21/10/2021
ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብርን ቀንሶ ስለማስቀረት 1ከመቀጠር ከሚገኝ ገቢ ላይ ግብርን ቀንሶ ማስቀረት ።ማንኛውም ቀጣሪ ከመቀጠር ከሚገኝ ገቢ ላይ ግብር ስለመጣል በተደነገገው መሰረት የቅጥር ገቢ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ለተቀጣሪው በሚከፍልበት ጊዜ በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈፃሚ በሚሆኑ መጣኔዎች መሰረት በእያንዳንዱ የክፍያ ጊዜ መከፈል የሚኖርበትን የገቢ ግብር ከጠቅላላው ክፍያ ላይ ቀንሶ የማስቀረት ግዴታ አለበት:: ።ቀጣሪውተቀጣሪው ከአንድ በላይ የሆነ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ እንዳለው ያወቀና ሌላው ቀጣሪ በጠቅላላው የተቀጣሪው ገቢ ላይ ተመስርተው የገቢ ግብሩን ቀንሰው እንደማያስቀሩ ያወቀ እንደሆነ ቀጣሪው የተቀጣሪውን ገቢ በማጠቃለል የገቢ ግብር ቀንሶ የማስቀረት ግዴታ አለበት:: ።ቀጣሪው ለተቀጣሪው ከሚከፍለው ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ላይ ግብር ቀንሶ የማስቀረት ግዴታው ለሰራተኛው ከሚፈፅማቸው ክፍያዎች ላይ በቀጣሪው ተቀናሽ መደረግ ካለባቸው ሌሎች ግዴታዎች ቅዲሚያ ይኖረዋል::