱን የማትሰማ ነፍስ ትሞታለች" እንደተባለ ዘዳ 18፤15 የሃጢአት ደመወዝም ሞት ነውና ሰው የስጋ ሞትንና የነፍስ ሞትን አገኘ፡፡ ይህንንም ሞቱን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ የገደለው::
እኛ ልጆቹን ሁሉ ከሞት ወድ ህይወት ከድቅድቅ ጨለማ ወድ ብርሃን አፈለሰን::
#ተሰቀለ #ሞተ
1. የእኛን ሞት ለመሞት፡፡ ሮሜ 5፣15

2. ፈውስን እናገኝ ዘንድ ፡፡ ኢሳ 53፣5

3. 7ነትን እንወርስ ዘንድ መርገማችንን ወስዶ ተሰቀለ፡፡ ዘዳ 21፣23

4. የእኛን የበደል ቅጣት እርሱ ሊቀጣ፡፡ ኢሳ 53፣6

#በሞቱም
1. ህይወትን አግኝተናል- ሞት ነግሶብን ነበርና ያጣነውን ህይወት አገኘን፡፡ 1ቆሮ 5፣12

2. የህይወትን ምግብ አግኝተናል- ስጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ህይወት አለው፡፡ ዮሃ 6፣53

3. ሰላምን አግኝተናል- "ሰላምን እተውላችሁ፣ሰላሜን እሰጣችሁ..." የሐ 14:27

4. አዲስ ሰው ሆነናል- "ከእንግዲህ ወዲያ ለሃጢአት እንዳን7ዛ የሃጢአት ስጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰውነታችን ከእርሱ ጋር እንደተሰቀለ እናውቃለን። ሮሜ 6፣6

5. ታርቀናል- "ጠላቶቹ ሳለን ከእግዚአብሄር ጋር በልጁ ሞት ታረቅን.." ሮሜ 5፣10፡፡

በነፃነት ልንኖር ነፃ ያወጣንን ጌታ በማሳዘን እና ፍሬ ቢሶች በመሆን ዳግም በባርነት ቀንበር እንዳንያዝ እግዚአብሄር ይርዳን::

ሆሳዕና በአርያም  🌴 "አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን፤አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና።" መዝ 118፥25
13/04/2025

ሆሳዕና በአርያም

🌴 "አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን፤
አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና።" መዝ 118፥25

ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል፡፡"(ማቴዎስ 6፥34)“ጌታ ቅርብ ነው፡፡ በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ ...
07/04/2025

ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል፡፡"

(ማቴዎስ 6፥34)

“ጌታ ቅርብ ነው፡፡ በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ፡፡"

(ፊልጵስዩስ 4፥6)

ትናንት አልፏል፡፡ ዛሬ ላይ ትኩረት እናድርግ፡፡ እግዚአብሔር አዲስ ነገር ያደርጋል፡፡

ነገ ምን ሊከሰት እና ሊመጣ ስላለው ነገር በማሰብ ተስፋ አንቁርጥ፡፡ በሚመጣው በማንኛውም አስቸጋሪ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይረዳናል ።

መጨነቃችንን እናቁም፡፡ ወደ ፊት መራመዳችንን እንቀጥል፡፡

ችግሩ ሊኖር ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ሁልጊዜም ለእኛ ታማኝ መሆኑንም ማስታወስ አለብን።

ሁላችንም በእግዚአብሔር ጥበቃ ስር መሆናችን የሚታወቅና የተረጋገጠ እውነት ነው ፡፡ የእኛ እርዳታ የሚመጣው ከእርሱ ነው፡፡

"እግዚአብሔርም ለድሆች መጠጊያ ሆናቸው፧ እርሱም በመከራቸው ጊዜ ረዳታቸው ነው፡፡ ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፧ የሚሹህን አትተዋቸውምና፡፡"

(መዝሙር 9 9-10)

# አትጨነቅ፣ ሁሉም ነገሮች በእግዚአብሔር እጅ
ናቸው

#አትናቴዎስ (Christology)

Address

Welk'it'e

Telephone

+251904189833

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ብርሃን ዘበአማን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ብርሃን ዘበአማን:

Share